✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አስር [፲]
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ እመቤታችንም በደብረ ሊባኖስ ሦስት ወር ያህል ተቀመጠች፡፡ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሊባኖስ በተባለው ተራራ እነዮሴፍ መኖራቸውን ሰምቶ በሠራዊት አስከብቦ ሊይዛቸው ሞከረ፡፡
ጊጋር የሶርያ ገዥ /ጊጋር መስፍነ ሶርያ/
አንድ የሶርያ ገዥ /መስፍነ ሶርያ/ ጊጋር የተባለ ሰው የሄሮድስን እኩይ ምክር ሰለሰማ ወደ እመቤታችን መልእክተኞችን ላከ፡፡
ጊጋር የላካቸው ሰዎች በፈረስ እየጋለቡ በፍጥነት ደርሰው የሊባኖስን ተራራ ሄሮድስ በሠራዊት ሊያስከብበው ነውና ሊባኖስን ለቃችሁ ሽሹ አሏቸው፡፡
መልአኩም መጥቶ ከሊባኖስ ውጡ አላቸው፡፡ እመቤታችን ጌታችን ዮሴፍና ሰሎሜ ደብረ ሊባኖስን ለቀው ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ጊጋር መልእክተኞችን ልኮ እነ ዮሴፍን ከደብረ ሊባኖስ እንዳስወጣቸው ሄሮድስ ሰማ፡፡
የምንፈልጋቸውን ሰዎች ያሸሽህብኝ አንተ ነህ በማለት ጊጋርን ተጣላው፡፡ ሄሮድስ ወታደሮቹን ልኮ የሶርያ ገዢ ጊጋርን አስያዘና በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ጊጋርም በሰማዕትነት ሞተ ። ነሐሴ 16 ቀን በሚነበበው ስንክሳር ይህን የጊጋርን ታሪክ እናገኛለን፡፡
መ.ደብረ ቶና ፦
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ዮሴፍና ሰሎሜ ወደ ደብረ ቶና ሄዱ፡፡ በደብረ ቶና የይሁዳ አገሮች ይታያሉ፡፡ እመቤታችን ብዙ መንገድ በመሄድ ደክማ ነበርና አልሲስ ከተባለ ዛፍ ስር ተቀመጠች፡፡ በጣም ስለደከማት ከዛፉ ስር ተኛች፡፡
መላእክት ነፍሷን በራዕይ ወደ ጽርሐ አርያም ወሰዷት፡፡ የእሳት መጋረጃዎች በቀኝና በግራ በግራ ተከፈቱ፡፡ ልጅዋ ኢየሱስ ክርሰቶስ የሰው ዓይን ያላየውን የሰው ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን በመንግሥተ ሰማያት የሚገኘውን ብዙ ምሥጢር ነገራት፡፡ የሰው ልጆች ለዘለዓለም የሚወርሱትን እጅግ ደስ የሚያሰኘውን ዓለም አየች፡፡
ከዚህ በኋላ ነፍሷ ወደ ሥጋዋ ተመለሰች፡፡ ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ልጅዋን ለምን ወደዚህ የመከራ ዓለም መለስኸኝ አለችው፡፡ ሕፃን ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ አላት ያለመከራ ፀጋ አይገኝም፡፡ በዚህ ዓለም በእኔ ስም መከራ የተቀበሉ ሁሉ በወዲያኛው ዓለም ደስ ይላቸዋል፡፡ አንቺም በወዲያኛው ዓለም ደስ ይልሽ ዘንድ በዚህ ዓለም በመከራ ውስጥ ማለፍ ይኖርብሻል፡፡ ከዚህ በኋላ ከደብረ ቶና ወጥተው ወደ ሲዶና ሄዱ፡፡ ከሲዶናም ወጥተው ወደ ደብረ ዘይት ሄዱ፡፡
ሠ.ቤተልሔም፦
ከደብረ ዘይትም ወጥተው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉ ከሄሮድስ ሠራዊት አንዱ አያቸው፡፡ በፈረስ እየጋለበ በፍጥነት ከሄሮድስ ቤተመንግሥት ደርሶ ማርያም እና ዮሴፍ ሰሎሜም በቤተልሔም አሉ ብሎ ለሄሮድስ ነገረው፡፡ ሄሮድስ ይህን ዜና ያመጣለትን ሰው እንዲህ አለው የነገረኸኝ ነገር እውነት ቢሆን የመንግሥቴን እኩሌታ እስጥሃለሁ እውነት ባይሆን ግን አንተን እገልሃለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ እነ ዮሴፍ በዚህ ቦታ አሉ እየተባለ ተራራውን ሸለቆውን ዋሻውን በሠራዊት እያስከበበ ቢፈልግ ሳያገኛቸው ቀርቷል፡፡
ፈልጎ አለማግኘቱ በብስጭት ላይ ብስጭት ስለጨመረበት አሁን ግን ፈልጎ ባያገኛቸው የጠቆመውን ሰው ለመግደል ቆርጦ ተነሣ፡፡ በዚያች ሌሊት ገብርኤል ወርዶ ዮሴፍን እንዲህ አለው፡፡ በነቢይ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይፈጸም ዘንድ ወደ ግብፅ ሽሽ።ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩ ፡፡
እነ ዮሴፍም በዚች ሌሊት ቤተልሔምን ለቀው ወጡ፡፡ በነጋ ጊዜ ሄሮድስ ቤተልሔምን አስከበባት፡፡ እመቤታችን በታየችበት አካባቢ የተገኙትን ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም አስገደለ፡፡ ሰዎችን ጨርሶ ከዶሮ እስከ ውሻ ያሉ እንስሳትን ሁሉ አስገደለ፡፡ ሰማዩም እንደ ደም ቀይ ሆነ ደም መሰለ፡፡ሄሮድስ ላስገደላቸው ሰዎች ከሰማይ አክሊል ወረደላቸው፡፡ የአክሊሉን መውረድ የተመለከቱ የሄሮድስ ሠራዊትም በማርያም ልጅ በሕጻኑ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን አሉ፡፡
የሥልጣን ፍቅር ውስጡን ያጨለመው ሄሮድስ ግን በድንግል ማርያም ልጅ ያመኑትን ወታደሮች በሰይፍ አስቆራረጣቸው፡፡ ማርያምን በቤተልሔም አየኋት ብሎ የነገረውን ወታደርም በሰይፍ አስቆራረጠው፡፡ የሰዎችን ደም በማፍሰስ የሚረካ እየመሰለው የደም ማፍሰስ ሱስ ያዘው፡፡
ዛሬም ምድራችን የምስኪኖቹን ደም በማፍሠስ ወንበር በሚያደላድሉት የስልጣን ዘመን በሚያራዝሙ ግፈኞች ተሞልታለች፡፡ ይቆይ ይሆናል እንጂ ሁሉም የዘራውን እንደሚያጭድ ይህ ታሪክ ያስረዳልና፡፡
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ በፈረስ ላይ ሆኖ ሲሄድ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ የፈረሱን አፍንጫ መታው፡፡ ፈረሱ ወደ ላይ ሲዘል በላይ የነበረ ሄሮድስ በታች ሆነ በታች የነበረ ፈረስም በላይ ሆነ፡፡ ሄሮድስ ተንኮታኮተ፡፡ አጥንቱ ተሰባበረ ሥጋው ተቆራረጠ፡፡ የብዙዎችን ደም ባፈሰሰበት መሬት ላይ የእርሱም ደም ፈሰሰ፡፡ ሠራዊቱ ተሸክመው ከቤቱ አደረሱት፡፡
ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል...
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem