💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🧬
የታሪኩ ርዕስ
👩🎓 #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አንድ 1️⃣
#✍_ፀሀፊ_☞_#ዘቢባ_ሱልጣን
ሁሉም ሰው ከትልቅ እስከ ትንሹ የልጅነት ጊዜውን የማይናፍቅ የለም እኔም ምንም እንኳን የዚን ያክል የመቦረቂያ እና የመጫወቻ ጊዜ ባይኖረኝም ትንሽም ብትሆን ያሳለፍኳት ነገር ትናፍቀኛለች ከአይምሮዬም አይጠፋም። እኔ የዘጠናዎቹ ትውልድ ነኝ። የዘጠናዎቹ ትውልድ በ facebook ግሩፕ ላይ ካያቹ በጣም የሚወራለት የዋህ እና ምንም የማያውቅ ትውልድ ነው።ይህ ግሩፕ በface book ብቻ ሳይሆን በ telegram ብዙ ተከታዮችን ያፈራ ነው።
ሲቀለድም የዘጠናው ትውልድ ሲጣላ ሮጦ ወደ ቤቱ ገብቶ አንበሳ ጫማውን አስርጎ ነበር የሚወጣው ያሁኑ ትውልድ ግን ሮጦ ወደ ቤቱ ገብቶ ስለት ይዞ ይወጣል ይባላል። የገጠሩን ባላውቅም እዚህ አዲስ አበባ በኛ ጊዜ ትምህርት የሚጀመረው በ ቄስ ትምህርት ቤት ነው። ኬጂ አናውቅ ነርሰሪ አናውቅ ሙስሊሙም ክርስትያኑም የቄስ ትምህርት ቤት ይገባል።
እኔም በ 6 አመቴ የቄስ ትምህርት ቤት አሀዱ ብዬ ተመዘገብኩ።እኛን ያስተማሩን የኔታ ክብር ምስጋና ይገባቸውና አንድም እውቀት አልሰሰቱብንም።ስንረብሽ ስናጠፋ እመሬት ተደፉ እያሉ ሲያሻቸውም ብላክቦርዱን ሳሙ እያሉ ቂጣችንን እየገረፉን አንድም ነገር ሳይገባን እንዳናልፍ አድርገው አስተምረውናል።ሲያስነጥሱ የኔታን ይማርልን እያልን ክፍል ስንገባም በአንድ ሰፊ የተሰነጠቀ ጣውላ(መቃን) ላይ ከ10_15 ልጆች አብረን እየተቀመጥን ጠበበን ቆረቆረን ሳንል የኔታም ሲገቡ እንደምን አደራቹ
ወይም እንደምን ዋላቹ ሲሉን ሙስሊም ክርስትያኑ በአንድ ላይ ደህና እግዚአብሄር ይመስገን መምህር!!!! እያልን አሳልፈናል።
ወላሂ ያን ጊዜ በጣም ነው የሚናፍቀኝ ዘረኝነት የለ መናናቅ የለ መኖር ብቻ! ለነገሩ የሚፍጀው ያሁኑ ትውልድ ነው እንጂ በኛ ዘመን አንድ አንባሻ የክፍል ተማሪዎችን በሙሉ ያዳርስ ነበር።ብቻዬን ልብላ የለም።መቼም የማይረሳኝ ግን ያንዳችንን ምሳ
በ እረፍት ሰአት ያንዳችንን ደግሞ ምሳ ሰአት የምንበላው ነገር ነው። ኢሊፖፕ ከረሜላ ገዝተን እስከ ማስቲካው ድረስ አንዳችን ጠብተን ማስቲካውን ደግሞ ለሌላችንን የምንካፈለው ነገርም አይረሳም።
ለነገሩ ይሄን ባህሪ ያላበሰን ዘመናችን ብቻ ሳይሆን መዲናችን አዲስ አበባም ጭምር ነው። ብዙዎች አዲስ አበባ መወለድ በራሱ first degree ነው ይላሉ።እውነት ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። አዲስ አበባ ጥብቅብቅ ጭንቅንቅ ያለች የተጣበበች ብትሆንም ህዝቦቿ በጭንቅንቁ ውስጥ ፍቅርን ለግሷቸዋል። ሀገሪቷ ሰፊ ከመሆንዋ የተነሳ ነዋሪዎችዋም ከጥግ እስከጥጉ የሚያውቋት አይመስለኝም። ቀና ቢሉ የሚታየው ሰማይ ሳይሆን ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ነው።በፎቅ ተጥለቅልቃለች። ቂያማ ሲደርስ ፎቅ ይበዛል እርጉዝ ይበዛል ዚና ይስፍፍል የተባለው እውነት መሆኑም የሚረጋገጠው እዚቹ ከተማ ላይ ነው።
አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ ዘር ከዘር የማይለይ ኦሮሞ ከጉራጌ አማራ ከትግራይ ሶማሌ ከኦሮሞ አማራን ከስልጤ ሀመርን ከጉራጌ ሀድያን ከኦሮሞ ወላይታን ከስልጤ አደባለቃ ድራ ሞሽራ የያዘች ብቸኛ ከተማ አዲስ አበባ ናት። ለስራ እና ለጉብኝት የሚመጡ ቻይኖች እና የተለያዩ ሀገር ዜጎች መመልከት የተለመደ ነው። ሰውም ሌላ ከተማ ስራ የለም የተባለ ይመስል የሚጎርፈው አዲስ አበባ ነው። የገጠር ልጅ አዲስ አበባ ሲመጣ የአሜሪካ ዲቪ እንደደረሰው የሚቆጥረው እና የሚደሰተውም ለዚህ ይመስለኛል። ለነገ መጨነቅ አያውቅም መልበስ መጠጣት መብላት የየለት ተግባራችን ነው። ዝንጥ ብላ ስትዝናና አይተህ ወደሀት ተከትለሀት ቤትዋ ብትገባ ግን የፈራረሰ ሊወድቅ አንድ ሀሙስ የቀረው ቤት ነው የሚሆነው።
አዲስ አበባ አንዱ ቤት አንዱ ላይ ተጭኖ ሌላኛው ደግሞ በአንዱ ቤት ተንጠልጥሎ ነው የሚሰራው።ጎረቤት ቡና ለመጥራት በር ከፍቶ መውጣት አይጠበቅበትም እዛችው የቤቱ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ እከሌ!! ብሎ ቢጣራ ድምፁ ከጎረቤቱ ጆሮ ውስጥ ገብቶ ድርግም ይላል።ግን እኔን የማይገባኝ ነገር ቻይና ፈረንጅ ነው እንዴ? ልጅነቴ ይሁን ጅልነቴ ባላውቅም ፈረንጅ አይመስሉኝም።መልሱን ለናንተ ትቼዋለው።
አዲስ አበባን ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል በተለይ ግን የአብነት እና የአፍሪካ ትልቁ የገበያ ማእከል የሆነው የመርካቶ ልጅ መሆን ግን ይበልጥ መታደል ነው። የአብነት ልጅ ሲናደድ በድንጋይ ይበረቅሳል የተክለሀይማኖት ልጅ ሲናደድ 2 ተቆራጭ ኬክ አዞ ይበላል የመርካቶ ልጅ ሲናደድ ጉሮሮ ይዘጋል የቦሌ ልጅ ሲናደድ ያለቅሳል ተብሎ ይተረታል። አዲስ አበባ ላይ ሙዝ አንድ በልቶ መድገም እና ካፌ ቁጭ ብለህ ለብቻህ ሁለት ኬክ አዘህ መብላት ነውር ነው። ተክለሀይማኖት መርካቶ እና አብነት እንዲሁም አቶቢስ ተራ የአራዶች ሰፈር ተብሎ ሲጠራ ቦሌ እና መሰሎቹ የሀብታም ልጆች ሰፈር ነው። በዚህ መልኩ ከአብነት ትንሽ ዝቅ ብሎ ልደታ ሚባለው ሰፈር አድጌ ከቄስ ትምህርት ቤት ወደ አንደኛ ክፍል ገባሁ.......
Part 2⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል ከ60👍 በኋላ ይለቀቃል ቶሎ ቶሎ ተጫኑት እንዲለቀቅ አንብባቹ ከጨረሳቹ በኋላ👍