🩶 ቁርኣን 🩶
ቁርኣን የሰው ልጆች መመርያ ይሆን ዘንድ ከጌታቸው የወረደ የህይወት መንገድ ነው::
▪ቁርኣን ህግ ነው::
▪ቁርኣን መንገድ ነው::
▪ቁርኣን መታከሚያ ፈውስ ነው::
▪ቁርኣን መመለሻ ነው::
▪ቁርኣን መታረቂያ ነው::
▪ቁርኣን መንገድ የሳተን መላሽ ነው::
▪ቁርኣን ፈራጅ ነው::
▪ቁርኣን መደሰቻ ነው::
▪ቁርኣን መሸሻ ነው::
▪ቁርኣን ቀን ሲከፋ መደበቂያ ነው::
📍ቁርኣንን የያዙ ሰዎች አይጠሙም:: በርሱ የተፋረዱ አይቆጩም :: እሱን በመሃከላቸው ያረጉ ህዝቦች መቼም ቢሆን መንገድ አይስቱም::
« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ :: መልእክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ ( የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው:: » አል-ቁርኣን 4:59
ያጨቃጨቀንና ለንትርክ የዳረገንን ጉዳይ ወደ ቁርኣን እና ወደ ረሱሉ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፈለግ እንመልሰው ዘንድ ያዘዘን አላህ ነው:: ወደዛ የመለስነው እንደሆነ መጨረሻው ያማረ እንደሆነ ቃል የገባልን እርሱ ነው::
« ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደኾነችው መንገድ ይመራል:: እነዚያንም በጎ የሚሰሩትን ምእመናን ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል » ኣል-ቁርኣን 17:9
በጎ መስራት በቁርኣን ከመመራት ጋ የተጣመረ መሆኑን ከዚህ አንቀፅ እንማራለን :: ቁርኣን ውስጥ የተተወ ነገር እንዳለመኖሩ ለየትኛውም ጉዳያችን መፍትሄ ፈልገን አናጣበትም ::
«በዚያም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለፅን:: » 30:58
«ህዝቦቼ ቁርኣንን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት» እንዳለው መልእክተኛው እንዳንሆን መጠንቀቅ ያሻል ::
« አላህ በዚ መፅሃፍ(በቁርኣን) ከፊል ህዝቦችን ከፍ ሲያደርግ ከፊሎችን ደሞ ዝቅ(የበታች) ያደርጋል » ሰሂህ ሙስሊም
ከፍ ማለት በቁርኣን በመመራት ቢሆን እንጂ አይገኝም :: በርሱ ባለመስራትና በመሸሽ ደሞ ውርደት ይከተላልና የስልጣኔ ማማን መጎናፀፍ ብሎም ስኬትን የሻን እንደሆን ቁርኣንን አጥብቀን እንያዝ:: አላህ ይመልሰን ያግራልንም::
☘ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
https://t.me/furqan_school