#ETA
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ጉዳዩ፦ በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የመውጫ ፈተና በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ፈተናውን በዓመት ሁለት ጊዜ መሰጠት እንዳለበት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ይደነግጋል፡፡
ስለሆነም በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ከወዲሁ ብቁ እጩ ተፈታኞች ለማጣራት እንዲቻል ዘንድ በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከዚህ ደብዳቤ አባሪ በተደረገ ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
✅ University News ✅