🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 5️⃣
ዛተችብኝ።
ወዲያው ከውጪ ድምፅ ሰማች እየጎተተች ወደ ጓዳ አስገብታ አስቀመጠችኝ ድምፅ እንዳላወጣ አፌ ውስጥ ጨርቅ ጠቀጠቀችብኝ እንግዶቹ እስኪሄዱ አንድ ድምፅ ብሰማ ስመለስ እጨርስሀለሁ አለችኝና እየሳቀች እንግዶቹን ለመቀበል ወጣች ።
ሁለት ወንዶች ነበሩ ቁርሳቸውን ሰራርታ አብልታ ቡና አፍልታ እነሱን እስክትሸኝ ድረስ እኔ ጓዳ ቁስሌ እየጠዘጠዘኝ ቁጭ አልኩ።
እነሱን ሸኘችና ወደኔ መጣች ተነስ ውጣ ምሳ ሰርተህ አብላን እኔ ደክሞኛል ልተኛ ነው እኔ እንደተኛሁ ወደ ውጪ እወጣለሁ አጎትጋ እሄዳለሁ ብትል ለሰጆቼን ይንሳኝ ገድዬህ እጄን ለመንግስት ነው ምሰጠው አለችኝ።
የመታችኝ ቀስሉ እየጠዘጠዘኝ ተነስቼ ምሳ መስራት ጀመርኩ።
ሰርቼ አበላኋቸው ዛሬ እንደቅጣት ምንም ነገር አትቀስም ብላ አይኔ እያየ አጠገባቸው አስቀምጠውኝ እነሱ ተመግበው ጨረሱ ።
በዛ ሁኔታና ስቃይ ውስጥ ሆኜ እንደምንም እስከ 20 አመቴ ድረስ ከሷጋ ተቀመጥኩ ያባቴና የናቴን መልክ ምን አይነት እንደሆነ ሁላ አላቀውም ነበር።
20 አመቴ ላይ ከሷ እህል ሰርቄ ሸጥኩና ገንዘቧን ይዤ ዝም ብዬ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ ።
በስም ቀጨኔ መድሀኒአለም ሲባል ስለምሰማ ቀጨኔ መድሀኒአለም የት ነው የት ነው እያልኩ እየጠየኩ እዛ ደረስኩ
እኔ ገጠር በማቀው ሁሉም ሰው እርስ በርስ ይተዋወቃል ዝም ብዬ አንዱን ሰው የእንትናን ቤት አሳየኝ ብዬ ብጠይቀው ያሳየኛል።
አዲስ አበባም እንደዛው መስሎኝ ነበር ያገኘሁትን ሰው እንዳለ የአንተነህን ቤት ታቁታላችሁ እያልኩ ብጠይቅ ማንንም የሚያሳየኝ ጠፋ።
መሸብኝ እዛው አስፋልት ዳር ተደግፌ ነጋልኝ በሚቀጥለው ቀንም ያገኘሁትን ሰው ሁላ ስጠይቅ አመሸሁ እኔ የጠየኩበትና እሱ ያለበት አይገናኝም ኖሯል ለካ ሳጣው ተመልሼ ወደገጠር ወረድኩ።
ከዛን አክስቴ እግርህ እዚህ ቤት እንዳይረግጥ ብላ አባረረችኝ።
ማደሪያ አጣሁ የማርፍበት ቸገረኝ ዝም ብዬ ምግባባቸው ሰዎችጋ ዛሬ አንዱጋ ነገ አንዱጋ እያልኩ ማደር ጀመርኩ።
አጎቴጋም ጨክኖ ስለማይጨክንብኝ እሱጋም አንድ ወር ምናምን ተቀመጥኩ ግን ከዛ በላይ መቆየት አልቻልኩም ወጣትነት እድሜ ላይ ሆኖ የሰው እጅ እያዩ ለሰው ሸክም መሆን ያስጠላል።
ከሱጋ ደሞ ወጣሁና እመቤት ምትባል ልጆቿን ብቻዋን ምታሳድግ ትልቅ ሴትዮ ቤት ገባሁና እሷጋ መኖር ጀመርኩ።
እሷጋ መኖር ስጀምር በገጠር እህል ሸመታ ሚባል እሩቅ አገር እየሄድን ሁለት ቀን ሶስት ቀን ወይም አንድ ሳምንት ያህል እየቆየሁ መነገድና ገንዘብ ማግኘት ጀመርኩ ካገኘሁት ገንዘብ ላይ ግማሹን ለሴትዮዋ ግማሹን ለራሴ አደርገዋለሁ።
እናቴም ዘመዶቼም እንደቆሻሻ ከጣሉኝ አይቀር ዛሬ አምሮብኝ ማየት አለባቸው ብዬ አሰብኩና ከማንም በላይ መልበስ መዘነጥ ፀጉሬን ማሳደግ ሹርባ መሰራት ጀመርኩ ።
እያማረብኝ ሲሄድ ሰው የለበስኩትን ልብስ እንጂ የውስጤን አያይምና ሴቶች እኔ ላይ መሻፈድ ይጀምሯሉ ከሁለትም ሶስት ሴቶች ድንግልናቸውን እየሰጡኝ ሽማግሌ ልከህ አግባኝ ብለው ጠይቀውኝ ነበር።
ግን የአንዷም ቤተሰቦች እኔን አልተቀበሉኝም ልጃችንን በምን ሊያስተዳድራት ሊያኖራት ነው እያሉ ሽማግሌዎቹን መልሰውብኛል።
በቃ ህይወት ላይ ተስፋ ከመቁረጤ የተነሳ ባገኘሁበት ድግስ ቦታ መጨፈር መደሰት ብቻ ሆነ ሳምንቱን ሙሉ ለፍቼ ተንከራትቼ ያገኘሁትን ገንዘብ ለልብስና ለፀጉሬ ማዋል ጀመርኩ ከዛም ሲተርፈኝ ቴፕ የሚባል ሙዚቃ ማጫወቻ ነበር እሱን ገዛሁ በድሮ ጊዜ እሱን የያዘ ሰው በቃ የወጣት ዘናጭ ነበር በየድግስ ቦታ ቴፕ ያለው ሰው ይጠራል በቃ እሱን ጥሩት እሱ ያድምቅልን እንደተባለ ነበር።
ብቻ ሴትዮዋጋ ለተወሰነ አመታት ተቀመጥኩ ከጉዳቴ ጥቅሜ ስለሚያመዝንባት አታባርረኝም ነበር የለፋሁበትን ያገኘሁትን ገንዘብ ግማሹን ለሷ ስለሆነ ምሰጣት ልጆቿን ጭምር እኔ ነኝ ማስተዳድርላት ማለት እችላለሁ።
ታዲያ አብረን ስንነግድ የተግባባሁት ጓደኛ ነበረኝ ከሱጋ በጣም ሚስጠረኛም ጭምር ነን ማለት እችላለሁ ።
እጮኛ ነበረችው በጣም ነው ሚወዳት ለማግባት ይጓጓላታል እሷ ከቤተሰቦቿ ተደብቃ ልታገኘው ስትመጣ ቁጭ ብለው እስኪያወሩ ድረስ ሰው እንዳያያቸው እጠብቅላቸዋለሁ እሷን ሊያገኛት በሄደበት አጋጣሚ ሁሉ እኔ አለሁ።
የሆነ ቀን ላይ እኔና እሱ ተለያይተን ብቻዬን ለምኖርባት ሴትዮ ጨፈቃ የሚባል አጥር ማጠሪያ ላመጣላት ሄድኩኝ በዛ አጋጣሚ የጓደኛዬን እጮኛ አገኘኋት እንደሁል ጊዜው በደንብ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ልታወራኝ ምትፈልገው ጥብቅ ጉዳይ እንዳለ ትነግረኝና ቁጭ ብለን እናውራ ትለኛለች እሺ ብዬ ቁጭ አልኩኝ ምነው ምን አጋጠመሽ ብዬ ጠየኳት።
እኔኮ ለመናገር አፍሬ ነው እንጂ ከሱ ይልቅ አንተን ነው ምወደው ለምን አብረን አድረን አንተ አታገባኝም ብላ ጠየቀችኝ።
እየቀለደችም መስሎኝ ነበር
እሱኮ ወንድሜ ነው እሱ አንቺን ለማግባት ከዛሬ ነገ ሲጠብቅ እንዴት እኔ አገባሻለሁ ብዬ ጠየኳት።
እሷ ግን ምንም ሳታፍር በቃ ካላገባኸኝ ውሽማዬ ሁን አለችኝ ።
አንቺ አብደሻል እንዴ ብዬ ተነስቼ ወደ ጉዳዬ ሄድኩ።
በነጋታው ጎረቤት ሰርግ ነበርና እዛ ተጠርቼ ሄድኩ ጓደኛዬም እዛ ነበር ሁኔታው ከወትሮው ተለየብኝ አኳኋኑ ልክ አልነበረም ከመጠን በላይ እየጠጣ መሳሪያውን እያቀባበለ ወደኔ ያያል ምን ሆኖ ብዬ ግራ ተጋባሁ ።
ጨፍረን ጠጥተን አምሽተን እኔ ወደቤቴ ለመሄድ ወጣሁ ለካ እሱ ቀድሞ ወጥቶ እኔን ለመግደል እየጠበቀኝ ኖሯል።
እኔ አገር አማን ብዬ ያቺ ሞቅታዋም አለች
ቤቴጋ ለመድረስ የተወሰነ ሲቀረኝ ከተደበቀበት አጥር ውስጥ ወጥቶ በመጥረቢያ አናቴን አለኝ መሳሪያ ከተኮሰ ድምፅ እንዳይሰማ ነበር መጥረቢያ የተጠቀመው ።
የነዘረው ለአንገቴ ነበር ትረፊ ያላት ነፍስ ሆነችና እኔ ዝቅ ስል ጭንቅላቴ ላይ አረፈ ወይኔ ወንዱ ብዬ እዛው ተደፋሁ ሊደግመኝ ሲል ድምፅ ሲሰማ ጥሎኝ እሮጠ ለመነሳት ስሞክር የማይታሰብ ሆነብኝ
ከአንገቴ በላይ ያለሁ እራሱ አልመሰለኝም
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል 6️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet💔
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔