የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


⛪️1ኛ ቆሮንቶስ 6÷2፤ቅዱሳን፡በዓለም፡ላይ፡እንዲፈርዱ፡አታውቁምን፧በዓለምስ፡ላይ፡ብትፈርዱ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ትንሽ፡
ስለሚኾን፡ነገር፡ልትፈርዱ፡አትበቁምን፧
@Brkeyazew
@Brkeyazew
https://t.me/yekidusantarikachewhiywetachew

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций






የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው ነፍስንም ይመለሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ሕጻናትንም ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፤ልብን ደስ ያሰኛል ።የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ አይኖችንም ያበራል ::እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው ለዘለዓለም ያኖራል የእግዚአብሔር ፍርድ እውነት እና ቅንነት በአንድነት ነው ::ከወርቅ እና ከክቡር እንቁ ይልቅ ይወደዳል ፤ከማርና ከማር ወለላም ይልቅ ይጣፍጣል:: ባርያህ ደግሞ ይጠብቀዋል በመጠበቁም ብዙ ዋጋ ይቀበላል ::

(መዝሙር ፲፰፥፯-፲፩)




Репост из: በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)
የየትኛውም ብሔር ተወላጅ ብትኾን መጀመሪያ በራስህ፤ ቀጥሎ በቤተሰብህ፤ ከዚያም በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ እና በመጨረሻም በሀገር ላይ ይመጣ ያለውን አስከፊ እልቂትና መከራ ሳይታክቱ ሌት ተቀን ነግረውሃልና እነዚኽ ኹለት ሰዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለ ዕዳዎች ናቸው። ግለሰቦቹን ወደድካቸውም ጠላኻቸውም፤ ሰማኻቸውም አልሰማኻቸውም እርሱ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ነቢይም ሐዋርያም መምህርም ኾነው ትናንትም ዛሬም ሲጮኹ አይተንና ሰምተን እንደ እብድ ብንቈጥራቸውም ነገ ጅብ ከሔደ በኋላ የውሻ ጩኸት የምንጮኸው እኛ ነን። ይኽ በእርግጥ ሩቅ አይደለም። የዐዋጅ ነጋሪ ቃል ሲጮህ አልሰማ ብለህ ለንስሓ ያልተዘጋጀህ ኹላ አይዞህ ጊዜው ሩቅ አይደለም። አራጁ ቢላውን ስሎ ሞርዶ ከደጅ ቆሞልሃል፤ አንተም አንገትህን አደንድነህ ጠብቀው።


"" ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው! "" (መዝ. ፻፲፭:፪)

☞ክፍል ፩/1

"ዝክረ ቅዱስ ዳዊት - ዘወርኀ ጥር"

(ጥር 23 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn




ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ

“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)


"" ስንክሳር - ጥር ፳፭/25 ""

❖በዓለ ቅዱሳን መርቆሬዎስ ፥ ወስብስትያኖስ፥ ወጴጥሮስ

(ጥር 24 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


ሰላም ለአፃብዒከ

ቅዱስ ዑራኤል ሆይ፤ሁለቱ አዕጋረ ጕንድ ለበቀሉ ዓሥሩ ጣቶችህና ጽፍሮችህ ሰላም እላለሁ ዑራኤል ሆይ፤ ለሄኖክ ምሥጢረ ጥበባትን እንደገለጽህለት ሁሉ ከነበልባላዊው መልአክ ከቅዱስ ገብርኤልና ከደገኛው ከቅዱስ ደቅስዮስ በዓል ጋር በኅብረት በሚከበረው በዓልህ የተሰበሰቡትን ምዕመናን ሁሉ ባርካቸው።

ሰላም ለቆምከ

ቅዱስ ዑራኤል ሆይ፤ ነበልባላዊ አካለ ቆመህና ለእሳታዊ ሥነ መልክእህ ሰላም እላለሁ። ዑራኤል ሆይ፤ ለዕዝራ ሱቱኤል ምስጢርን የሚገልጽ ትንቢትን የሚያናግር ጽዋዓ ልቡናን ለመጋት እንደ ተቻኮልክ ሁሉ። በውስጥ በአፍኣ የከበርክ መልአክ ነህና የአንደበቴን ምስጋና ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን ከኅዘኔ ታረጋጋኝ ዘንድ በሩጫ በችኮላ ፈጥነህ ወደኔ ናዐ ናዐ ናዐ ።

(መልክዐ ቅዱስ ዑራኤል )

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል በሃይማኖት ማስተዋልን ያድለን በምልጃው ይጠብቀን!


ከመ ሀሊብ ዘዕጉልት ወከመ ወይን ዘገነት ስምከ ይጥዕም ዑራኤል መልአክ

በዲያቆን ያለው አይቀር @Yaleway


✝እንኳን አደረሳችሁ!

"" እውነትን ፍረዱ "" (ዮሐ. ፯:፳፬)

❀በዓለ ዕረፍታ ለሶልያና

(ጥር 21 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


Репост из: ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
✝እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ጥር ቡሩክ፥ አመ ፳፩

✝በዓለ ማርያም ድንግል እግዝእትነ
✝ዕረፍተ ሶልያና (እሙ ለፀሐየ ጽድቅ)
✝አስተርእዮታ ለድንግል ውስተ ደብረ ማኅው

✞ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦

✿ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (እኅወ ባስልዮስ ዐቢይ)
✿ኢላርያ ገዳማዊት (ወለተ ዘይኑን)
✿ቀውስጦስ ዐቢይ (ዘመሐግል)
✿ዐቢይ አብሳዲ (ዘደብረ መጉና)
✿ዮሐንስ ከማ (ዘደብረ ሊባኖስ)
✿ተስፋ ኢየሱስ (ዘዋሸራ)
✿ኤልያስ ጻድቅ (ዘመርጦ)
✿ቶማስ አረጋዊ (ዘሐይዳ ደብረ ማርያም)
✿ኒቆላዎስ ወፊቅጦር
✿ዮሐንስ ወእስክንድር
✿ጳውሎስ ወሲላስ
✿ዮሐንስ መጥምቅ
✿ኤርምያስ ነቢይ
✿ብሩታዎስ ዘአቴና
✿ዮሐና ወሰሎሜ
✿ደናግለ እሥራኤል
✿ዮሐንስ ወቶማስ
✿ማርያም ክብራ (ዘጽላልሽ)
✿ጽርሐ ጽዮን ወጌቴሴማኒ

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

https://t.me/zikirekdusn






✝እንኳን አደረሳችሁ ፤ አደረሰነ!

"ስንክሳር - ጥር ፳፩/21"

✝በዓለ ማርያም ድንግል

(ጥር 20 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


Репост из: ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
እንኳን አደረሰን !

አስተርዮ፡ማርያም
------------------------
በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሀዱ፡አምላክ፡አሜን፡፡
አስተርዮ፡ማርያም፡ስልሽ፡ደስ፡ይለኛል፡
የመገለጥ፡ሚስጢር፡ተከናውኖልኛል፡
ገና፡ልጅም፡ሆኜ፡አስተርዮ፡ሲባል፡
እሰማ፡ነበረ፡እስኪደርስ፡ያጓጓል፡፡
አሁን፡ትልቅ፡ሆኜ፡ታሪኩ፡ሲገባኝ፡
ለካስ፡እናቴ፡ነሽ፡አምላኬ፡የሰጠኝ
የመድሃኔ፡ምክንያት፡ተስፋዬ፡የሆንሽኝ፡፡
የሆነውም፡ሆነ፡እሱ፡የወሰነው
የአምላክ፡እናት፡ሆነሽ፡ሞትን፡እንድትቀምሽው፡፡
የአዳም፡ልጆች፡ጠላት፡አስደናቂው፡ሞትም
ወረደ፡ወደ፡አንቺ፡ግዳጁን፡ሊፈጽም
እረፍት፡እንጅ፡ላንቺ ሞት፡ባይስማማሽም፡፡
ሞተች፡ሲባል፡ሰምተው፡የአንቺ፡ጠላቶችሽ
መጡ ከያሉበት፡በእሳት፡ሊያቃጥሉሽ፡፡
መሆንሽን፡እረስተው፡የፈጣሪ፡እናት
ክብር፡እንደ መስጠት፡በስተት፡ላይ፡ስህተት፡፡
ነገሩንም፡ጭረው፡ወደ ኀላ ሲሉ
ቅደም፡ታውፋንያ አንተ ጀግና፡እያሉ
ታውፋንያ፡ሞኙ በእሳት፡ሊያቃጥላት
የተዘጋጀውን ስጋዋ እንዲያርፍበት
የአልጋውን፡ሸንኮር፡ሲነካ፡በድፍረት፡
ምንም፡ሳያስበው፡መላኩ፡በቅፅበት
ሁለቱን፡እጆቹን፡በሰይፍ፡ቆረጠለት፡፡
ይህ፡ነው፡መጨረሻው፡ማን፡አለብኝ፡ማለት፡
ያ ሁሉ፡ፉከራ፡መሬት፡ገባ፡ድንገት
አይ፡የሰው፡ልጅ፡አቅም፡ያሳዝናል፡በእውነት፡፡
እጆቹንም፡ሲያጣ፡ጀግና፡የተባለው፡
የቀረው፡አማራጭ፡ወደ፡እሷ፡ማልቀስ፡ነው፡
እጆቹ፡እንዲድኑም፡አማልጅኝ፡ማለት፡ነው፡፡
እሱ፡መቼ፡አወቀ፡የእሷን፡ሕያው፡መሆን፡
ሞተች፡ሞተች፡ሲሉ ሲሰማ፡ወሬውን
መጣ፡እንጅ፡ዝም፡ብሎ፡ሊያቃጥል፡ስጋዋን፡፡
የእኛም፡እናት፡ድንግል፡የማታሳፍረው፡
የሞተች፡ብትመስልም፡ህያው፡የሆነችው፡
አማላጅነቷን፡አሳየችው፡ወዲያው፡
እጆቹን፡ቀጥላ፡ስለ፡ሆኑ፡ህያው፡፡
እንዲህ፡ናት፡የእኛ፡እናት፡ጠላቶቷን፡የማትወድ፡
ማርያምን፡ይወቃት፡የማያውቃት፡ትውልድ፡
በጦር፡የወጋውን፡አይኑን፡እንዳበራ፡ልጇ፡መድሃኔ አለም
ልጇ፡እንዳደረገ፡አደረገች፡እርሷም፡፡
ስሟ፡ማር፡ወለላ፡ፍቅር፡ናት፡የእኛ፡እናት
የማያውቅ፡ይወቃት፡የሚያውቅም፡ያክብራት፡፡

እንኳን፡ለአስተርዮ፡ማርያም፡አመታዊ፡ክብረ፡በዓል፡በሰላም፡በጤና፡አደረሳችሁ አደረሰን፡፡




✞ በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ ✞

●●◎◉••••••• ✞ •••••••◉◎●●
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
●●◎◉••••••• ✞ •••••••◉◎●●


“ማግባት ለሚሹ”
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

Показано 20 последних публикаций.