በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያው ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ እንደነበረና ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንደነበር ቢሮው አስታውቋል።
አሁን የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ደግሞ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ መሆኑን ያስታወቀው ቢሮው፤ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ እያሳሰበ፤ ይህንን በሚተላለፉት አካላት ላይ ቢሮውና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ አሳስቧል።
ህብረተሰቡም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙት በአቅራብያው ለሚገኝ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎችና ለትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በአቅራቢያዎ ባለ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአካል ወይም በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ መስጠት የምትችሉ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa