‹‹አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ረሃብ ተጋርጦባቸዋል›› የዓለም የምግብ ፕሮግራም
አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያን ረሃብ እንደተጋረጠባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
በመላው ኢትዮጵያ ለከፋ ረሃብ ከተጋለጡት ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ያህሉ በግጭትና በአየር ፀባይ መለዋወጥ (Extreme Weather) ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያው ሲረዱ የነበሩ ናቸው ብሏል፡፡
የድርጅቱ ነፍስ የማዳን ተግባራት አቅም በመዋዕለ ንዋይ እጥረት የተነሳ እጅግ መዳከሙን ያወሳው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአሥር ሚሊዮን ረሃብተኞች 3.5 ሚሊዮን ያህሉ እጅግ ተጠቂ ተብለው የተያዙና ዕርዳታ ከእነ አካቴው ሊቋረጥባቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ከፈረሰ በኋላ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታ የማድረስ አቅሙ በእጅጉ እንደተጎዳ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
@Yenetube @Fikerassefa