🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ኢላሪ (እውነተኛ ታሪክ) ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ህሊና
ክፍል 1️⃣0️⃣
ወደ ዶርም ስገባ ሁሉም ቁጭ ብለዋል አብሬአቸው ቁጭ አልኩኝ።አንድ አንድ ተባብለን ተኛን።ስለ እዮባ ምንም አላልኩም።ጠዋት ተነስተን ካፌ ሄደን ቁርስ በላን ወደ 6 ሰዓት የአቤል አፍቃሪ ትዝ አለችኝ።ዛሬ አቤል ላገናኛት አሰብኩ ወዲያው ደወልኩላት።ከተመቻት ዛሬ ላስተዋውቃት እንዳሰብኩ ስነግራት ያለማቅማማት በሀሳቤ ተስማማች።ጉአደኞቼም ምን እንደሆነ ሲጠይቁኝ አሳጥሬ ነገርኳቸው።
ለአቤል ቀደም ቦዬ ደውዬ ጠራውት ሰባት ሰዓት ባለፈው እኔና ቤዛ ያወራንበት ቦታ ሄድን።እኔ ና አቤል ስንደርስ ቤዛ ቀድማን ደርሳ ነበር።አምሮባታል ልክ እንዳየችን ብድግ አለች።ሰላም አልኩዋት አቤልም ተዋወቃት።አስተናጋጇም ስትመጣ ስልክ እንደማናግር ሆኜ ወይኔ መጣው በቃ ብዬ አስተናጋጁአን እነሱን ታዘዢአቸው አልኳት።
ስማ አቤላ ሀኒን አሞታል መሄድ አለብኝ ቤዚዬ ይቅርታ እሺ እንደኔ ሆኖ አቤል ያጫውትሻል...እረ ኢላሪ አትጨነቂ አለችኝ።በቃ ሌላ ቀን እክሳችዋለው ብዬ ቤዚ ቻው ብዬ አቤላንም ቻው ልል ዝቅ ስል በጆሮዬ ...አንቺ አይጥ ቆይ ጠብቂኝ አለኝ ፈገግ ብዬ ቻው ብያቸው ወጣው።
የኔን ስራ ጨረስኩ ወደ ግቢ ስገባ ሀኒ ደወለች።....ወዬ ሀኒ...ኢሉ ትቆያለሽ እንዴ...እረ ጊቢ ደርሻለው ...በቃ እዛው ጠብቂኝ በሩ ጋር አለችኝ እሺ ብዬ ወደ አንድ ዛፍ ጋር ቆምኩ።ድንገት ግን ዳግም መጣ የኔ ቆንጆ ብሎ አጠገቤ ቆመ ዝም አልኩት።
...አንቺ እንዴት ነው ያማረብሽ አልዋሽሽም ትንሽ ቢዚ ሆኜ የሌለ ነበር የናፈቅሽኝ...ተው እንጂ...በእውነት የኔ ቆንጆ ...ባክህ ወደዛ ዞር በልልኝ....ቆይ አንቺ ልጅ በግድ ለምን እልህ ውስጥ እንድገባ ታደርጊኛለሽ....በአንድ ጥፊ እልህ ውስጥ ከገባክ የራስህ ጉዳይ።
ስሚኝ ሁለት ምርጫ አቅርቤልሻለው ከእኔ እኮ በአንድ ቀን አዳር መገላገል ትችያለሽ አካደበድሽው ስላስፈቀድኩሽ ነው እንዴ...ስላስፈቀድኩሽ ነው ማለት...ምን ማለት አለው በፍላጎትሽ አብረሽኝ እንድታድሪ ስለፈለኩ እንጂ ብሎ ዝም አለ...እንጂ ምን በሽተኛ ነክ ትሰማኛለክ ደግመክ አጠገቤ እንዳትደርስ ብዬው ልሄድ ስል እጄን ያዘኝና...ፍቅረኛዬም መሆን ትችያለሽ አለኝ።
ተናድቼ እንቼን ላስለቅቀው ስታገል ሀኒ መጣች።..አንተ ልቀቃት አለችው ሳቅ ብሎ ለቀቀኝ ...እሺ ሀና አላት የት እንደሚያውቃት አላውቅም ...ትሰማኛለክ ደግመህ እንዳትነካት እሺ አለችው ምንም ሳይል እየሳቀ ሄደ።
ከሀኒ ጋር ወተን አንድ ካፌ ገባን ሀኒ አይን አይኔን እያየች ...ቆይ ይሄ ጀዝባ እስካሁን አልፈታሽም ማለት ነው እንዳትደብቂኝ ስትለለኝ ያለውን ነገር ነገርኳት።ምንም እንደማያመጣ ነገረችኝ። እኔም የት እንደምታውቀው ጠየኩዋት በሆነ አጋጣሚ እንዳወቀችው ነገረችኝ እሺ ብዬ ዝም አልኩ።
..እና ሀኒ ምን አሰብሽ አልኳት ምኑን ...እህ ለዳን አትነግሪውም ....አላውቅም እሱን ላማክርሽ እኮ ነው ....እኔ የሱን ስሜት ተረጂና ንገሪው ነው ምልሽ እንዳይረፍድብሽ አልኳት።በውስጤም የራሴ እያረረ የሰው የማማስል እያልኩ።ከሀኒ ጋር ብዙ አወራን ለጊዜው ዝም እንድትል ተስማምተን ወደ ዶርም ሄድን።
ሰሞኑን ዳን ወጣ ያለ ባህሪ እያሳየን ነው።ይነጫነጫል በሆነው ባልሆነው ከሰው ጋር ይጣላል።መጠጥ በየቀኑ እየጠጣ ይሰክራል። ሁላችንም ግራ ተጋብተን አስቀምጠን ጠየቅነው ግን ትንሽ ከቤተሰብ ጋር ተጣልቶ እንደሆነ ነገረን ባይዋጥልንም ዝም አልን።
ዛሬ በጣም የሚያስጠላ ነገር ተፈጠረ።ቅዳሜ እና እሁድን ቤት ቆይቼ ሰኞ ወደ ጊቢ ተመለስኩ።ቶሎ ነው ሚናፍቁኝ ጉአደኞቼ።ዶርም ገብቼ ጉአደኞቼን ሰላም ብዬ ተኛው።የሆነ ሰዓት መቅዲ yes ብላ ስጮህ ተነሳው።ምንድ ነው አለቻት ማኪ መቅዲም...ዛሬ ዳን ማታ ፋአ እንላለን ብሏል አለች ...ውይ እኔ አልሄድም አልኳትና ተኛው...ወደሽ ነው ምትሄጅው አለችኝ።
መቅዲ መታ...አንቺ ተነሽ አለችኝ...ምንድ ነው መቅዲ...ታጠቢ ና እንሂድ ...የት ..ዳን ጋር ነዋ..አልሄድም አልኳት እንደምንም ጎትጉታ አሳምና አስነሳችኝ።ተጣጥቤ ጅንስ እና ጃኬት ለበስኩ።ቀይሪው ስትለኝ እምቢ አልኩ አልኳት።ማኪም ወደ እኔ እያየች በጣም ያምራል አለባበስሽ ቀለል ያለ አለችኝ😂 ሁላችንም ተያይዘን ወጣን።
እዮባ ልዑል ዳን እና ሌሎች 4 ልጆች ሱራፌል ሚኪ ናቲ እና አማን አብረዋቸው አሉ።ሁሉንም ሰላም ብለን ተያይዘን ወጣን።አንድ ቦታ እራት በላን።ዳንም በሉ ተነሱ አለን ወዴት ስንለው ዝም ብላቹ ኑብሎ አንድ ትልቅ ክለብ ወሰደን።ሁላችንም ክብ ሰርተን ተቀመጥን።
ጨለማ ነው ትንሽ ብርሀን ነው ያለው አስተናጋጇ መጣች እነ እዮባን እንደምታውቃቸው ከአነጋገሩዋ ያስታውቃል ስለዚህ ለነሱ ቦታው አዲስ አይደለም።መጠጥ ታዘዘ እኔ አልጠጣም ብዬ alcohol free የሆነ ነገር መጣልኝ።
የዳን ሁኔታ ግን ምንም አላማረኝም መጠጡን እንደጉድ ይጠጣዋል ገና ምሽቱ ከመጀመሩ እሱ ብዙ ከመጠጣቱ የተነሳ መስከር ጀምሯል።አንዴ ይጮሀል ይዘፍናል አንዴ ሴት ይዞ ይጨፍራል ሀኒ በዚህ ሰዓት እንባዋ ይመጣል።ድንገት ግን ዳን ከሰው ጋር ተጣላ። እዮባ እየጎተተ አወጣው።እኛም ሂሳብ ከፍለን አብረናቸው ወጣን።ዳን አሁን ላይ የሌለ ሰክሯል የሚናገረውን አያውቅም ዝም ብሎ ይዘላብዳል።
መሀል መንገድ ላይ ድንገት ለቅሶ የሚመስል ቃር እያወጣ እዮባን እያየ ...ወንድሜ እዮባ እኔን አትርዳኝ እኔ ከሀዲ ሰው ነኝ ርካሽ ነኝ ሲል እዮባ ክንዱን ይዞ ...ምንድን ነው ዳን ሲለው ..አትንካኝ እዮባ ተው እኔ እኮ ወራዳ ነኝ አንተ ጉአደኛዬን ከዳውክ ወንድሜ በእውነት እምልልካለው ይሄ እንዳይሆን ታገልኩ ግን አልቻልኩም ምንም እንዳልሆንኩ አስመሰልኩ አሁን ግን አልቻልኩም።
ዳን ምንድ ነው ንገረኝ አለው እዮባ...እውነት ታግያለው እዮባ ታግያለው ግን ኦሷ እሷ አሸነፈችኝ እዮባ እየታመምኩ ዝም አልኩ ሌሎች አጠገቤ እያሉ እሱዋን ተመኘው ወይኔ ዳን ታገልኩ ለራሴ እሷን ተዋት ተው ብዬ ነገርኩት ግን ውስጤ እሷን መተው ሞት መስሎ ተሰማው ግን እዮባ ላንተ እሞታለው።
እዮባ ጮክ ብሎ ...ዳን ምንድ ነው ንገረኝ ማናት ስለማን ነው ምታወራው አለው።ዳንም ...እዮባ አንተ ወንድሜ የምታፈቅራትን ሴት ልብህን የከፈትክላትን ሴት ሚስቴ እንድትሆን እፈልጋለው ያልከኝ ሴትን ተመኘዋት እዮባ ከኢላሪ ፍቅር ይዞኛል ካቅሜ በላይ ሆነብኝ።ጥፈተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ ልርቃት ብሞክርም አልቻልኩም ለመርሳት ስሞክር የባሰ እየወደድኩዋት መጣውኝ አሁን ግን ላብድ ነው አልችልም እዮባ አልችልም።
ይሄን ሲያወራ የማስበው ሁሉ ጠፋብኝ ያለማቋረጥ እንባዬ ይወርዳል።ዳንም እዮባ እግር ስር ወድቆ... ይቅር በለኝ እዮባ ፈልጌ ያመጣውት አንድም ነገር የለም ይቅር በለኝ እያለ እዮባን ይለምናል።ማንም ቃል አልተነፈሰም።ሳናስበው ሀኒ እራሷን ስታ ወደቀች።ሀኒ ብዬ ሄድኩኝ ሁሉም ደነገጡ።
ሀኒን ልዑል ከመሬት ተሸክሞ አነሳት።ካለንበት አቅራቢያ ሆስፒታል ስለነበር ወሰድናት።ሁሉም ግራ ተጋብቷል ዳን ስካሩ አለቀቀውም አሁንም ይለፈልፉል እዮባም ጮክ ብሎ ዳን ዝም በል አለው።