ቸርነትህ ብዙ
ቸርነትህ ብዙ ምሕረትህ ብዙ
በጉዟችን እርዳን ጠባብ ነው መንገዱ
ድንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለእኛ
ድንቅ ነዉ ለእኛ አንተ ነህ መልካም እረኛ
አስራኤል ወደቀ እስራኤል ተነሳ (2x)
መንገዱ አልቀናውም አምላኩን ቢረሳ (2x)
የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔርን ይዞ (2x)
ምን እንዳተረፈ አውቆታል በጉዞ (2x)
አዝ==========
መንገዱ አይታክትም ጎዳናዉ የቀና (2x)
እግዚአብሔር በፊትም ከኋላሞ አለና (2x)
እርሱ በሌለበት ቢመችም መንገዱ (2x)
አቅጣጫው ወደ ሞት አይቀርም መውሰዱ (2x)
አዝ==========
በመንገዱ ዝለን ወድቀን መች ቀርተናል (2x)
የያዕቆብ አምላክ ደግፎ አንስቶናል (2x)
እግዚአብሔር ሲጠራን በቀደመው መንገድ (2x)
ጉዞአችን ወዴት ነው በሞት ለመወሰድ (2x)
አዝ==========
አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልባችን ሳለው (2x)
እስከሞት በመስቀል የወደደን ማነው (2x)
በበረሃዉ ጽናት ሲጸናብን ርሀቡ (2x)
በረከት ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ (2x)
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs