💎የአደባባይ ጥሪ ነብያዊ ትውፊት!💎
☞ነብያት አውነተኛ ወደ ሆነው ቅናቻ ድምፃቸውን ከፍ አርገው በየገበያው፣ በየአደባባዩና ሰው በተሰበሰበበት ስፍራ ሁሉ ጥሪያቸው አጉልተው ያሰሙ ነበር። ይህን የተቀደሰ ጥሪ ከፊሉ ሲቀበል ከፊሉ ይሳለቅበታል። ከፊሉ ጥሪውን ላለመስማት በልብሶቹ ይከናነባል። ከፊሉ ይዘልፋቸዋል ይብስ ብሎም ይገፈትራቸዋል።
☞ይህ ሁሉ የሚደርስባቸው እኔና አንተን የመሰሉ ጫማችን ተረገጠ ብለው "ዘራፍ!" የሚሉ ትንንሽ ስብእናዎች አይደሉም። እጅግ የተከበሩ የአለማቱ ጌታን መድህን ለአደም ልጅ ለማደረስ መርጧቸው ቃሉን በልሳናቸው ላይ ያኖረ ክቡራን ነብያቶች ናቸው።
☞የአደባባይ ሰበካ ጥንታዊ የነብያት ፋና የቅኖች ልማድ ነበር። መለኮታዊ እዝነትን ለፍጡር ያነገበው ጥሪያቸው ዘልቆ ጆሮኣቸው ደርሶ ልቦናቸው ይመሩ ዘንድ ድምፃቸው እረፍት የለውም። ይሰማል።
☞ከገበያው መሀል ሰው ከተሰበሰበበት ሁሉ ሰተት ብሎ ይዘልቃል። "ህዝቦቼ ሆይ! ጌታቹህ አሏህ ነው ከሱ ሌላ እውነተኛ አምላክ የላችሁም!" የምትለው የተውሒድ ቃል ከአንደበታቸው ጎልታ ትሰማለች።
☞ይህቺን ቃል ሸምቶ የመጣ የእውነት ከንግዱ ያተረፈ ስኬታማ ሸማች አልያም ነጋዴ ነው። እነዛ በነብያት ጥሪ የተሞሉ ገበያዎችና አደባባዮች ዛሬ ታሪክ እንጂ ህዋስ አይደርስባቸውም። የድምፆቹ አሻራ በህሊናችን ቢኖርም፣ ፈለጋቸው ቢታየንም ከጆሮኣችን ግን ርቋል። ንግዳቸውም ከስሟል። ለዘልኣለም ያተረፉት የነብያት ጥሪዎችን በቅን ልቦናና በስል ምልከታ የተቀበሉ ትጉኃን ብቻ ናቸው።
☞ከዳንኪራና ዘፈን ከማስታወቂና ክህደት ጩኸት የነብያት ጥሪ የረበሸው ከንቱ ትውልድ ላይ ነህና እንዳያሰናክሉህ!! ድምፅህን የናፈቁ የተዘጉ ልቦች አሉና በአላህ ፈቃድ ትከፍታቸዋለህ።
☞የነብያት ጥሪ ከቧልትና ዛዛታ ይልቅ ከሰዎች ልብ ሰርፃ ትገባለች። ፍሬን ታፈራለች። ያኔ ጆሮን የሚያውኩ ሰይጣናዊ ድምፆች ይተናሉ። ምን አልባት ላይመለሱ ይሸሻሉ። ግና ይህ የነብያት የስብከት ስልት በግዜ ሂደት በሚገጥሙት እክሎችና ድክመቶች እየተመናመነ ሊጠፋ ጫፍ ደርሷል። አንዳንድ ጥቂት ወንድሞች ፋና ወጊ ሆነው ቢጀምሩትም ቅሉ ጠላትን አፍርቷል። ይህ ነብያት የሚገጥማቸው ፈተና ነውና ፅናቱን ተላበሱ። ህዝቤም ይመራልና! ከጨለማው ብርሃን የናፈቀው የሰይጣን ሲሳይ ታገኘዋለህና በርታ።
☞የኑሕ ምዕራፍ የነብያት ጥሪ ታላቁ ማሳያ የተከበረው ቁርአን ምዕራፍ 71!
71) ኑሕ፣ (የኑሕ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
71:1 - እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡»
71:2 - (እርሱም) አለ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡
71:3 - «አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡
71:4 - «ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡»
71:5 - (ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡
71:6 - «ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡
71:7 - «እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡
71:8 - «ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡
71:9 - «ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ
71:10 - «አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡
71:11 - «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡
71:12 - «በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»
71:13 - ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ?
71:14 - በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡
71:15 - አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?
71:16 - በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡
71:17 - አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡
71:18 - ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡
71:19 - አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡
71:20 - ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡
71:21 - ኑሕ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡
71:22 - «ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎች» (ተከተሉ)፡፡
71:23 - አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡
71:24 - «በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸው» (አለ)፡፡
71:25 - በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡
71:26 - ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡
71:27 - «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡
71:28 - «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤» (አለ)፡፡
- ተፈፀመ-
✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/joinchat/AAAAAEq8AN90dYXSHRVgZA