በሰሜን ዳርፉር በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ
በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) ተከፈተ የተባለው የአውሮፕላን ጥቃት እሁድ እለት በሰሜን ዳርፉር ግዛት አል-ማሊሃ አካባቢ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድል አራት ሰዎችን አቁስሏል። ከኤል ፋሸር በስተሰሜን 210 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው እና ሱዳን ከሊቢያ በሚያገናኘው ድንበር ላይ የምትገኘው አል-ማሊሃ ከሱዳን ጦር ጋር በመተባበር እየተዋጉ ባሉት የታጠቁ ቡድኖች የጋራ ሃይል ቁጥጥር ስር ነች።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከተማዋ ወደ ኤል ፋሸር ከተማ ለማምራት እንደመነሻ አድርጎ በማሰብ ከሰራዊቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ማጠናከሪያ እያገኘችም ነው።በሰሜን ዳርፉር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ኢብራሂም ካቲር ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት “ፈጣን የድጋፍ ሰጪ ሃይሎች በአል-ማሊሃ ከተማ በፈፀሙት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 4 ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ አረጋግጠዋል። ወታደራዊ ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ ደግሞ አንድ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ቡድን በአካባቢው ወታደራዊ ቦታዎችን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ ኢላማ አድርጎ መቷል ብለዋል።
የፀረ-አውሮፕላን መከላከያ የተወሰኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ እንዲወድቁ ያደረገ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ የጋራ ሃይሉ ያለባቸውን ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ጉዳት ሳያደርሱ በተሳካ ሁኔታ መውደቃቸውን ጠቁመዋል። ከሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ወደ ከተማዋ የሸሹ ተፈናቃዮች መኖርያን ጨምሮ በአንዳንድ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ እና የእሳት ቃጠሎ መፈጠሩን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል።
በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ በሆነችው በኤል ፋሸር፣ ጦር ሰራዊቱ እና የጋራ ኃይሉ ቀደም ሲል በከተማዋ ደቡባዊ እና ደቡብ-ምስራቅ ሰፈሮች ውስጥ በRSF ወደተያዙ አካባቢዎች መግፋታቸውን ቀጥለዋል። ሰራዊቱ እና አጋሮቹ ባለፉት ወራት ሲቆጣጠሩት የነበሩት የ RSF ታጣቂዎችን ከነዚህ ቦታዎች ካባረሩ በኋላ “አል-ፍርዳውስ፣ አል- ሂጅራ፣ አል-ጀዋማአ፣ አል-ዋህዳ፣ አል-ሰላም እና አል-ዋህዳ” የተባሉትን ሰፈሮች እንደገና መቆጣጠር ችለዋል።
ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ የዳርፉር ግዛት ታሪካዊ ዋና ከተማ የሆነችው ኤል ፋሸር በሰራዊቱ እና በተባባሪዎቹ መካከል በአርኤስኤፍ ላይ በተነሱት የትጥቅ እንቅስቃሴዎች መካከል ኃይለኛ ግጭቶች ታይተዋል። አርኤስኤፍ በዳርፉር ክልል የመጨረሻው የቀረው የሱዳን ጦር ይዞታ ለመቆጣጠር ይፈልጋል።
በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ በተካሄደው ጦርነት የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ የተዘገበ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ከ500ሺ በላይ ሰዎች ወደ ታዊላ፣ ጀበል ማርራ እና በሰሜን ሱዳን በሚገኙ አካባቢዎች አንደተፈናቀሉም ተዘግቧል። የተራዘመው ጦርነት እና ከበባ ከፍተኛ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት አስከትሏል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል