በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜና እሁድ ባጋጠሙ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
ለሰዎች ህልፈት ምክንያት ከሆኑት መካከል አንደኛው ሞት የተመዘገበዉ የተቆለለ አፈር ተደርምሶ የተከሰተ ሲሆን ሌላኛው ሞት ደግሞ የስምንት አመት ልጅ የፍሳሽ ማስወገጃ ታንከር ውስጥ በመግባቱ የተነሳ ነው።በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ባለፉት የእረፍት ቀናቶች ሶስት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።
አደጋዎቹ ያጋጠሙት ቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ቡልቡላ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን የተተዉ ጉድጓድ በአፈር የሙላት ስራ እየተከናወነ በሚገኝበት ስፍራ ውስጥ በተሽከርካሪ ከሚደፋዉ አፈር ብረትና መሰል ቁሳቁሶችን ለመልቀም ወደጉድጓዱ ከገቡ አራት ወጣቶች መካከል የተቆለለው አፈር ተደርምሶ የአንደኛዉ ህይወት ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የግለሰቡን አስከሬን ለማዉጣት ከስምንት ሰዓት በላይ የፈጀ ሲሆን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አንድ ስካቫተር በማቅረብ ፍለጋዉን ማገዙ ተገልፃል፡፡በሌላ በኩል በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 ፍየል ቤት እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እድሜዉ ስምንት ዓመት የሆነ ታዳጊ ጠፍቶብናል በሚል ወላጆች ለፖሊስ ሪፖርት ያደርጋሉ።ሪፓርቱ የደረሰው ፖሊስ ባካሄደው ፍለጋ የታዳጊዉ ጫማ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሚገኝ የፍሳሽ ማስወገጃ ታንከር አጠገብ በመገኘቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በፍሳሽ ማስወገጃ ታንከር ዉስጥ ባካሄዱት ፍለጋ የታዳጊዉን አስከሬን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
ባለፈው አመት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገብስ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግቢ ዉስጥ ኳስ በመጫወት ላይ የነበረ የአምስት ዓመት ታዳጊ ክፍቱን በተተወ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ዉስጥ ገብቶ ህይወቱ ማለፉን አቶ ንጋቱ አስታውሰዋል።በአዲስ አበባ በተለይም የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የመጸዳጃ ቤት የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከሮች ክዳናቸዉ ያልተዘጋና በቂ ከለላ ባልተደረገባቸዉ ቦታዎች መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ አስፈላጊዉን ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ በመዉሰድ ሊያጋጥም የሚችለዉን አደጋ አስቀድሞ መከላከል ይገባልም ሲሉም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በኮልፌ ወረዳ 9 ጦር ሀይሎች አካባቢ ፣ በአቃቂ ወረዳ 5 ፣በኮልፌ ወረዳ አራት አለም ባንክ አካባቢ በመኖሪያና በመጋዘን ላይ ቀላል የእሳት አደጋ አጋጥሞ በፍጥነት መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በትግስት ላቀዉ
#ዳጉ_ጆርናል