በ2017 በጀት ዓመት በአዊ ዞን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች በአስር የውጪ ዜጎች ብቻ መጎብኘታቸው ተነገረ
በ2017 በጀት ዓመት በአዊ ዞን የሚገኙ የቱሪዝም ቦታዎች ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገልጿል ።በአዊ ዞን በበጀት ዓመቱ 330 ሺህ ሰው ወደ አካባቢው በመሄድ ይጎበኛል ተብሎ ቢጠበቅም ወደ ቦታው የሄደው 75 ሺህ ቱሪስት ብቻ መሆኑ ተገልጿል ።
በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ አለመሆኑ በአካባቢው የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት መሆኑን የአዊ ዞን የባህል እሴቶች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዋለልኝ ጌቴ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በሩብ ዓመት እቅዱ 330 ሺህ ጎብኝዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ወደ አካባቢው የሄዱ ቱሪስቶች ቁጥር 75 ሺህ 364 ብቻ ነዉ። ይህም ከተያዘው እቅድ በታች መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም በገንዘብ ደረጃ ከቱሪስት ለማስገባት የታቀደው 131 ሚሊዮን 640 ሺህ ብር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን 12 ሚሊዮን 175 ሺህ ብር ገቢ ማድረግ ተችሏል። በአካባቢው ከተገኙት ጎብኝዎች መከካል 10 ብቻ የሚሆኑት የውጪ ዜጎች መሆናቸውን እና 60 ሺህ ብር የሚሆነው ገንዘብ ገቢ የተደረገው ከአስሩ የውጪ ዜጎች መሆኑን አቶ ዋለልኝ ጌቴ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በአካባቢው በርካታ ቱሪስቶች የሚገኙበት የፈረስ ውድድር በጥር 27 የሚከበር መሆኑ እና በዚህም በርካታ ቱሪስቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል ። ይህንንም ክብረ በዓል ለማክበር በርካታ ቅድመ ዝግጅቶች የተደረጉ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በበዓሉ ላይ አካባቢውን የምትወክለዋን ቆንጆ ለመምረጥ የቁንጅና ውድድር ፣ ኤግዚብሽን ፣ የፈረስ ውድድሮች እና ሌሎች ስርዓቶችም በእለቱ የሚጠበቁ መሆናቸው ተጠቁሟል።ክብረ በዓሉም ጥሩ የሚባል ገቢ እና በርካታ ቱሪስቶች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን አቶ ዋለልኝ ጌቴ ገልጸውልናል ።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል