በትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ
ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ ወረዳ ባላሚ በተባለ ከተማ
ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ላይ ነው የደረሰው።
በትራፊክ አደጋው ህይወታቸው ካለፈ 17 ሰዎች በተጨማሪም 13 ሰዎች ላይ ከከባድ
እስከ ቀላል አካላዊ ጉዳት መድረሱም ነው የተገለፀው።
ከእነዚህም ውስጥ 9 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት 4 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል
ጉዳት መድረሱን የሚዳቀኝ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር
አዲሱ ኮሬ ተናግረዋል።
በትራፊክ አደጋውም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አምቦ እና በጌዶ ሆስፒታሎች
ተወስደው የህክምና ክትትል እንዲያገኙ መገደረጉንም አስታውቀዋል።
የትራፊክ አደጋው የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ ከባለሚ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ
ከከተማው መናኸሪያ በመውጣት ላይ እያለ ከጌዶ ከተማ በመምጣት ላይ በነበረ ሲኖ
ትራክ ተሽከርካሪ በመገጨቱ ነው የደረሰው።
ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪው ፍሬኑ አልይዝ ብሎት ቁልቁለት በፍጥነት በመጓዝ ላይ
እያለም አነስተኛ ተሽከርካሪ በመግጨት መንገዱን ስቶ እንዲወጣ አድርጎ አንድ ሰው
ተገጭቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉም ነው የተገለፀው።
@zena24now