💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አስራ ሁለት 1⃣2⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
ለማግባት ዝግጁ እስካልሆንኩ ድረስ ከወንድ ጋር የሀራም ግንኙነት ላልጀምር በአላህ ቃል ቁርአን መትቼ ማልኩ
አመቱ ማብቂያ ደረሰ ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ነን። የሚኒስትሪ ውጤት ወጣ። ይወድቃሉ ተብለን ስማችን ይጠራ የነበረው ዮናታን ዩሴፍ እና እኔ በተርታ 91.5 ,92.4 እና 93.6 አመጣን። ትምህርት ቤታችንም ሁላችንም የተፈተነዉ ተማሪዎች አልፈናል። ከዚህም ባሻገር ሁሉም ተማሪ ከ 77.3 በላይ በማምጣቱ ምክንያት ትምህርት ቤቱ ከ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የዋንጫ እና የማበረታቻ ሰርተፊኬት ሽልማት አግኝቶዋል። 4 ተማሪዎችም 99.9 በማምጣት በ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ተሸልመዋል። ከድርም 99.9 አምጥቶ ማለፉን ከሰፈሩ ልጆች ሰምቻለው። ደስ የሚል እና የሚያሳዝን አመት የማይረሱ ትዝታዎች ብዙ ነገር ተፈጥረዋል።
በከድር ፍቅር ታውሬ ዋናውን ነገር ረሳሁት። ሰባተኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ ማለትም የረመዳን ወር ላይ እነ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፤ልጅ አቡበከር አደም...........የመሳሰሉት በአሸባሪነት ስማቸው ተነስቶ ታስረዋል።
ለ እስልምናዬ ቦታ መስጠት የጀመርኩት እነ አቡኪ (አቡበከር አህመድ) ፤ አህመዲን ጀበል እና እነ ያሲን ኑሩ የመሳሰሉትን ኡስታዞቻችን አሸባሪ ናቹ ተብለው የታሰሩ ጊዜ ነው። እምነት ማለት ምን እንደሆነ የገባኝ ያን ጊዜ ነው። ሰላትም መስገድ የጀመርኩት በዛ ምክንያት ነው።
በተለይ ደግሞ የዛን ጊዜ የረመዳን ወር ፆም ማብቂያ የኢድ ሰላት ላይ በተደረገው ተቃውሞ ምክንያት በተነሳው ረብሻ ፖሊሶች ህዝቡን በፍልጥ ሲያደቁ እኔንም በደረሰኝ አንድ ዱላ እና የጉልበት መላላጥ አማካኝነት ነው ይበልጥ እስልምናዬን እንድወድ መንገድ የከፈተልኝ።እድሜዬ 13 ወይም 14 አመት ገዳማ ይሆነኝ ነበር።እድሜያችን በጨመረ ቁጥር አዳዲስ ነገሮችን አብረን እንማራለን አይምሮአችንም ማገናዘብ ይጀምራል።በተለይ ደግሞ ከ elementary ትምህርት ቤት ወደ hign school ስንሸጋገር መቆሚያው እና መቀመጫው ይጠፍናል። dv ደርሶት አሜሪካ የሚሄድ ሰው እንኳን የኛን ያክል አይደሰትም።
የትምህርት ጥግ የደረስን እስኪመስለን ድረስ ደስታችን ወደር አይኖረውም።ይሄ ስሜት ሳይሰማው ያለፈ አንድም ተማሪ የለም።እኔም በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነው ዘጠነኛ ክፍልን ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የገባሁት። ከ 1 እስከ 8 የተማርኩበት ትምህርት ቤት የግል ቢሆንም የሚኒስትሪ ውጤት ከወጣ በኋላ የሚመድበው ግን የመንግስት ትምህርት ቤት ባልቻ አባነፍሶ የሚባል ትምህርት ቤት ነው። እኔም የተመደብኩት ባልቻ ቢሆንም ካለሁበት ሰፈር ትንሽ ርቀት ስላለው አቅራቢያዬ ወዳለው ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ ጓደኛዬ አባት አማካኝነት ተመዘገብኩ።
ጓደኛዬ ኬብሮን ትባላለች ፕሮቴስታንት(ጴንጤ) ናት ኢለመንተሪም አብረን ነው የተማርነው። ከተመዘገብንም በኋላ ክፍል ተመደብን። ብዙ ተማሪ ስለነበር ዘጠነኛ ክፍል ብቻ 23 ክፍሎች ነበሩ።ዘጠኝ 1 ፤ ዘጠኝ 2 ፤ ዘጠኝ 3............ እየተባለ ነው ሚጠራው። እኔ የደረሰኝ ዘጠኝ 7 ሲሆን ኬብሮን የደረሳት ዘጠኝ 5 ነበር። ሁሉም ተማሪ ለኛ እንግዳ ስለነበር በ እረፍት እና በ ምሳ ሰአታት እየተገናኘን ብቻችንን እንቀመጣለን። ተማሪዎች ሲጫወቱ ሲላፉ እኛ ተመልካች ነን። ትምህርት ቤቱ በጣም ደብሮናል። ላይናችን ያስጠሉናል።
እኔም የሀብታሞቹ ልጆች ባህሪ ተጋባብኝ መሰለኝ ተማሪዎቹ ሊያናግሩን ሲሞክሩ ኩራት ኩራት ይለኛል። ገና ከትውውቃችን ስም ከተለዋወጥን በኋላ ቀጣዩ ከየት ትምህርት ቤት ነው የመጣሽው?? የሚል ጥያቄ ስለሆነ ይኬንን ጥያቄ እንዳቀረቡልኝ ስለ ትምህርት ቤቴ ዝና እና ስም እንዲሁም የልጥጥ ትምህርት ቤት እንደሆነ ክፍያውም ምን ያክል እንደሆነ ኮራ ብዬ በጋንኜ ቅመም ጨምሬ እነግራቸዋለው።
.....ቀስ በቀስ ሁላችንም የየራሳችንን ጓደኞች አፈራን
Part 1⃣3⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
🔻ክፍል 1️⃣3️⃣ ከ7️⃣0️⃣ 👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍😀 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!