💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ ሰባት 7⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
እኔም እግሩ ስር ተደፍቼ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ ሁለተኛ አይለመደኝም የፈለከውን ቅጣኝ ወላጅ አታስመጣኝ ብዬ ለመንኩት በስተመጨረሻም 15 ግርፍት ተፈርዶብኝ ቂጤ እስኪላጥ ጠረፔዛ ላይ አስተኝተው ገረፉኝ።
እውነት ለመናገር አባቴን ከማመጣው አይደለም ቂጤ እስኪላጥ አካሌ እስኪሰባበር ቢገርፉኝ እመርጣለው። ምክንያቱም አባቴ ሱናደድ ሰይጣን ነው አንቆም ሊገለኝ ይችላል። ግርፋቱ እና ፍርሀቱ ተጨማምሮ እያንቀጠቀጠኝ ወደ ክፍል ገባሁ። ናትኔኤል የሆነች ልጅ ጠየቀችኝ ብሎ ለአባቱ ደብዳቤውን አሳይቶት አባቱ ደሞ ትምህርት ቤት መቶ ከሶኝ ነው ለዚህ የተዳረኩት። ከዛን ቀን ጀምሮ እኔና እየሩስ ደብዳቤ መፃፉን እርም ብለን ተውን።
እየሩስ ለከድር ያለኝን ስሜት ከነገርኳት ቀን ጀምሮ ካልነገርሽው እያለች ትጨቀጭቀኛለች። ለሱ ደብዳቤ ብትፅፊለት እኮ የሚመታሽ የለም እያለች የናቲን ጉዳይ እያስታወሰች ታስቀኛለች። በዚህ በኩል እስዋ በዛ በኩል ደሞ ይክላስ ተማሪዎች አላስቀምጥ አሉኝ እናም ደብዳቤ ፅፌ ልሰጠው ወሰንኩ።
ከድር ተክለ ሰውነቱ ረጅም እና ወፈር ያለ ነው ቡኒ አይን እና አመዳማ ወርቃማ የሚመስል ፀጉር አለው።እኔ ደሞ የሱ ተቃራኒ አጭር ቀጭን ነኝ። አብረን ስንሆን ላየን ሰው አባት እና ልጅ ነው የምንመስለው።
ሰኞ ረፋድ አካባቢ ደብዳቢውን ፃፍነው። ተፃፈ በ 20/06/2006 መልሱ ለ ጁመአ 24/06/2006 ብለን ቋጨነው። እናም ከክላስ ስንወጣ ልሰጠው ተስማማን
ከዛም ከመድረሳ ስወጣ እንደተለመደው ሰላምታ ተለዋውጠን ብቻ ደብዳቤውን ሳልሰጠው አለፍኩ። ልቤ በጣም ፈራ። እየሩስም ተናደደችብኝ እናም ነገ እኔ እሰጠዋለው ብላ በንዴት ቀማችኝ። አይነጋ የለ ነጋ ስንማር ውለን አስተማሪ አዳርቀን ..ወደ መድረሳ ስሄድ አገኘነው እና እዩ እሰጠዋለው ብላ እንዳልደነፍች ስታየው ተንቀጠቀጠች።ኧረ እራስሽ ስጭው ብላ ደብዳቤውን ሰጠችኝ። እኔም ሳልሰጠው አለፍኩ።
...... እዩ ተናዳለች ምክንያቱም ደብዳቤው ላይ ተፃፈ በ 20/06/2006 የሚለው ፅሁፍ ቀኑ በጨመረ ቁጥር ልንሰጠው ፈርተን እንዳቆየነው ይናገርብናል ብላ ተጨንቃለች።በስተመጨረሻም እሮብ በ 22/06/2006 አመተምህረት ደብዳቤውን ሰጠሁት። ከሰጠሁት በኋላ አይኑን ማየት ሞት መስሎ ታየኝ ፈራሁት። አላፈቅርሽም ተይኝ ቢለኝስ ምንድነው የማደርገው??? እያልኩ እራሴን በሀሳብ ወጠርኩ።
በሀሳብ ብዛት ሳልተኛ ስላደርኩ እራሴን በጣም አመመኝ በዚህም ምክንያት ሀሙስ ትምህርት ቤት ከመሄድ ቀረሁ። ጁመአም እራስ ምታቱ ቢሻለኝም አልተሻለኝም በሚል ስበብ በድጋሚ ቀረሁ።
ትምህርት ቤት ቀርቼ የማላውቀው ልጅ ዛሬ አመመኝ ብዬ ስቀር አባቴ በጣም ተጨንቆ ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ ብሎ ቢጋተተኝም ደህና ነኝ እረፍት ላድርግ ብዬ ነው ብዬ አረጋጋሁት። ደስ እንዲለውና ደህንነቴ እንዲታየው ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ ቤቱን አፀዳድቼ ቆንጆ ምስር ወጥ ሰርቼ ቤቱን ፏ ሽክ አደረኩት ።
ጁመአ ማምሻ አካባቢ እየሩስ ቤታችን መጣች እኔም ለምን እንደቀረሁ ጠየቀችኝ
.....እኔም አባቴ ስለነበር ትንሽ አሞኝ እንደሆነ ነገርኳት። ሻይ አፍልቼላት ከጠጣች በኋላ ልሸኝሽ ብያያት ተያይዘን ከቤት ወጣን እናም የቀረሁት ከድርን ላለማየት ብዬ እንደሆነ ነገርኳት።
....እስዋም የስንቱን ወንድ ፊት እንዳልፈተንን ዛሬ ምን ነክቶሽ ነው እንዲህ የምትሆኚው ??ብላ አደፍፈረችኝ እናም ነገ ቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርቱን እንዳልቀር አስጠንቅቃኝ ሄደች።
ቃልዋን ተቀብዬ ቅዳሜ ጥዋት ቦርሳዬን ይዤ ለሜካፕ ክላስ ዩኒፎርም ስለማይለበስ ሽቅርቅር ብዬ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ። ከድርን የማገኝባት ያቺ ፖል ብቻዋን ተገትራለች።የናፍቆት አይኔ እየተንከራተተ ትምህርት ቤቴ ገባሁ።
ተምረን ከጨረስን በኋላም ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወጣን። ከድር በተለምዶው ቦታው ቆሞዋል። ላናግረው ፈራሁ።
......አሰላሙ አለይኩም ሳልለው ዝም ብዬ ላልፍ ወሰንኩ እናም እየፈጠንኩ ስራመድ እዩ እንዳልሄድ እላዬ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቃብኝ መልሱን ሳንሰማ ዛሬ አንሄድም ብላ ትመልሰኛለች።አሁንም አመለጥኳት ብዬ ስጓዝ ከየት መጣች ሳልል ገፍትራ ወደነበርኩበት ትመልሰኛለች።
ሳልፈልግ በግዴ እየተንቀጠቀጥኩ ወደ ከድር አመራሁ እናም መልሱን ለመስማት እንደወታደር ፊት ለፊቱ ተገትሬ ቆምኩ
.......ከድርም
Part 8️⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
🔻ክፍል ስምንት ከ6️⃣0️⃣ 👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍😀 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!