🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 4️⃣
ቆሜ ማወራው ነገር ግራ እንደገባኝ አለቃዬ መጣና በቃ እንሂድ አሪፍ ነው የሰራነው ዛሬ መኪናው እኔጋ ይደር በዛውም ልሸኝል አለኝ።
እሺ ብዬ ትቻት ልገባ ስል አሳዘነችኝና የት ነው ቤትሽ እንሸኝሽ አልኳት።
ነገረችን እኔም እሷም ከኋላ ገባን ንዴቴ ስላልበረደልኝ እየደጋገምኩ ድጋሜ እዚህ ቆመሽ እንዳታመሽ ሰፈሩ እንኳን ለሴት ለወንድ ያስፈራል አልኳት።
እንደዛ ከሆነ ስልኬን ከብሎክ አውጣው አልጨቀጭቅህም አላስቸግርህም አንዳንዴ ብቻ ድምፅህን እንድሰማው ነው ብላ ስትለምነኝ እሺ ብዬ ስልኳን ከብሎክ አወጣሁት በዛውም ሰፈሯ ደርሰን ስለነበር ተሰናብታኝ ከመኪናው ወረደች።
እሷ ከወረደች ቡሀላ አለቃዬ እየሳቀ አይ ይች አለም በቃ ፍትሀዊ አደለችማ።
አንተ ሴት አትቀርብ ሴት አጠገብህ ቆማ እራሱ አታስታውላትም ሴቶች ግን አንተን ነው ሚከተሉት ምነው ላንተ ከሚያሽቃብጡ እኛንም ቢመለከቱን አለና ተሳሳቅን።
ሰፈር አድርሶኝ በዛውም እናቴን ገብቶ ሰላም ብሏት ሄደ ደክሞኝ ስለነበር ቶሎ ነበር የተኛሁት።
ጠዋት እንደተለመደው እናቴ ቀስቅሳኝ አርፍጄም ቢሆን ወደስራዬ ሄድኩ ።
ቀኑን ሙሉ ስራ ባይኖርም ውስጥ ቁጭ ብለን ነበር የዋልነው ማታ ላይ ከስራ ስወጣ ልጅቷ መንገድ ላይ እንደምጠብቀኝ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን የለችም የሆነ እቃ እንደረሳ ሰው ቅር ቅር አለኝ።
ቤት እንደገባሁ ዛሬኮ ታምሜ ነው ላይህ ያልመጣሁት ይላል መመለስ ስላልፈለኩ ዝም ብያት ተኛሁ።
እንዲሁ ፊልም እንደሰራችብኝ ድጋሜ ሌላ ሳምንታቶች ተቆጠሩ እኔም ልክ ከስራ ስወጣ የሆነ ነገር እንደሚጠብቀኝ ነገር ልቤ ስቅል ይላል ግን ደሞ ስልክ መደወል text መመለስ ወይ ስትደውልልኝ ማንሳት አልፈልግም።
ድንገት ግን ምን እንደተፈጠረ ሳላቅ ለአስራአምስት ቀን ያህል ጠፋች በየቀኑ እንደምትመጣ ተስፋ እያደረኩ ከስራ እወጣለሁ ግን የለችም ከዛሬ ነገ ትደውላለች ብዬ ጠበኩ እሷ በፍፁም መልእክት እራሱ ሳትልክልኝ ስለቆየች ድንገት የሆነ ነገር ተፈጥሮባት ቢሆንስ ብቻ መጨነቅ ጀመርኩ መሰለኝ ለእናቴ ነገርኳት ምነው አንተ በዚህ ልክ ይጨከናል እንዴ የሆነ ነገር ሆና ቢሆንስ ታማም ሊሆን ይችላል ባትወዳት እንኳን ድንገት ምታቀው ሰው እንደዚህ ቢሆን ያስችልሀል በል ደውልላት ብላ ተቆጣችኝ።
እኔ ግን መደወሉ ሞት መስሎ ታየኝ አልደውልም ብዬ ከተውኩት ቡሀላ የእናቴ ውትወታ አላስቀምጥ ሲለኝ ስልኬን አንስቼ መልእክት ላኩላት
በሰላም ነው የጠፋሽው የሆንሽው ነገር አለ እንዴ ?ብዬ ላኩላት
ፅፌ መጨረሴንና መላኬን እርግጠኛ ባልሆንኩበት ቅፅበት አዎ ደናነኝ ብላ መለሰች።
ዝም አልኳት።
ቀጠለችና መልእክት በድምፅ መላክ ቢቻል ምን ያህል ደስ እንዳለኝና መልእክቱን ሳየው እንዴት እንደጮኩ ብታይ ደስ ይለኝ ነበሮ አለች።
በድጋሜ አይቼው ዝም አልኩ።
ድጋሜ ሌላ መልእክት።
አለመኖሬን ማስተዋልህ ገርሞኛል እኔኮ ማታ ማታ እዛ ስቆም ብርድ መቶኝ ታምሜ ተኝቼ ነበሮ ከስራም ተባረርኩ ታምሜ ብዙ ቀን በመቅረቴ አባረሩኝ።
በጣም ከፍቶኝ ነበር መልእክትህን ሳየው ልቤ እንዴት እንደመታ
ይላል።
መልእክት ተከታታይ ስትልክ ደበረኝና ደና ደሪ ብዬ ላኩላት።
ደና ደር ከቻልክ ነገ ስራ ከሌለህ እንገናኝ እኔ ማታ መጥቼ እንዳልጠብቅህ ድጋሜ በሽታዬ ይነሳብኛል አለችኝ።
ሲመቸኝ አሳውቅሻለሁ በቃ ድጋሜ መልእክት እንዳትልኪልኝ ብዬ ላኩላት።
በዛው አመረረችና ለሳምንት ያህል ዝም ስትለኝ ድጋሜ በኔ ምክንያት ታማ ይሆን እንዴ ብዬ ሲጨንቀኝ ነገ ቅዳሜ ስለሆነ ከሰአት ስራ አንገባም ከሰአት ላግኝሽ ብዬ መልእክት ላኩላት እሺ ስንት ሰአት አለችኝ 8 ሰአት ብዬ መለስኩላት።
በነጋታው 6.30 ሲል ስራ ቦታህጋ መጥቻለሁ እስክትወጣ እየጠበኩህ ነው ብላ ላከችልኝ።
ስምንስት ሰአት እንደተቀጣጠርንና አሁን ለምን እንደመጣች ጠየኳት።
አይ የምር ልታገኘኝ መሆኑን ስላላመንኩ እዚህ ተቀምጬ ልጠብቅህ ብዬኮ ነው ሀሰብ እንዳትቀይር ፈራሁ ችግር የለም እስከ ስምንት ሰአት እጠብቅሀለሁ ብላ መለሰችልኝ።
ሳቄ መጣ ያማታል እንዴ ይቺ ደሞ ከሁሉም የባሰች ናት ብዬ ከራሴጋ አወራሁና ልብሴን ቀያይሬ ተጣጥቤ ወጣሁ እዛው ቅርብ የነበረ ቤት ይዣት ሄድኩ ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ተቀመጥን አይን አይኔን ስታየኝ እኔም ትኩር ብዬ አየኋት።
በጣም ቆንጆ ናት ድርብ ጥርስም አላት ፀጉሯም የራሷ ነው በዛ ላይ በጣም እረጅም ነው በውስጤ እሷን እያደናነኩ ለማውራት ግን ጅንን አልኩባት።
በዛ መሀል አስተናጋጇ መጥታ ምን ልታዘዝ አለችኝ እኔ ምንም አልፈልግም አልኳት እሷ ግን አረ ምሳኮ አልበላሁም አትበላም እንዴ አለችኝ
ውጭ ምግብ በልቼ እንደማላቅ ነገርኳት እሺ በቃ እኔም አልበላም አመሰግናለሁ አለች።
ያምሻል እንዴ አሁን ምሳ አልበላሁም አላልሽም መልሰሽ አልበላም ማለት ምን ማለት ነው አልኳት።
አይ እኔኮ አብረን እንበላለን ብዬ አስቤ ስለመጣሁ ነው አሁን ግን በቃኝ አልበላም አለች።
ለማንኛውም ፈጣሪ ያመመሽን ህመም ያርቅልሽ ደና መሆንሽን ለማወቅ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ በኔ ምክንያት የታመመሽ መስሎኝ ጥሩ ስሜት ስላልተሰማኝ ነው ደና ከሆንሽ ደና ሁኚ በቃ ድጋሜ እንዳትደውይ እኔም መልእክት አልክልሽም በዚህ ሰአት ስራዬ ላይ ማተኮር ነው ምፈልገው አንቺ ደሞ ነፃነቴን እያሳጣሽኝ ነው ብያት በተቀመጠችበት ጥያት ወጣሁ።
አልተከተለችኝም መኪና ውስጥ እየሄድኹ ግን ከራሴጋ ክርክር ጀመርኩ አንዱ ልቤ ደግ አደረክ ይለኛል ሌላኛው ልቤ ደሞ ልክ አላደረክም ወንድ የሆንክ መስሎህ ነው ይለኛል
ይቀጥላል...
🔻ክፍል 5️⃣ ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔