ቲክ ቶክ በአሜሪካ ተቋረጠ!
አሜሪካ ቲክ ቶክ በሀገሪቱ እንዲቋረጥ የሚያዘውን ሕግ ከሰዓታት በፊት ተግባራዊ አድርጋለች፡፡እግዱ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ የቲክ ቶክ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱ ፤ “ቲክ ቶክን ለጊዜው መጠቀም አይችሉም” የሚል የጽሑፍ መልዕክት እየደረሳቸው ነው፡፡
መተግበሪያው በአሜሪካ ከጎግል አፕ ስቶር ላይ መጥፋቱም ተነግሯል፡፡ቲክ ቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን ዛሬ እንዲሆን ተቀጥሮ ነበር፡፡ከሰሞኑ የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ አሊያም አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ የተዘጋጀውን ሕግ መደገፉ ይታወሳል፡፡
ባይት ዳንስ በተባለው ካምፓኒ የሚተዳደረው መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ ከ170 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ነበሩት፡፡የካምፓኒው ባለቤት ዣንግ ይሚንግ ከቻይና ዜግነቱ ጋር ተያይዞ ቲክ ቶክ የአሜሪካ መንግሥት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው በሚል ሲያሟግት መቆየቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa