ቲቶ ማን ነው ?
ቲቶ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪ፣ ታማኝ የሐዋርያው ጳውሎስ ጓደኛ እና ታማኝ የጌታ የኢየሱስ አገልጋይ ነበር። ቲቶ አህዛብ የነበረ (ገላ 2:3) በጳውሎስ ምክንያት ወደ ወደዚህ መዳን የመጣ (ቲቶ 1፡4) ከጳውሎስ ጋር አብሮ ሰራተኛ ነበር፤ ጳውሎስ እርሱንና በርናባስን ከአንፆኪያ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ ሄዶ ነበር (በሐዋ 15፡2)። ቲቶ ዳግም የተወለደ የአህዛብ ክርስቲያን እውነተኛ ምሳሌ ነበር! ቲቶ የስጋ ግርዘት ስርዓት ለመዳን እንደማያስፈልግ እውነተኛ ማስረጃ ነበር (ገላ 2፡3)።
በኋላ ቲቶ በቤተክርስቲያን ለማገልገል ወደ ቆሮንቶስ ሄደ (2ኛ ቆሮ 8፡6፣ 16-17)። ከ53 እስከ 57 ዓ.ም በተካሄደው የጳውሎስ ሦስተኛው የወንጌል ጉዞ፣ ጳውሎስ ወደ ጢሮአዳ ደረሰ እና ቲቶን አገኘው! (2ኛ ቆሮንቶስ 2፡12-13)። ቲቶ በፊልጵስዩስ ከጳውሎስ ጋር ተገናኝቶ በቆሮንቶስ ስላለው አገልግሎት መልካም ዜና ነገረው (2ኛ ቆሮንቶስ 7፡6-7፣ 13-14)።
ጳውሎስ ቲቶ ወደ ቆሮንቶስ በተመለሰ ጊዜ የ2ኛ ቆሮንቶስ መልእክት በእጁ ሰጠና በኢየሩሳሌም ያሉ የተቸገሩ ቅዱሳን ሰበሰበ (2ኛ ቆሮንቶስ 8: 10, 17, 24)። ከበርካታ ዓመታት በኋላ ቲቶና ጳውሎስ ወደ ቀርጤስ ደሴት ሄዱ፤ በዚያም ቲቶ ሥራውን ለመቀጠልና ለማጠናከር ወደ ኋላ ቀርቷል።
የቲቶ ተግባር አስተዳደራዊ ነበር፣ በአብዛኛው ጤናማውን ትምህርት መጠበቅ እና "ያልተጠናቀቁትን ማቅናት እና በየከተማው ሽማግሌዎችን መሾም" (ቲቶ 1፡5) ነበር። አርጤማስ እና ቲኪቆስ አገልግሎቱን ለመምራት ወደ ቀርጤስ በደረሱ ጊዜ ጳውሎስ ቲቶን በምዕራብ ግሪክ በአካይያ አውራጃ በምትገኝ በኒቆጶል ከተማ እንዲገኝ አስጠራው (ቲቶ 3፡12)።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ቲቶ ለመጨረሻ ጊዜ የተጠቀሰው ጳውሎስ በመጨረሻ የሮም እስር ቤት በነበረበት ወቅት ከጳውሎስ ጋር እንደነበረ ያሳያል። ከሮም ቲቶ ዳልማጥያን እንዲሰብክ ተላከ (2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡10) አሁን ሰርቢያ ናት!
ቲቶ ታማኝ የጌታ አገልጋይ እና ለጳውሎስ የተሰጠ ረዳት ነበር። ጳውሎስ በቆሮንቶስ፣ በቀርጤስ እና በድልማጥያ ሥራዎችን እንዲመራ ስለ ሾመው ታማኝ እና እምነት የሚጣልበት እንደሆነ እንረዳለን።
በእርግጥም ጳውሎስ “ባልንጀራዬና አብሮኝ የሚሠራ" (2ኛ ቆሮንቶስ 8፡23) ብሎ ይጠራዋል። በቆሮንቶስም ሆነ በቀርጤስ የነበሩትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በማወቅ ቲቶ ችግሮችን በጸጋ የሚፈታ አስተዋይ ሰው እንደነበረ መገመት እንችላለን።
መጽሐፍ ቅዱሳችን ቲቶ ለቆሮንቶስ አማኞች ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፍቅር እንደነበረው ይናገራል። እንዲያውም ቲቶ ወደ ቆሮንቶስ ሲመለስ በጋለ ስሜትና በራሱ ተነሳሽነት ሄደ ይላል ቃሉ (2 ቆሮንቶስ 8፡16-17)።
እያንዳንዱ ክርስቲያን ቲቶ ለእውነት ያለውን ቁርጠኝነት፣ ወንጌልን በማስፋፋት ያለው ቅንዓት እና ለቤተክርስትያን ያለውን ፍቅር ስናይ በዚህ ዘመን ላለን ለሁላችንም ምሳሌ የሚሆን ነው!
ተባረኩልን!
Source
@Lejunegnለሌሎች ሼር ያድርጉላቸው
JOIN and SHARE በማስተዋል ዘምሩ ✨ ቻናል For More Updats!
👉
@zemeru