በኢትዮጵያ 40 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት 5 ዓመት ሳይሆናቸው በውሃ ብክለት ህይወታቸውን እንደሚያልፍ ተነገረ
በኢትዮጵያ አሁንም በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና ጤንነቱ የተጠበቀ መጸዳጃ ቤት እንደማይጠቀሙ ተነግሯል።በጤና ሚኒስትር የውሃ ሳኒቴሽን እና ሃይጅን ባለሙያ የሆኑት አቶ ይመኑ አዳነ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በኢትዮጵያ 40 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት አምስት ዓመት ሳይሆናቸው በውሃ ብክለት በሚመጡ በሽታዎች ህይወታቸው እንደሚያልፍ ገልጸዋል ።
ንጹህ ውሃ አለመኖር እና መጸዳጃ ቤቶች ንጽህናቸውን የጠበቁ አለመሆናቸዉ ከጤና ባለፈ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ህይወት ላይ ትልቅ ጫና እንደሚያሳድር ተገልጿል ። በዓለም ላይ 3.5 ቢሊዮን ህዝብ ንጽህናውን የጠበቀ የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት እንደማይጠቀም የተጠቆመ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 419 ሚሊዮን የሚሆነው ሜዳ ላይ የሚጸዳዳ መሆኑ አክለው ገልጸዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ሜዳ ላይ፣ በቆሻሻ እና በወንዝ ዳሮች ላይ በሚጸዳዱ ግለሰቦች ምክንያት ለበርካታ በሽታዎች እና ለጤና እክል እየተዳረጉ መሆኑ ተነግሯል።
በተመሳሳይ በትምህርት ቤቶች ላይ የመጸዳጃ ቤቶች ባለመኖራቸው ምክንያት በርካታ ሴት ተማሪዎች በወር ከ 5 ቀን ባላነሰ ከትምህርት ገበታቸው እንደሚቀሩ ተነስቷል ።ደረጃቸዉን ባልጠበቁ በመጸዳጃ ቤቶች እና ንጹህ የውሃ አገልግሎት ባለመኖሩ በሚመጡ በሽታዎች ኢትዮጵያ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ይህም ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደሚያስከትል አቶ ይመኑ አዳነ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። እጅን መታጠብ ብቻ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑ በንጽህና የሚመጡ በሽታዎችን መከለካል የሚያስችል እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል