አንድ አጭር የፍቅር ታሪክ ልጋብዛቹ!!
በአንድ ወቅት ሁለት እጅግ የሚዋደዱ ፍቅረኛማቾች ነበሩ፡፡ በፍቅራቸው ሙሉ አካባቢው ይቀናባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ግን በአንድ ሆቴል ልጆቷ በድንገት ከሌላ ወንድ ጋር ትታያለች፡፡
በዚህ ሰአት የሆነ ሰው ደውሎ "ና የፍቅረኛህን ቅሌት ተመልከት" ብሎ ይነግረዋል፡፡
ልጁም ካለበት በፍጥነት ሲመጣ ክፍል ይዘው
ገብተዋል፡፡ ገቡ ወደ ተባለበት ክፍል ቀርቦ ሲያዳምጥ ከውስጥ ይሳሳቃሉ።
እስከመጨረሻው የመታገስ አቅም አልነበረውም፡፡ በኔ ላይ ሌላ ወንድ ? ሲል ይናደዳል ፡፡ በዚህ ግዜ የሷ ጉዋደኛ የሆነች ልታፅናናው ትቀርበዋለች፡
እሱም አጋጣሚውን በመጠቀም እንደውም ላስቀናት በሚል እሷ በምታየው ቦታ ጓደኛዋን እየወሰደ ያዝናናታል እንደፍቅረኛ አድርጎ ለሰው ያወራል፡፡
ከ ወር ቡሀላ ፍቅረኛው ሞተች፡፡ በዚህ ግዜ በእናቷ በኩል አንድ ደብዳቤ አስቀምጣለት ነበር፡፡ እሱ የኔ ግፍ ነው ብሎ በቀብር ስርአቱ ላይ እንኳን አልተገኘም፡፡ እናትየዋ ባለበት ሄዳ የልጇ አደራ የሆነውን ደብዳቤውን ሰጠችው፡፡ ደብዳቤው ይህን ይላል፡፡
"ውዴ የኔ ፍቅር አንተ አዝነክብኛል እኔ ግንተደስቻለው፡፡ ያን ቀን ሆቴል ደውዬ እንድትመጣ ያደረኩት እኔ ነኝ፡፡ በዛ ክፍል ውስጥ ምንም አልተፈጠረም፡፡
አንተ በኔ ተናደክ ወደሌላ ሴት እንድትሄድ የሰራውት ድራማ ነበር፡፡ በሀዘንህ ሰአት ያፅናናችክ ጉዋደኛዬ እኔ ነኝ የላኳት፡፡ እሷ በጣም ትወድካለች ፡፡
እንዳትተዋት፡፡ አንተ እኔን ለማስቀናት ፍቅር ስትሰጣት ሳይ እኔ እደሰት ነበር፡፡ ያንን ፍቅር ከልብህ አድርገው፡፡ ደስታህን አይቼ
በመሞቴ እድለኛ ነኝ፡፡ ቢያንስ ብቻክን አልተውኩህም፡፡ ይሄንን ያደረኩት ዶክተሩ ባለብኝ ካንሰር ምክንያት ለመሞት ቢበዛ 30ቀን እንደቀረኝ ስለነገረኝ ነው፡፡"
"ፍቅር ማለት አብረው ላሉት ብቻ ሳይሆን ትተውት ለሚሄዱትም ደስታ መጨነቅ ነው፡፡"