🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 9️⃣
እንደምንም ደፈር ብዬ ፊቷን ለማየት ሞከርኩ ግን አቃተኝ።
ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ የአጎቴ ሚስት ምሳና ትንሽ አጥሚት ትንሽ ገንፎ እህል ይዛላት መጣች።
ከዛን ቀን ቡሀላም አንዳንድ ሰዎች ድግስ ሲኖራቸው የማርያም አራስ እያሉ ምግብ እየላኩላት እሱን ትቀምሳለች።
አንዳንዴ ከሷጋ ቁጭ ብዬ በረሀብ አንጀቴ ሲታጠፍ ሳይ እኔ ወንዱ ልጅ እንደዚህ ያቃተኝ የልጅ እናቷ ባለቤቴስ እንዴት ትሆን ይሆን እረሀቡን እንዴት ቻለችው ለዛውም እያጠባች እልና ተነስቼ ቤተክርስቲያንን እሄድና አልቅሼ እመለሳለሁ ።
ብቻ በፈጣሪ ቸርነት ክርስትናው ሲቃረብ አጎቴ ክርስትናውን እኔ እደግስልሀለሁ አንተ ክርስትና አባት አዘጋጅ አለኝ በደስታ ብዛት አበድን ግን ክርስትና አባት ሚሆነን ሰው አልነበረንም እንደምንም አንደ ደገፉ የተባለ ሰውዬ እሺ አነሳልሀለሁ አለኝና ልጁን ለሱ ሰጠሁት ክርስትናው ተደገሰ የክርስትናው ቀን ልጁን ያየው ሰው ሁሉ ተገረመ ምነው አንዴ በሳምኩት ማለት ጀመሩ ቅላቱ ወደር አልነበረውም።
ከክርስትናው ቡሀላ እህል ሚሰበሰብበት ወቅት ደረሰ ተመስገን እንደሰው የራሳችንን እህል ዘርተን አጭደን ወቅተን ለመብላት በቃን ብለን ተደሰትን።
ያመርትነውን እህል ግማሹን አስቀምጠን ግማሹን ሸጥነውና በብሩ ጎጆ ቤት ሰራንበት ባለቤቴ ጉብዝናዋ ወደር አልነበረውም በገጠር ግርግይ የሚባል ነገር አለ በአዲስ አበባ እቃ መደርደሪያ ቡፌ እንደማለት ነው ቤታችንን በግርግይ ታስጌጠው ነበር ።
ቀስ በቀስስ ሰው ወደመሆን ጉዞ ጀመርን እሷም እንደሰው ልብስ መልበስ ከሰውጋ መግባባት ጀመረች ። እንደሰው ዘግተን ወጥተን ከፍተን ምንገባበት ቤት አገኘን።
ግን በዛ አልቆመም ነበር የኛ ስቃይ ድንገት ያባተበ ወንድም ተነሳና የያዝሽው መሬቱ የወንድሜ ነው ልቀቂ አላት እንግዲህ ጎዳና እያደረች በቀዳዳ ልብሷ ባልጠነከረ ጉልበቷ ተራራ እየወጣች ተካሳ ከናቷ ስትቀበል ዝም አሉና ልክ እሷ እህል አግኝታ ከመሬቱ መጠቀም ስትጀምር እሷን ከሰው መሬቷን ለመውሰድ መታገል ጀመሩ።
ይሄን ሁሉ የሚያደርጊት ለኔ ካላቸው ንቀት ነው ምክንያቱም በገጠር ወንድ ልጅ ሲከበር ሲፈራ አደለም ሚስቱን አደለም ልጆቹን የበሩን አጥር እንኳን ማንም አይነካበትም እኔን ግን አንዴ ፈሪ ነው ምንም አያረገንም ብለው ስላሰቡ እሷን ፍርድ ቤት ገተሯት ባለቤቴ የሴት ወንድ ስለሆነች ወገቧን አስራ በድጋሜ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት መንከራተት ጀመረች።
ከኛ ቤት ፍርድ ቤት እስክትደርስ በእግራ የሶስት ሰአት መንገድ እየተጓዘች ነው ምትካሰሰው ።
በዛ መሀል የሷ አጎት(የሚከሳት ሰውዬ) ከኔጋ በጣም ለመቀራረብ ሞከረ እንደጓደኛ ሲያወራኝ ሲያሳስቀኝ በፈገግታ ተቀበልኩት እንጠጣ ሲለኝ አብሬው መጠጣት ማምሸት ጀመርኩ።
ከባለቤቴጋ ተካሰው ተካሰው የመጨረሻ የፍርዱ ቀን እንደነገ ሆኖ እንደዛሬ ጠራኝና አብረን መሸታ ቤት አመሸን ባለቤትህኮ ለመካሰስ ሳይሆን ፍርድ ቤት ካሉ ከተሜዎችጋ ለመጋደም ነው ምትሄደው አሉኝ።
ሞኝነቴ መገለጫዬ ሳይሆን አልቀረምና ቤት ገብቼ ነገ እግርሽን ወደፍርድ ቤት ብታነሺ ሰባብሬ ነው ምጥልሽ አልኳት ዛትኩባት አስፈራራኋት አንድ ቀን እንኳን የፍርድ ቤቱ በር በየቱጋ እንደሆነ ሳላቀው አንድ ቀን እንደወንድ ልከተልሽ ሳልላት በ16 አመቷ የሴት ወንድ ሆና ልጅ እያዘለች በተንከራተተች በምላሹ እሷን መጠርጠር ጀመርኩ።
እሷ ግን ሞቼ እገኛለሁ እንጂ በፍርዱ ቀን አልቀርም አለችኝ።
እኔ ደሞ አስቲ ትሄጃለሽ ብዬ ዝቼባት ተኛን ።
ለካ እሷ ልቧ እንደተሰቀለ ነበርና ትንሽ እንቅልፍ ወስዷት ሸለብ እንዳደረጋት በዛው የነጋባት መስሏት እኔ ሳልነሳም ቶሎ ለመውጣት አስባ ልጄን ካጠገቤ አስተኝታው ከቤት ወጥታ ትሄዳለች።
በዛ በጨረቃ በሌሊት ለመድረስ እያለች በጥድፊያ እየተራመደች ቀስ በቀስ ከመንደሩ ትርቃለች ባጋጣሚ ከዳገቱ በታች የሚኖሩ ማለትም ወደ ተራራው መውጣት ከመጀመሯ በፊት ትንሽዬ መንደር ነበረችና እሷጋ ስትደርስ ምንም ድምፅ ታጣለች።
እየፈራችም ቢሆን ወደፊት መራመዷን አላቆመችም ነበር።
አጋጣሚ ሆኖ እሷ እየተራመደች ሁለት ሽፍቶች ከፊት ለፊቷ ይመጣሉ ።
መጀመሪያ ማን እንደሆነች አስኪያውቁ ድረስ መሳሪያ ያነጣጥሩባታል እኔ ነኝ እኔ እያለች ስሟን እየጠራች ስትጮህ መሳሪያቸውን አውርደው ወደሷ ይቀርቡና በዛ ሰአት እዛ ምን እያደረገች እንደሆነ ይጠይቋታል የፍርድ ቤት ክስ እንዳለባትና በጠዋት ለመድረስ እንደፈለገች ትነግራቸዋለች።
አንድኛው በጣም እየተቆጣና እየጮኸ ታዲያ እንዴት በዚህ ሰአት ትወጫለሽ ይሄኮ የጅብና የሽፍታ ሰአት ነው ገናኮ ማታ ነው ምንስ ሰአት ምታይበት ባይኖርሽ ዶሮ እስኪጮህ አጠብቂም ብሎ ይቆጣታል። የነጋ መስሎኝኮ ነው ትላቸዋለች።
ለማንኛውም ወደቤትሽ ተመልሰሽ ዶሮ ሲጮህ ውጭ አሁን ገና ከምሽቱ አምስት ሰአት አካባቢ ነው ጨረቃዋ እንዳትሸውድሽ ብለው እነሱ ወደቤተሰቦቻቸው ቤት ለመግባት ይሰናዳሉ።( ሽፍታ በቀን አይሄድም በሌሊት ነው ቤተሰቦቹንና ልጆቹን ጠይቆ ወደጫካ ሚመለሰው)።
እሷ ግን ወደቤት ከተመለሰች እኔ አትሄጂም ብዬ እንደማስቀራት ስለምታውቅ እዛው መንደር ውስጥ አንዱን አጥር ደገፍ ብላ ለመተኛት ታስብና ጥጓን ትይዛለች ጎዳና ለሷ ብርቋ አደለም አደል።
ከዛ ግን አንድኛው ለምን አንደፍራትም እኛ እንደሆንን አንዴ ሸፍተናል ማን ይናገረናል በራችን ድረስ የመጣችልን ሲሳይኮ ናት ለምን ታልፈናለች ይለዋል...
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል1️⃣0️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet💔
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔