በትግራይ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 17 ሺህ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ
በትግራይ ክልል የወባ በሽታ እየጨመረ እንደሚገኝ እና በየሳምንቱ በሚደረግ ሪፖርት መሰረት ባለፈው ሳምንት 17 ሺህ ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል። የበሽታው ስርጭት ቢጨምርም የሰው ሞት አለመመዝገቡን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋዊ ገ/መድህን ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።
አጎበር እና ኬሚካል በብዛት ማግኘት እንዳልተቻለ ኃላፊው ተናግረዋል። በሽታውን መቆጣጠር ያልተቻለበት ምክንያት የግብአት እጥረት፣ የአየር ሁኔታው ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል ብለዋል።
አያይዘውም በተለይም ያለመረጋጋትእና የተፈናቃዮች ቁጥር መብዛት ስርጭቱን ለመቆጣጠር አክብዶታል ሲሉ አቶ አረጋዊ ገ/መድህን ጨምረው ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በተቻለው አቅም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የማስገንዘብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል