የጾታዊ ግንኙነት ጥያቄን አልተቀበልሽም በማለት በፍቅረኛዉ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰበታ አዋስ ወረዳ የወሲብ ጥያቄዬን አልተቀበለችም በማለት ፍቅረኛው ላይ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቅጣቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ እንደገለፁት ተከሳሽ ከድር ሁላላ የተባለው ግለሰብ ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዐት ተኩል ላይ የ 25 አመት እድሜ ያላትን ፍቅረኛውን ወደ መኖሪያ ቤቱ በመጥራት የጾታዊ ግንኙነት ጥያቄ እንዳቀረበላት እና ወጣቷም ጊዜው አሁን እንዳልሆነ እና እርሷም ለዚህ ዝግጁ እንዳልሆነች የገለፀችለት መሆኑም ተረጋግጧል።
በዚህ በፍቅረኛው ምላሽ ንዴት የገባው ተከሳሽ በርካታ ብሮችን እየቆጠረ ለፍቅረኛው በማሳየት ለማባበል ቢሞክርም የብር ማሰሪያ ላስቲክ መሬት ላይ በመጣል የብር ማሰሪያውን አንስታ እንድትሰጠው በትዕዛዝ መልክ መጠየቁም ተገልፆል።የ25 አመቷ የግል ተበዳይ የሆነችው ወጣትም የብር ላስቲኩን ለማንሳት ከተቀመጠችበት ተነስታ ጎንበስ ስትል ተከሳሹ ያዘጋጀውን ስለታም ቢላ በቀኝ የጀርባ አጥንቷ ላይ በማሳረፍ እንደወጋትና ጉዳት እንዳደረሰባት በማስረጃ ተረጋግጧል። ጉዳት የደረሰባት ወጣት በወቅቱ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት የአካባቢ ሰዎች ደርሰው በፍጥነት ወደ ሰበታ ጤና ጣቢያ በማድረስ የህክምና አገልግሎት በማግኘቷ ህይወቷ ሊተርፍ ችሏል። ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በክትትል ከተሸሸገበት በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉንም ገልፀዋል።
ተጎጂዋ ወጣት ተከታታይ የህክምና እርዳታ ካገኘች በኋላ ፖሊስ በማስረጃነት ቃሏን ተቀብሎ የምርመራ መዝገቡን በተገቢ የሰው ማስረጃ እና ወንጀሉ የተፈፀመበትን ቢላዋ በኤግዚቢትነት በመያዝ እንዲሁም ከአካባቢው ሰዎች ማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገብ አጠናቆ ለአቃቤ ህግ ልኳል።
አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በሰው መግደል ወንጀል ሙከራ አንቀፅ 540 እና አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት ክስ የመሠረተ ሲሆን ከአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረዎ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ከድር ሁላላ የሱፍ ጥፋተኛነቱ በአቃቤ ህግ ማስረጃ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ በሰው መግደል ወንጀል ሙከራ በሰባት አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ገልፀዋል።
በሰመኃር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል