🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ኢላሪ (እውነተኛ ታሪክ) ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ህሊና
ክፍል 1️⃣5️⃣
ሚኪም ትኩር ብሎ ካየኝ በኃላ...እሺ ምንድ ነው የተፈጠረው ንገሪኝ አለኝ።እኔም ሁሉንም ልዑል ያለኝን ነገርኩት።...ይኸውልሽ ኢላሪ ሲል አቋርጬው..ሚኪ እዮባን አፈቅረዋለው የእውነት እወደዋለው...ታድያ ለምን እንዲ አደረግሽ የምትወጂው ከሆነ ሁሉንም መጋፈጥ ነበረብሽ...አላውቅም በቃ ልዑሌ እንደዛ ሲለኝ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ ምንም ማለት አቃተኝ እና ደግም ዳንንም ማጣት አልፈልግም።
ኢላሪ ጓደኝነት እና ፍቅርን አታወዳድሪ ኢላሪ እንዳይቆጭሽ...በቃ ሚኪ ስለዚህ አናውራ እሺ ብሎ ወሬ ቀይረን ስንስቅ ስንዝናና ዋልን።ማታ ላይ ወደ 2 ሰዓት አካባቢ ጊቢ በር ላይ አድርሶኝ ሄደ።ወደ ውስጥ እየገባው እያለ ሀኒ ደወለች።ጊቢ ውስጥ እንዳለው ነግሪያት እነሱ ወዳሉበት ካፌ መሄድ ጀመርኩ።
ድንገት ከሩቅ እዮባን እና ረድኤትን አየዋቸው። ቀረብ እያልኩ ስመጣ እሷም አየችኝ።ወዲያው ተንጠራርታ እዮባን አይኔ እያየ ከንፈሩን ሳመችው።ባለሁበት ፈዝዤ ቀረው ውስጤ እንደ እሳት ሲነድ ተሰማኝ።እዮባም ገፈተራት እኔ እንዳየውት ግን አላየኝም።እሱ ሳያየኝ ቶሎ ሄድኩኝ።የሆነ ሰው ከኃላዬ ጮክ ብሎ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አይደል አለኝ።እየወረደ የነበረውን እንባዬን ጠርጌ ዞር ስል ዳን ነው።
ደንግጬ ዳን አልኩት...ኢላሪ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አለኝ...ማለት ስለው አቋረጠኝ ንዴት እና ቁጣ በተቀላቀለበት ንግግር...ኢላሪ በእናትሽ ንገሪኝ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አለኝ አይኖቹ እንባ አቅረዋል ደነገጥኩኝ ምንም ሳልመልስለት አልፌው ሄድኩኝ።
ተከትሎኝ መጣ እና አስቆመኝ....እባክሽ ንገሪኝ አትሽሺ ሲለኝ እንባው ጠብ አለ።አቀፍኩት እሱም አጥብቆ አቀፈኝአንዳንዴ የምናፈቅረውን ላለማጣት እየጣርን የምናስብለት ሰውም እንዳይጎዳ መሞከር በጣም ከባድ ነው።ከኃላ ኢላሪ ተባልኩ ዞር ስል እዮባ ከረድኤት ጋር ቆመዋል።ዳንን ለቀቀኩት እዮባም ...ኢላሪ ለምን ንገሪኝ ለምን አልወድህም ዳንን ነው ምፈልገው ምርጫዬ አይደለክም ብትይ እኮ አልቃወምሽም አላስቸግርሽም ነበር ለምን በድብቅ ምንም ቢሆን ዳን ወንድሜ ነው በመሀላችሁ አልገባም ነበር ለሁሉም ነገር አመሰግናለው ብሎ ጥሎን ሄደ። ዳን ምንም ቃል አልተነፈሰም።እኔም እዮባን እየሮጥኩ ተከተልኩት።
እዮባን እየሮጥኩ ተከተልኩት እዮባ ብዬ ጠራውት ...አቤት ምንድነው ምትፈልጊው ...እዮባ አዳምጠኝ ተረጋጋ እና ልንገርህ...ኢላሪ እስከዛሬ ስሰቃይ ዝምታሽ ሲገለኝ የት ነበርሽ እእ ንገሪኝ ዳን ነው ምወደው ብለሽ ብትነግሪኝ እኮ አላስቸግርሽም ዳን ወንድሜ ነው አንቺ ፈልገሽ ከሆነ ቢያሳምመኝም እችለው ነበር።ለምን ዝም አልሽ እ አላሪ አንቺ እኮ ህልሜ ምኞቴ የወደፊት ሚስቴ እንድትሆኝ የምመኝሽ ሴት ነበርሽ።አዎ ከብዙ ሴት ጋር ብዙ ነገር አድርጌ ሊሆን ይችላል።
ለብዙ ሴት እንባ መፍሰስ ተጠያቂም ልሆን እችላለው።ግን አንቺን ኢላሪ አንቺን የእውነት አፈቀርኩሽ።ኢላሪ አንዳንዴ ቁጡነትሽን ሳይ እፈራለው ዙሪያሽን ሳይ እሰጋለው የኔ ላትሆን ብዬ አንቺን ለመርሳት ወይም በፍቅርሽ እንደተሸነፍኩ ላለማመን ከብዙ ሴት ጋር የፈለኩትን አደረኩኝ ግን ጭራሽ አልሆነልኝም።እያንዳንዱን ነገር እያደረኩ ትዝ ትይኛለሽ።
ማፍቀሬ ጥፋት ከሆነ የፈለግሽውን አድርጊ ግን ዝም አትበይኝ ብዬሽ ነበር። አሁን ምን አለ ብለሽ ነው ምታወሪው... እዮባ እባክህ አቋረጠኝና...አንቺ የምታውቂኝ እዚ ነዋ እዚ ግቢ እኔ ግን አይደለም።...ማለት እዮባ...ኢላሪ ትዝ ይላሻል መጀመሪያ አካባቢ በእኛ ምርጫ እራት ልንጋብዛቸው ብለን የወሰድኳቹ ቦታ እሱም ያንቺ ምርጫ ነበር።እንደምትወጂውም የገባኝ የእናተ የማትሪክ ውጤት የወጣ ቀን ይመስለኛል።ከቤተሰቦችሽ ጋር እዛው ቦታ ነበራችሁ እኔም ከአንዷ ጋር ነበርኩ።ድንገት ግን ተጋጨን አየውሽ።
ወደድኩሽ ላናግርሽ ብዬ ምን ብዬ እንደማወራ ግራ ገባኝ።እዮባ እየነገረኝ እኔ ሁሌ እዮባን የሆነ ቦታ እንዳየውት ይሰማኝ ለዚህ እንደነበሮ ገባኝ አለማስታወሰ እየገረመኝ ማዳመጤን ቀጠልኩ።ኢላሪ አናንተ እስክጨርሱ ጠብቄ ልጅቷን ትቼ ቤታችሁን ተከትዬ አየውት።አልዋሽሽም ቢያንስ በሳምንት ሶስቴ ድንገት ካየውሽ በሚል መጥቼ በራችሁ አካባቢ እቆማለው።እሚገርመው ግን እዚው አገኘውሽ።
መጀመሪያ የተዋወኩሽ ቀን ፈጣሪዬን እንዴት እንዳመሰገኩ።የልቤን አይተህ አመጣሀት ብዬ ደስ አለኝ ግን ሁሉም ከንቱ ነው የኔ ላትሆኝ ነገር መደሰቴ።ኢላሪ ተይ በቃ አታሰቃይኝ ብሎ ጥሎኝ ሄደ።
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል 1️⃣6️⃣ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔