ሁለት ልጆችን ከቤተሰቦቻቸዉ እዉቅና ዉጪ ሰርቆ በመዉሰድ በጉልበት ስራ ላይ ሲያሰማራ የነበረዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጂዳ ወረዳ ዉስጥ ሲሆን ገዜ ታምሩ በተባለ ግለሰብ አማካይነት ነዉ ። ህፃናቱን በተለያየ ጊዜ እና ቀን ከቤተሰቦቻቸው እዉቅና ዉጪ ሰርቆ በመዉሰዱ በእስራት መቀጣቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ገልጿል ።
የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት የተለያዩ ወንጀሎችና የነፍስ ግድያ ምርመራ ክፍል ኃላፊ አቃቤ ህግ አብዮት አስፋዉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግለሰቡ ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በጂዳ ወረዳ ስርጤ ከተማ ዉስጥ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤት በመመለስ ላይ የነበረዉን የ14 አመት ልጅ በወር 25ሺህ ብር ክፍያ ታገኛለህ አዲስአበባ ስራ ላስቀጥርህ በማለት አታሎ በመዉሰድ ለጉልበት ስራ እንዳሰማራዉ ገልጸዋል ።
ይህዉ ተከሳሽ ከ3 ቀናት በኋላ ከአዲስአበባ በመመለስ የ13 አመት ልጅን በወር 20ሺህ ብር የሚያገኝበት ስራ እንዳገኘለት በመንገር ከቤተሰቦቹ ሰርቆ በመዉሰድ ወደ አዲስአበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ ሙቀጥሬ ከተማ ኬላ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል ። ተከሳሹ ህፃናቱን አታሎ በመዉሰድ ለጉልበት ስራና ብዝበዛ እንዲገላጡ አድርጓ። ፖሊስ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ ልኳል ።
አቃቤ ህግም ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን ለመቆጣጠር የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና በወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ክስ መስርቷል ። ክሱን ሲከታተል የቆየዉ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተካሳሹን ጥፋተኛ በማለት በ10 ዓመት እስራትና በ10 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን አቶ አብዮት አስፋዉ ገልጸዋል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል