💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ ሶስት 3⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
ምነው ይሄ ቀን ባልተፈጠረ ወይም ጥዋት ሳልነሳ በዛው ሞቼ በነበረ ብዬ ተመኘሁ .አይኔ ማመን አልቻለም ... ሳይንስ አስተማሪያችን ስታስተምረን እንስቅባት የነበረው በሀፍረትም አንገታችንን እንደፋ የነበረው የሴት ልጅ ፀጋ የሆነው የወር አበባዬ(ሀይዴ) መምጣት በሌለበት ቦታ መጣ።
ፈተናዉን ሰርቼ ጨርሼ ልሰጥ ስነሳ ወንበሩ በደም ተጨማልቆ ልብሴ በደም ተዘፍዝፎ አገኘሁት።መልሼ ቁጭ አልኩ።የምትፈትነዉ መምህርም ልትኮርጂ ነበር የተነሳሽው ከክፍል ውጪ ለ ዳይሬክተሩ ነው ማስረክብሽ እያለች ደነፋችብኝ
......እኔ ግን አልወጣም አልኳት። አልወጣም ስላት ንዴትዋ ተባብሶ ነይ ውጪ እያለች ትጎትተኝ ጀመር።
እኔም እንባዬ ከአይኖቼ እየዘነበ ኩብልል ኩብልል ብሎ ከጉንጬ እየተንሸራተተ አገጬን ረግጦ ደረቴን እያራሰ አልወጣም ብዬ ወንበሩን በሁለት እጄ ጠፍሬ ያዝኩት። አልወጣም ያልኩት በደም የተነከረው ልብሴን ነውሬን እንዳያዩብኝ ብዬ እንጂ ንቄያት አልነበረም። ጉልበትዋ ከጉልበቴ ስላልተመጣጠነ አሽቀንጥራ አስወጣችኝ።
በአግራሞት ሲመለከቱኝ የነበሩት የኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ደሙን ባዩ ጊዜ የድንጋጤ ድምፅ ሁሉም አሰሙ ።የሂወቴ ፍፃሜ እንደሆነ ተሰማኝ አላህ የረገመኝም እንደሆንኩም ተሰማኝ።አለቀስኩ።
...ፈታኝዋም መምህር ለምን አልነሳም እንዳልኩ ሲገባት መልሳ ታባብለኝ ጀመር። ሴት ተማሪዎቹም አይዞሽ ሁላችንም እኮ ሊመጣብን የሚችል ነገር ነው ነገ እኛም እንዳንቺ መሆናችን አይቀርም ለትንሽ ጊዜ ነው አሉኝ። ሳይንስ አስተማሪዬ ተጠራች እና ትንሽ ምክር እንድትሰጠኝ አደረጉ። በነገሩ በጣም ደንግጫለሁ ሰዎቹ የሚያወሩትም ነገር አይሰማኝም።ብቻ እያለቀስኩ እንዳለ አስተማሪዬ መጣችና አስተምሬሽ የለ? እንዲህ እንዳትሆኚ እንዳትደነግጪ እኮነው ያስተማርኩሽ አንቺ የተመረጥሽ ሴት ነሽ አንቺ ካሁን በኋላ አድገሻል ልቦና ገዝተሻል ማለት ነው ፡ ይሄ ማለት ለወላጆችሽ የደረሰች ሴት ልጅ አላቸው ማለት ነው ልደነግጪ አይገባም እያለች አባበለችኝ።
ነገሩን መቀበል ያቃተኝ ገና የ 12 አመት ልጅ ስለነበርኩ እና በ 5 አመት የምትበልጠኝ ታላቅ እህቴ ይሄንን ነገር(ሀይድ) አለማየትዋም ጭምር ነበር። ብቻ እንደምንም ተረጋጋሁ
አመቱ አለቀ አሪፍ ውጤት አምጥቼ ከ 59 ተማሪ 10ኛ ወጥቼ ወደ 6ተኛ ክፍል ተዘዋወርኩ። 10 ደረጃን ይዤ ስላችሁ ንቃችሁ ወይም ስቃችሁብኝ ሊሆን ይችላል ግን በዛ ትምህርት ቤት 10ኛ መውጣት በጣም ትልቅ ውጤት ነው። 10 ደረጃን ይዤ ብወጣም አማካኝ ውጤቴ 91.6 ነበር። እዛ ትምህርት ቤት የተማረ ተማሪ መጨረሻኛ እንኳን ቢወጣ ከሌላ ትምህርት ቤት 1ኛ ከወጣው ተማሪ ጋር ቢወዳደር ያሸንፍል። የማርክ ልዩነት ሆኖ እንጂ መጨረሻኛ የሚያሶጣው እውቀቱ አይደለም። አንድም ተማሪ ሳያውቅ አይሄድም። 6ተኛ ክፍልን አሀዱ ብለን ጀመርን።ቁርአን መቅራትም ጀመርኩ።እኔና እየሩስ የለየልን እብዶች ሆነናል። ቀልባችን ያረፈበት ወይም ደሞ ቀልቡ እኛ ላይ ያረፈ ወንድ ስናገኝ አስቀድመን እኛ የፍቅር ደብዳቤ ከሽነን እንፅፋለን፡፡
ብዙ ጊዜ የምንፅፈዉ ደብዳቤም ----------ካየሁህ ቀን ጀምሮ ላንተ ያለኝ ስሜት ከእለት ወደየእለት እየጨመረ መጥቶዋል። ከልቤ አፍቅሬሀለው ያላንተ ወንድ አይታየኝም ፡ ስተኛም ስነሳም የማልመው ስምህን የምጠራዉ አንተን ነው አንተ ማለት ለኔ ከፈጣሪ የተሰጠህ ልዩ ስጦታ ነህ ፡ አንተ ማለት ለኔ እስትንፋሴ ተስፋዬ የመኖሬ ትርጉም ነህ። እባክህ እሺ ብለህ የፍቅር ጥያቄዬን ተቀብለህ ነብሴን አስደስታት ልቤን ከጭንቀት ገላግላት እኔ ያላንተ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል።ከፈጣሪ የተሰጠኝን ነገን የማይብህ ልዩ ስጦታዬ ነህ ከእናትም ከአባቴም አስበልጬ አፈቅርሀለው.......
ብለን እየፃፍን እንሰጣቸዋለን
.......ጥያቄያችን ተቀብለው እሺታን ሊያሰሙን ሲመጡ ከመናገራቸው በፊት አስቀድመን ውሸት መሆኑን እና ለጨዋታ መሆኑን እንነግራቸዋለን።በዚህ መልኩ በወንዶች ስሜት እየተጫወትን እንዝናናለን።
እኔም ግን አንደኛ ክፍል ስማር የማውቀው ከድር ላይ አይኔ አርፏል። ከድር ሰቃይ ተማሪ ሲሆን ቤቱ አሁን ከምማርበት ትምህርት ቤት አጠገብ ነው።የሚማረው እዛው የተዋወቅንበት ትምህርት ቤት ካራማራ ነው።
ሰሞኑ ከድር አዲስ ባህሪ አምጥቷል ያለወትሮው ከትምህርት ቤት እና ከመድረሳ ስወጣ እየጠበቀ ሰላምታ መስጠት ጀምሯል ለዛም ነው መሰለኝ አይኔ ያረፈበት።
Part 4⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
ቤተሰብ react ቀንሷል ታሪኩን ደስ ካላላቹ comment ላይ አሳውቁን
ከ60👍 በኋላ ይለቀቃል ቶሎ ቶሎ ተጫኑት እንዲለቀቅ አንብባቹ ከጨረሳቹ በኋላ👍