ትራምፕ ወጣቶች የሥርዓተ-ፆታ ለውጥ ለማድረግ ከአሜሪካ መንግስት የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ አቋረጡ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኤልጂቢቲኪው ወጣቶች የሚሰጠውን የሥርዓተ-ፆታ ሽግግሮች የገንዘብ ድጋፍ እና ማስተዋወቅም ለማቆም የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ፈርመዋል። ማክሰኞ በተፈረመው ትእዛዝ መሰረት የፌደራል መንግስት ከ19 ዓመት በታች ለሆኑት የስርዓተ-ፆታ ሽግግሮችን “ገንዘብ አያስተዋውቅም ወይም አይደግፍም” ብለዋል ።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሕጻናት የጾታ ቅየራ የአካል ንቅለ ተከለ ካደረጉ በኃላ ተጸጽተዋል የራሳቸውን ልጅ መውለድ ወይም ልጆቻቸውን ጡት በማጥባት ማሳደግ እንደማይችሉ በመረዳት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል። "በተጨማሪም እነዚህ ተጋላጭ ወጣቶች በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከፍተኛ የህክምና ክፍያ ሊኖርባቸው ይችላል፣ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ በእድሜ ልክ የህክምና ችግሮች፣ በሰውነት አካሎቻቸው ላይ የተደረገው ቀዶ ህክምና ሰለባ ሆነዋል።
የትራምፕ ትዕዛዝ በስርዓተ-ፆታለሚሰቃዩ ወጣቶች የተለያዩ ህክምናዎችን እና ሂደቶችን ይሸፍናል ይህ ደግሞ ባዮሎጂካዊ ጾታቸው ከቀየሩት የጾታ ማንነታቸው ጋር የማይዛመድ ሰዎች የሚሰማቸውን ጭንቀት ለማስዉገድ ያግዛል። የጉርምስና ለውጦች አለመታየት ጨምሮ የጾታ ሆርሞን ሕክምና እና የቀዶ ሕክምናን ይጨምራል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል