የፍልስጤም ክርስቲያኖች የገና በዓልን ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ መልኩ ማክበራቸው ተነገረ
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ተብሎ በሚከበረው የልደት በዓል ቤተ ክርስቲያናት በገና ዛፍ ዛፍ ሳይደምቁ እና በጣጌጥ ሳያሸበርቁ በእስራኤል በተያዘች የዌስት ባንክ ቤተልሔም ከተማ የደስታ በዓል ሳይሆን አልፏል።
ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመትልት በማዕከላዊ ቤተልሔም የቴራ የገና አባት ጦር ቀይ ሸማ ለብሰው፣ ነጋዴዎች ኑግ እና ሻዋርማ የሚሸጡበት ዋናውን የገበያ ጎዳና እጅግ በሰዎች የተሞላ ነበር። የገና ዜማዎችን የሚዘምሩ ሕፃናት ደስ የሚል ድምፅ አየሩን ይሞላው ነበር። አሁን ላይ “እኛ የምንፈልገው ሕይወት እንጂ ሞት አይደለም” እንዲሁም “የጋዛን የዘር ማጥፋት አሁኑኑ ይቁም!” በሚሉ በባነሮች ላይ የተጻፉት መልእክቶች የበዓሉን ድባብ አጥፍተዋል።ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመታት በቤተልሔም የገና በዓል በጦርነት ውስጥ ለማሳለፍ ተገደዋል።
ኢየሱስ የተወለደው ከ2,000 ዓመታት በፊት ነው ብለው በሚያምኑበት ዋሻ አናት ላይ በተገነባው የክርስቶስ ልደት ቤተክርስቲያን ትይዩ አንድ ትልቅ የገና ዛፍ በመንገር አደባባይ ላይ ከዚህ ቀደም ይሰራ ነበር። ነገር ግን ልክ እንደባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም የቤተልሔም ማዘጋጃ ቤት በጋዛ ለሚሰቃዩ ፍልስጤማውያን አክብሮት በማሳየት ልከኛ በዓላትን ለመምረጥ ወስኗል።በቅዲስቲቷ አገር ያሉ ክርስቲያኖች ቡእስራኤል በኩል ቁጥራቸው 185,000 ያህሉ ሲሆኑ 47,000 በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ይገኛሉ። ክርስቲያኖቹ ጸሎት መጽናኛና የወደፊት ተስፋን ይሰጣል ሲሉም ይደመጣሉ።
የቤተልሔም ከተማ ከንቲባ አንቶን ሳልማን "መከራችንን እንዲያቆምልን ወደ እግዚአብሔርን እንጸልያለን፤ ሉዓለም ክፍል በሙሉ የምንጠብቀው ሰላምን ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውልደቱ ለዓለም ያመጣውን ሰላም እንዲሰጠን እንለምነዋለን" ብለዋል። የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በቤተልሔም እኩለ ሌሊት ቅዳሴን ለመምራት ሲዘጋጁ ተመሳሳይ የተስፋ መልእክት አስተላልፈዋል። ጳጳሱ እንዳሉት ትናንት ከጋዛ ነው የመጣሁት። ሁሉም ነገር ሲወድም፣ ድህነት ሲያይል እና ጥፋትን አይቻለሁ ብለዋል። ነገር ግን ህይወትንም አየሁ ፤ ተስፋ አትቁረጡ በማለት ፒዛባላ ከቤተልሔም የሰላምና የባህል ማዕከል በራፍ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ የቦምብ ድብደባ መፈፀማቸውን ቀጥለዋል፣ በደቡባዊ ካን ዮኒስ አራት ፍልስጤማውያንን፣ በሰሜን ቤይት ሀኖን 3 እና በማዕከላዊ የኑሴራት ካምፕ ውስጥ አንድ ሰው በጥቃቶቹ ተገድለዋል። የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ በታሙን ከተማ ላይ በፈፀሙት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያንን አቁስለዋል። በእስራኤል ግዛት ውስጥ ደግሞ የእስራኤል ጦር ከየመን የተተኮሰ ሚሳኤልን አውርዶ ለመጣል ከወሰደው ለመደበቅ ሲሮጡ ከነበሩ ሰዎች መካከል ቢያንስ 9 ሰዎች ቆስለዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል