🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ኢላሪ (እውነተኛ ታሪክ) ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ህሊና
ክፍል 1️⃣7️⃣
ከፍታልኝ ወደ ውስጥ ስገባ እዮባ አልጋው ላይ በጀርባው ተኝቷል።አጠገቡ ሄጄ ቁጭ አልኩ ዝም ብዬ መመልከት ጀመርኩ።ድንገት ግን እዮባ ነቃ ኢላሪ አለኝ..እዮባ ደህና ነህ ....እዚ ምን ታደርጊያለሽ ኢላሪ ...ምነው ልሂድ ስለው ዝም አለኝ እሺ በቃ ብዬ ብድግ ስል እጄን ያዘኝ አትሂጂ አለኝ።እሺ ብዬ ቁጭ አልኩ።...ኢላሪ አንዴ ሻወር ልውሰድ እና እናወራለን ብሎ ወደ መታጠብያ ቤት ገባ።እኔም ተነስቼ ክፍሉን ማስተካከል ጀመርኩ።የመጠጥ ጠርሙስ ሰብስቤ ለሰራተኛዋ ሰጠሁዋት ለእዮባም የሚበላ ነገር ይዛለት እንድትመጣ ነግሪያት ቁጭ አልኩኝ።ታጥቦ ጨርሶ መጣ።ፎጣ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመ ከላይ ግን ቲሸርት አልበሰም ነበር።የደረቱ ስፉት ደስ ሲል ብቻ የስፓርተኛ ሰውነት ነው ያለው።ከፈዘዝኩበት ደንገጥ ብዬ ፊቴን አዞርኩ እስኪለብስ ብዬ የተሰራለትን ላመጣ ወረድኩ።
ምግቡን ይዤ ወደ እዮባ ተመለስኩ።አጠገቡ ቁጭ አልኩኝ።ምግቡንም እንዲበላ ሰጠውት በልቶ ሲጨርስ የበላበትን አስቀምጦ በረንዳ ላይ እንሁን አለኝ።እሺ ብዬ በክፍሉ በኩል ያለው በረንዳ ላይ ወተን ቁጭ አልን።ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን።አይን አይኑን እያየው...እዮባ ለምን እንዲ ትሆናለህ ባንተ እንዲ መሆን አጠገብክ ያሉትን የሚጨነቁልክ ሰዎችን እየጎዳክ ነው።ደግሞ ለመመረቅ አንድ አመት ነው የቀረክ እባክህ እዮባ እንዲ አትሁን።...ታውቂያለሽ ኢላሪ እኔ ማለት እኮ ከሴት እንዳልተፈጠርኩ የሴት እንባ እና ህመም ደንታ ማይሰጠኝ ለእኔ ስሜት እንጂ ለእነሱ ቅንጣት ታክል የማልጨነቅ እዮብ ነበርኩ።ለዛም አሁን ዋጋ እየከፈልኩ ነው።አንዳንድ ሴቶች እኮ አሉ ምንም ለራሳቸው ክብር የሌላቸው።አሉ ደግሞ የተመረጡ ግን ዞሮ ዞሮ ሴት ፍቅር ሲይዛት የማትፈልገውን ማንነት ትላበሳለች።ኢላሪ የእውነት እያፈቀረችኝ እኔ ግን ለስሜቴ ስል ብቻ እቀርባታለው ያቺም ሴት እኔን ላለማጣት የምፈልገውን ታደርጋለች።ብቻ ለእነዚህ ሴቶች እንባ መፍሰስ ፍቅር በደንብ አድርጎ እየቀጣኝ ነው።
የእነሱን ስሜት ስረዳው ራሴን ጠላውት።ኢላሪ አንቺ በደንብ አድርገሽ እያስከፈልሽኝ ነው።በአንድ ቀን እይታ ጭንቅላቴ ውስጥ የነበሩትን የሴቶች መአት በአንዴ ደረመሽው።ወንድ ልጅ አያፍቅር ነው ነገሩ ብሎ ፈገግ አለ።...እዮባ በቃ ልሂድ ብዬ ተነሳው...ምነው አትቆይም...አይ እዮባ ይመሻል ...እሺ በቃ ነይ ላድርስሽ ብሎ ከቤት የአባቱን መኪና ይዞ መሄድ ጀመርን።በመሀልም...እኔ ምልሽ ኢላሪ አለኝ..አቤት...ዳንን አግኝተሽው ወይም አውርተሽው ታውቂያለሽ አለኝ።...አው እዮባ ዛሬ አጊኝቼው ነበር አልኩት ምንም ሳይመልስልኝ ዝም አለ።ቤት አደረሰኝና ተሰናብቼው ተመለሰ።
አሁን ላይ ጊቢ ተመልሰናል ጊቢ ከተመለስን ቀን ጀምሮ ዳግም አላስቀምጥ ብሎኛል።አንዴ እራት ልጋብዝሽ አንዴ ተገናኝተን እናውራ የማይለው የለም።እኔ ደግሞ ዳግምን ፈጥሮብኝ እንዲው አላምነውም ቀልቤ አይወደውም።ዛሬ ካፌ ተሰብስበን እራት በላን።በትንሹም ቢሆን ጉአደኝነታችን ተመልሷል።እራት ጨርሰን ወክ ማድረግ ጀመርን።ድንገት ግን በመንገዳችን አንድ ልጅ ትጮሀለች።ሀኒም ... ይመስለኛል ከፍቅረኛዋ ጋር እየተጣላችነው አለችን።በዛው ስናልፍ ቀረብ ማለት ጀመርን።አንዲት ከአንድ ወንድ ጋር ቆማ እያወራች ነው ማለትም እየተጨቃጨቀች ነገር።እኛም ዳራችንን ይዘን እየሄድን ልጆቹ አጠገብ ደረስን።ቤዛ እና አቤል ናቸው።አኔ እንዳየዋቸው እነሱም አዩን።
እኔም ዝም ብዬ አለፍኩ።ድንገት ግን ቤዛ ...ቆይ ኢላሪያ አለችኝ።ሁላችንም ዞር ብለን ቆምን።አቤት አልኳት ቀጥታ አጠገቤ መታ በጥፊ ደረገመችኝ😒።ጉአደኞቼም አንቺ ብለው ሊደረግሙአት ሲሉ አስቆምኳቸው።አቤልም አጠገባችን መቶ...አንቺ ያምሻል እንዴ አላት።እሷም እምባ እየተናነቃት ...አዎ ያመኛል ምን አጠፋሽ ልትለኝ ነው ንገረኝ ምን አልባት እሷ ቤትኖር እኮ ታፈቅረኝ ነበር።በጣም አናዳኝ...ምንድ ነው ምታወሪው ምን እየሆንሽ ነው ስላት እየጮህች...ዝም በይ አንቺ የምትረጁኝ መስሎኝ ስሜቴን ነገርኩሽ አቤልን የኔ እንድታደርጊልኝ ነበር።
አንቺ ግን በጣም ነው ምታስጠይው ወንዶችን እንዴት በፍቅርሽ መጣል እንዳለብሽ ታውቂያለሽ።በሁለት ጉአደኛሞች መሀል ስትገቢ ነበር መጠርጠር የነበረብኝ። በጭራሽ አቤልን አልሰጥሽም እሺ አለችኝ።ድንገት ግን ሀኒ መታ በጥፊ ደረገመቻት።ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ።ሀኒም ትሰሚያለሽ አለቻት...ለመፈቀር እኮ ንፁህ ልብ ያስፈልጋል አንቺ ደግሞ እንደማየው እሱ የለሽም እንዴት እንዳፈቀርሽም ፈጣሪ ይወቀው አለቻት።አቤልም ነይ ብሎ ይዞት ሄደ።
ልክ አቤል እና ቤዛ እንደሄዱ ሁሉም ወደ እኔ አፈጠጡ።...ምን ሆናችሁ ነው እንዲ ምታዩኝ መቅዲ ቀደም ብላ...እንድታስረጅን ነዋ ...እህ ምኑን ላስረዳችሁ ቤቲም እየሳቀች...አሁን የተፈጠረው ነዋ ቆይ ከአቤል ጋር የማናውቀው ግንኙነት አላችሁ እንዴ አለችኝ...እረ ምን ሆናችሁ ነው እንደዚህ አይነት ነገር የለም።ግን እኔም ቤዛ እንዲህ የሆነችበት ምክንያት አልገባኝም አልኳቸው ወንዶቹ ቃል አልተነፈሱም ብቻ ሁሉም ሀሳቤ ባይዋጥላቸውም ዝም አሉ።
ሰሞኑን ደህና ነኝ አያቴ ትዝ ብትለኝም ጠንክርያለው።አሁን ላይ ፈተና ላይ ስለሆንን ውጥረት ላይ ነን።እንደምንም ብለን ፈተናችንንም ጨረስን።ማታ ካፌ እራት እየበላን።ስለ ሶስቱ ምርቃትም እያወራን ማለትም እዮብ ዳን ልዑሌ በአሁኑ ይመረቃሉ።ሁላችንም በጉጉት ልንሞት ነው።ግን ይሄ ጊቢ ያለነሱ ለእኛ ደባሪ ነው።አቤልም ይመረቃል ትተውን ሊወጡ ነው።በወሬ መሀልም ሰሞኑን ለምን የሆነ ቦታ ሄደን አንዝናናም ተባለ።ሁሉም ተስማሙ።ዳንም ....እርሶስ እማማ አለኝ...እስማማለው አባባ አልኩት።
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል 1️⃣8️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔