━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
ብቻ ትስቃለች
ብቻ ታለቅሳለች
.
መሆን እያማራት
ማፍቀር እያማራት
ማለፍ እያማራት ፣ የቀን መከራ ግፍ ፣
ሃዘን ቢያባብላት ፣ እንባዋ እርግፍ እርግፍ ፣
ብላ የት ነበርኩኝ
ብላ ወዴት ሄድኩኝ
አሻግራ ስታየው
በየ ጥጋጥጉ
እንባ ተከማችቶ ፣ እንባ ተወትፏል ፣
ሁሉን አስተዋለች ፣ ልቧ ለሳቅ ተርፏል ፣
ፈገግ አለችለት
አንድ የቀረ ሳቋን ፤
ይሁን አለችለች
አንድ የቀረ ሃቋን ፤
ከዛ ትሄዳለች
ከዛ ትቆማለች
መሸሽ እያማራት
ማቀፍ እያማራት
መኖር እያማራት ፤ ህይወትን እንደ ሰው ፤
መሄድ አባበላት ፤ እግሯን የት ታድርሰው ?
እንዳለ ተወችው
እንዳለ አለፈችው
.
ጀርባዋ ላይ ያለን
የመሰልቸት ጅራፍ ፤
ጡቷ መሃል ያለን
ሴት የመሆን ምዕራፍ ።
ባለበት ገፋችሁ .!
እንደ'ተራ ነገር
እንደ'ተራ ሃዘን
ታሪክ ግን ነበራት ፤ በወንድ የሚመዘን ።
ሰርታ ነበር ታሪክ
ሰርታ ነበር እንባ
ናፍቆት ያልቆረጠው
ገብቷት ያልኖረችው ፤
አሁን ባይታይም ፤ ንቃ እንደ'ሸኘችው ።
ብቻ ትስቃለች
ብቻ ታለቅሳለች
ብቻ ትሄዳለች
ብቻ ትቆማለች
ተለያይቶ መቆም
ተቃርኖ መሰለፍ
ትርጉም ይሰጣታል ፤
አሁን ከኔ በቀር ፤ ሁሉም ይበልጣታል ።
.
-----------------
ሶሎሞን ሽፈራው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
ብቻ ትስቃለች
ብቻ ታለቅሳለች
.
መሆን እያማራት
ማፍቀር እያማራት
ማለፍ እያማራት ፣ የቀን መከራ ግፍ ፣
ሃዘን ቢያባብላት ፣ እንባዋ እርግፍ እርግፍ ፣
ብላ የት ነበርኩኝ
ብላ ወዴት ሄድኩኝ
አሻግራ ስታየው
በየ ጥጋጥጉ
እንባ ተከማችቶ ፣ እንባ ተወትፏል ፣
ሁሉን አስተዋለች ፣ ልቧ ለሳቅ ተርፏል ፣
ፈገግ አለችለት
አንድ የቀረ ሳቋን ፤
ይሁን አለችለች
አንድ የቀረ ሃቋን ፤
ከዛ ትሄዳለች
ከዛ ትቆማለች
መሸሽ እያማራት
ማቀፍ እያማራት
መኖር እያማራት ፤ ህይወትን እንደ ሰው ፤
መሄድ አባበላት ፤ እግሯን የት ታድርሰው ?
እንዳለ ተወችው
እንዳለ አለፈችው
.
ጀርባዋ ላይ ያለን
የመሰልቸት ጅራፍ ፤
ጡቷ መሃል ያለን
ሴት የመሆን ምዕራፍ ።
ባለበት ገፋችሁ .!
እንደ'ተራ ነገር
እንደ'ተራ ሃዘን
ታሪክ ግን ነበራት ፤ በወንድ የሚመዘን ።
ሰርታ ነበር ታሪክ
ሰርታ ነበር እንባ
ናፍቆት ያልቆረጠው
ገብቷት ያልኖረችው ፤
አሁን ባይታይም ፤ ንቃ እንደ'ሸኘችው ።
ብቻ ትስቃለች
ብቻ ታለቅሳለች
ብቻ ትሄዳለች
ብቻ ትቆማለች
ተለያይቶ መቆም
ተቃርኖ መሰለፍ
ትርጉም ይሰጣታል ፤
አሁን ከኔ በቀር ፤ ሁሉም ይበልጣታል ።
.
-----------------
ሶሎሞን ሽፈራው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA