መከራውም ያልፋል!
የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ" ዕንባ. 3፥16
በህይወታችን የሚመጡትን ፈተናዎችና መከራዎች አብዛኛዎቻችን ከምንቀበለው መከራ የተነሳ መከራውን ወይም ፈተናውን የሚያቀልልን ይመስል ወይ እናጉረመርማለን ወይም ደግሞ ላገኘነው ሰው ሁሉ ምሬታችንና ብሶታችንን እንናገራለን። አንዳንዶቻችንም የሃዘን እንጉርጉሮ መዝሙርም የምናወጣም አንጠፋም። ብሎም ከህይወት የምንደክምም እንኖራለን፣ “ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት፤ የኀዘን እንጕርጕሮዬን እለቀዋለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።” ኢዮብ 10፥1 እንደሚል።
የመከራ ቀን የሚቆይበት የተሰጠው ጥቂት ጊዜ አለ። ያልፋል! ችግሩ መከራ ሲመጣ የሚያልፍ ስለማይመስል በመከራው በፈተናው መታገስ አቅቷቸው አብረው የሚያልፉ ማለት በፈተናው የተወሰዱ መጽሐፍ ቅዱሳችን የሚጠቅሳቸው ብዙ ሰዎች አሉ ኤሳው በረሃብ ሲፈተን "ይህቺ ብኩርናዬ ለምኔ ናት?” ብሎ ብኩርናን ሸጧል፤ ሳኦል በፍልስጥኤም ሰራዊት ሲከበብ እግዚአብሔርን መጠበቅ ሲገባው ሳይታገስ ስርአቱን ጣሰ፤ የኢዮብ ሚስት ከመከራ በኋላ ያለውን ደስታ ሳታይ ባለመታገሷ ከእግዚአብሔር ተለየች። ሌሎች ሌሎችን ብዙዎችን
ስለዚህ ቅዱሳን
የእግዚአብሔር ቃል “መከራህንም ትረሳለህ፤ እንዳለፈ ወኃ ታስበዋለህ። ኢዮብ 11፥16 እንደሚል የመከራ ቀን ያልፋልና ሳናጉረመርምና ሳንደከም ከምስጋና ጋር በፈተና እንጽና።
እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ።" (መዝ. 71:14)
መልካም ቀን ይሁንልን፣
Via @AmenApostolicMedia
✨ ለሌሎች ሼር አድርጉላቸው
JOIN and SHARE በማስተዋል ዘምሩ ቻናል For More Updats!
👉 @zemeru