✞ ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር ✞
ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር
የአበው ቅዱሳን ምድር
ህዝቦች ሆነው ሰላምን
ኑሪልን ለዘላለም x2
አዝ
ከመጀመሪያው አብሳርሽ
ከጃንደረባው ባኮስ
በኋላም እውነትን ካስፋፋው
እስከ ሰላማ ድረስ
ወንጌልን ሰምተሽ ኢትዮጵያ
በተሰአቱ ቅዱሳን
ዛሬም ጠብቀሽ ይዘሻል
የነገው ትውልድን እንዲድን
አዝ
ብዙአላውያን ነገስታት
ሊያጠፉሽ ታትረው ቢነሱ
ሰይፍና ጎመድ ቢመዙ
ቅዱስ ስፍራሽን ሊያረክሱ
የሚጠብቅሽ አይተኛም
የምታመልኪው እግዚአብሔር
ዘላለም ላንቺ ብሩህ ነው
አይሰራም ያህዛብ ምክር
አዝ
ባጥንትሽ ብዕር አቅልመሽ
በደምሽ ቀለም ያስተማርሽ
ፊደልን ቀርፀሽ ያቆየሽ
የእውቀት ገበታን አንቺ ነሽ
ዘመንን ሰርተሽ ለትውልድ
ወንጌል የሰበክሽ በፍቅር
ተዋህዶ ነሽ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያም ሀገረ እግዚአብሔር
አዝ
በተዘረጉት እጆችሽ
እግዚኦ ባልሽው ተማጽኖ
ምህረት ሆኗል ለህዝብሽ
አምላክ ቀርቦሻል ባድኖ
ለሊት እና ቀን በምልጃ
ሰርክ እና ነገን በጸሎት
እየማለደሽ ዘወትር
ለህዝብሽ ሆኗል አብረሆት
አዝ
ወርቅ ላበደረ ጠጠር
ነገሩን አበው እንዲሉ
ጠላት በማይተብሽ መጣ
ስለሚሰበቅ መስቀሉ
እውነትን እንገልጣለን
ስላንቺ ክብር ላልሳማ
እየነደድሽ እንዳበራሽ
እየቀለጥሽ እንደሻማ
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs
ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር
የአበው ቅዱሳን ምድር
ህዝቦች ሆነው ሰላምን
ኑሪልን ለዘላለም x2
አዝ
ከመጀመሪያው አብሳርሽ
ከጃንደረባው ባኮስ
በኋላም እውነትን ካስፋፋው
እስከ ሰላማ ድረስ
ወንጌልን ሰምተሽ ኢትዮጵያ
በተሰአቱ ቅዱሳን
ዛሬም ጠብቀሽ ይዘሻል
የነገው ትውልድን እንዲድን
ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖቴ x2
አዝ
ብዙአላውያን ነገስታት
ሊያጠፉሽ ታትረው ቢነሱ
ሰይፍና ጎመድ ቢመዙ
ቅዱስ ስፍራሽን ሊያረክሱ
የሚጠብቅሽ አይተኛም
የምታመልኪው እግዚአብሔር
ዘላለም ላንቺ ብሩህ ነው
አይሰራም ያህዛብ ምክር
ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖቴ x2
አዝ
ባጥንትሽ ብዕር አቅልመሽ
በደምሽ ቀለም ያስተማርሽ
ፊደልን ቀርፀሽ ያቆየሽ
የእውቀት ገበታን አንቺ ነሽ
ዘመንን ሰርተሽ ለትውልድ
ወንጌል የሰበክሽ በፍቅር
ተዋህዶ ነሽ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያም ሀገረ እግዚአብሔር
ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖት x2
አዝ
በተዘረጉት እጆችሽ
እግዚኦ ባልሽው ተማጽኖ
ምህረት ሆኗል ለህዝብሽ
አምላክ ቀርቦሻል ባድኖ
ለሊት እና ቀን በምልጃ
ሰርክ እና ነገን በጸሎት
እየማለደሽ ዘወትር
ለህዝብሽ ሆኗል አብረሆት
ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሀይማኖት x2
አዝ
ወርቅ ላበደረ ጠጠር
ነገሩን አበው እንዲሉ
ጠላት በማይተብሽ መጣ
ስለሚሰበቅ መስቀሉ
እውነትን እንገልጣለን
ስላንቺ ክብር ላልሳማ
እየነደድሽ እንዳበራሽ
እየቀለጥሽ እንደሻማ
ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖት x2
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs