የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ትናንት ባካሔደው ስብሰባ አቶ ዳዊት ከድር (ጆኒ) ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ እና ኢንስትራክተር ፉዓድ ዩሱፍ ምክትል አሰልጣኝ በማድረግ ሰይሟል።
ኢንስትራክተር ፉዓድ ድሬዳዋ የተወለደ ሲሆን ድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ፣ ሓፍካት እና ድሬዳዋ ምድር ባቡር በተጫዋችነት አሳልፏል ፉዓድ በአሰልጣኝነት ሙያም ብዙ አመታት ያሳለፈ ሲሆን የሐረር ከነማ ከብሔራዊ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ የቻለ አሰልጣኝ ነበረ።
ፉዓድ የትምህርት ዝግጅቱም ከስፖርት ጋር የተያያዘ ሲሆን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ የመጀመሪያውን ዲግሪ ማግኘት ችሏል በአሰልጣኝነት ደረጃም ከፍተኛ የኢንስትራክተር ደረጃ ያለው የድሬ ልጅ ነው።
የድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ተጫዋች የነበረው እና በሙያ ደረጃም በተለያየ እርከን የድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅን እያገለገለ የነበረውን አቶ ዳዊት ከድር ዘከሪያ ወይም በቅጽል ስሙ ጆኒ በመባል የሚታወቀውን የክለቡ ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ አድርጓል በጥሩ ስነ-ምግባር እና ለሌሎችም ተምሳሌት የሆነ ጸባይ ያለው ጆኒ በስፖርት ዓለም ከማሳለፉ ባሻገር በትምህርት ዝግጅትም የማኔጅመንት ምሩቅ ስለሆነ ክለቡን በብቃት ይመራል ተብሎ ታምኖበታል፡ ጆኒ በድሬዳዋ ማህበረሰብ ዘንድም ተቀባይነት ያለው ሰው ነው።
ከሀትሪክ ስፖርት
@zena24now