ኮካኮላ በትራምፕ ታሪፍ ህግ የተነሳ ከጠርሙስ ይልቅ ተጨማሪ የፕላስቲክ ለስላሳ እንደሚያቀርብ አስታወቀ
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የታሪፍ ዋጋ የአሉሚኒየም ጣሳዎችን የበለጠ ውድ የሚያደርግ ከሆነ ኮካ ኮላ በአሜሪካ ውስጥ በፕላስቲክ ጠርሙሶች ውስጥ ብዙ መጠጦችን መሸጥ ሊኖርበት ይችላል ሲሉ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄምስ ኩዊሴ ከባለሃብቶች ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል ።ትራምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሁሉም ብረት እና አሉሚኒየም ላይ 25 በመቶ ቀረጥ እንዲጣል ካዘዙ በኋላ በሀገሪቱ የታሸጉ ምግቦችን እና መጠጦችን ዋጋ ከፍ ሊያደርግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል ።
የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች ለስድስት ተከታታይ ዓመታት የለስላሳ መጠጥ አምራቾችን "የዓለም አቀፍ የፕላስቲክ ብክለት ዋና ምንጭ" ብለው ሰይመዋል። ይህም ተጨማሪ ብክነት እንዲከሰት የትራምፕ የታሪፍ እቅድ ያደርገዋል፡፡አንድ ጥቅል የግብአት ወጪ ላይ የተወሰነ ጭማሪ ካጋጠመን በተመጣጣኝ ቦታ ላይ እንድንወዳደር የሚያስችለን ሌሎች የማሸጊያ አቅርቦቶች መጠቀማችንን እንቀጥላለን ሲል ኩዊሴ ተናግረዋል።"ለምሳሌ የአሉሚኒየም ጣሳዎች የበለጠ ውድ ከሆኑ በፕላስቲክ ጠርሙሶች ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ እንችላለን" ብለዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ የምትጠቀመውን አሉሚኒየም ግማሹን ወደ ሀገር ውስጥ ታስገባለች፡፡፡ ስለዚህ በሁሉም ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ሲጣልባቸዉ የበለጠ ውድ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል።ለፕላስቲክ ብክለት አስተዋፅዖ ሊያደርግ በሚችለው የተለየ እርምጃ የአሜሪካ መንግስት የፕላስቲክ ምርቶችን በወረቀት ለመተካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናቆ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ትራምፕ የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ተፈራርመዋል።ትዕዛዙ የፕላስቲክ ብክለትን “ቀውስ” ፈጥሯል ተብሎ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተፈረመውን እርምጃ ቀይሮታል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል