🚫
ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!
♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!
📵እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!
☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ ላይ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!
☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።
☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ? ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)
☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?
☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?
☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?
☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?
☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?
☞ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!
☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።
☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?
☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?
☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?
☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?
☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?
☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?
✅✅✅✅✅
☞ለላጤዎች ምክር!
♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!
♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!
♻️ ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......
♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ
♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!
♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!
♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
☞ለባለ ትዳሮች ምክር
♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!
♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!
♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!
♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!
✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን/ሁኚ!
♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!
ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ
ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ቅን ቀርቷል/ተመዝግቧል
♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ይምራን!
✍Abdurazaq alhabeshiy
https://t.me/abdurezaq27