ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ በመሬት ናዳ ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች መርጃ የሚውል 1 ሚሊዮን ብር ለገሠ
በጎፋ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳው ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቁጥር 257 መድረሳቸውን፤ የሟቾቹ ቁጥር እስከ 500 ድረስ ሊያሻቅብ እንደሚችልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁን መዘገባችን ይታወቃል።
ድምፃዊው ትናንት በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሰሞኑን በደቡቡ የሀገራችን ክፍል (ጎፋ) በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ በደረሰውም አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ።” ማለቱም ይታወሳል።
#ዳጉ_ጆርናል