ሀማስ ሶስት ታጋቾችን መልቀቁን ተከትሎ 90 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ተለቀቁ
የእስራኤል ባለስልጣናት ሃማስ በጦርነት ለተጎዳው የጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሴት ምርኮኞች አሳልፎ መስጠቱን አረጋግጠዋል። የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ እሁድ አመሻሹ ላይ እንደተናገሩት የ24 ዓመቷ ሮሚ ጎነን፣ የ28 ዓመቷ ኤሚሊ ዳማሪ እና የ31 ዓመቷ ዶሮን ሽታይንብሬቸር ለቀይ መስቀል ተላልፈው በእስራኤል ውስጥ “ደህንነታቸው በተጠበቀ ስፍርል ውስጥ ናቸው” ብለዋል።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት 90 የፍልስጤም እስረኞች ተለቀዋል። ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱት ፍልስጤማውያን 69 ሴቶች እና 21 ታዳጊ ወንዶች ከዌስት ባንክ እና እየሩሳሌም እንደተለቀቁ ሃማስ አስታውቋል። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከተፈቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በቅርቡ የታሰሩ እንጂ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ወይም አልተፈረደባቸውም ብሏል።
በመጀመርያው የእርቅ ሂደት እስራኤል ወደ 1,900 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትፈታ ሲጠበቅ ሃማስ 33 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።የመከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት በዚህ የመጀመሪያ ስድስት ሳምንት ሂደት "በየሳምንቱ ከሦስት እስከ አራት ተጨማሪ ታጋቾች ይለቀቃሉ"። የሐማስ ባለስልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ቀጣዩ የታገቱ ሰዎችን የማስፈታት እና የእስረኞች ቅያሬ ቅዳሜ ይካሄዳል።
ከ630 በላይ ሰብዓዊ ርዳታዎችን የጫኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች እሁድ እለት ጋዛ የገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 300 ያህሉ ወደ ሰሜናዊው ጋዛ ሰርጥ አቅጣጫ ማቅናታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ቶም ፍሌቸር ተናግረዋል።በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአማካይ 40 የጭነት ተሽከርካሪዎች ብቻ እየገቡ ነበር፣ ከግጭቱ በፊት ግን በየቀኑ 500 የሚጠጉ የረድኤት ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ ይገቡ ነበር። የተኩስ አቁም ስምምነቱ በየቀኑ 600 የእርዳታ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ የሚያስችል ነው።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል