የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህጋዊ መንገዶች የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለሚከፍቱ ተቋማት ፈቃድ መስጠት ለጊዜውም ማቆሙን አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2024 ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የሀገር ውስጥ የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡በፖሊሲ አውጪ ባንኩ በኩል ይህ ውሳኔ የተላለፈው ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የትይዩ ውጭ ምንዛሬ ገበያውም ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያው ጋር ያለውን የምንዛሬ ዋጋ ልዩነት በማጥበብ ቀስ በቀስም ትይዩ ገበያውን ለማዳከም በማሰብ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት ፒኤልሲ፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል ኢንዲፔንደንት፣ ሮበስት ኢንዲፔንደንትና ዮጋ የውጭ ምንዛሬ መገበያያ ቢሮዎች ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ይታወሳል፡፡አሁን ላይ ታዲያ ሌሎች አዳዲስ ተቋማትን ወደዚሁ ገበያ ከማስገባት አስቀድሞ እነዚህ የውጭ ምንዛሬ መመንዘሪያ ቢሮዎች አፈጻጸማቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለመገምገም ሲባል አዲስ ፈቃድ መስጠት መቆሙን ነው ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው፡፡
እነዚህ ተቋማት ከዚህ ቀደም የባንክ ሥራዎችን ሰርተው የማያውቁ በመሆናቸውና ወደገበያው ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ምክንያት ለገበያው አዲስ አሰራርን ይዘው መምጣታቸውንና ይህም ሁኔታ ባለፉት ጥቂት ወራት ያስመዘገበው ውጤት መገምገም እንዳለበትም ነው በምክንያትነት የቀረበው፡፡የፋይናንስ ዘርፉን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ቢሮውን ለመክፈት እያንዳንዱ ተቋም 15 ሚሊዮን ብር ካፒታልና ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን 30 ሚሊዮን ብር በዝግ አካውንት እንዲያስገቡ በመስፈርትነት ማስቀመጡም የሚታወቅ ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa