የአዲስ አበባ ፖሊስ የባለሀብቱን ገዳዮች መያዙን አስታወቀ
መሰረት ሚዲያ ከሀያ ቀን በፊት ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ መዘገቡ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ይፋ ባረገው መረጃ የባለሀብቱን ገዳይ እና አስገዳይን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
"ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመቀየር ከወንጀሉ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሐሰተኛ ስም ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመጥፋት ቢያስቡም በተሰራው እረፍት አልባ ፖሊሳዊ ጥበብ በታከለበት የክትትልና የምርመራ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል" ያለው ፖሊስ የወንጀሉ ፍሬ የሆነው ንብረትነቱ የአቶ አብዪ አይተነው ፈንታ የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ እና ለማምለጥ የሞከሩበት እንዲሁም ሽጉጡን የደበቁበት ላንድክሩዘር ተሽከርካሪ በኤግዚቢትነት ተይዟል ብሏል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት እና የ 'ምናሉ ሆቴል' ባለቤት አቶ ቢረሳው ግድያ ከተፈፀመባቸው በኋላ ቀብራቸው በሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ምንጭ:- መሰረት ሚዲያ
#ዳጉ_ጆርናል