ዜና፡ በ #ሰሜን_ጎጃም ዞን ህጻን ያዘሉ ሴት አስተማሪዎችን ጨምሮ 13 መምህራን "በፋኖ ታጣቂዎች" መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆላላ ወረዳ ኮሬ ጣንክሪ ቀበሌ በሚገኝ ኮሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በማስተማር ላይ የነበሩ 13 መምህራን "በፋኖ ታጣቂዎች" ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ታግተው መወሰዳቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ አንድ የታጋች ቤተሰብ መምህራኑ "በባጃጅ በመጡ ታጣቂዎች" መወሰዳቸውን ጠቅሰው፤ ታጣቂዎቹ "ስርዓቱን ተቃውመን እየታገልን እናንተ ለምን ታስተምራላችሁ" በሚል በነፍስ ወከፍ እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ካልሆነ ግን እንደማይለቀቁ አስጠንቅቀዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ታግተው ከተወሰዱ መምህራን ውስጥ ልጃቸው እንደምትገኝ የገለጹ አንድ ወላጅ አባት በበኩላቸው ትምህርት አስተምሩ መባሉን ተከትሎ አንድ ልጇን አዝላ ወደ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በሚገኘው ኮሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሄደች ልጃቸው መታገቷንና ይህንንም በእጅ ስልካቸው ተደውሎ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa