╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... #መጅኑኑ_ለይላ❤️🔥🧕......
✎ ፀሐፊ፦ ሷሊህ አስታጥቄ
✎አዘጋጅ፦Mukerem
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
በ @Hafu_islamic_posts የተዘጋጀ
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
የጥርጊያው ዱብዳ
╚════•| ✿ |•════╝
ቀይስ ከአብሮ አደጉ ጋር በመንደሩ እየተንቀሳቀሰ አንድ ጥርጊያ ላይ ሲደርሱ ድንገት ውዝ ሆነ። ወሬውን አቆመ:: ጓደኛው ድንገት ዝም ማለቱ ገርሞት ወደሱ ሲዞር ልጁ እይታውን ወደ አንድ አቅጣጫ አፍጥጦ ሃውልት ሆኗል። ወደሚመለከትበት አቅጣጫ ሲዞር ለይላን ከሩቅ አያት። ቀይስ ዓይኑን ባለበት እንደተከለ ከአገጩ ብቻ ወደ ጓደኛው ዘምበል ብሎ ለይላ ናት አለ በለሆሳስ፡፡ አዎ አለ ጓደኛው ለይላ ጉፍታዋን እነ ቀይሰ መንደር ስትደርሰ ፊቷን እንደምትሸፍንበት ታውቅ ነበር። ግን ድንገት ተቀደመች፡፡ እሷም በጥርጊያው በዚያኛው ገጥ ቀጥ ብላ ቆማለች። የደነገጠችው ቀይስን ሰላየችው ሳይሆን ቀይስ ስላያት ነበር። ቀድሞውኑ እንዲያገ አልፈለገችም። ስለ ሰሜቱ አታውቅም፡፡ ፊት ቢነሳኝሰ የሚል ሃሳብ ገብቷታል። የከተማዎቹን ኮረዶች ውበት ታውቃለች፡፡ የትዳር ጥያቄ ሲመጣላት እንኳን ቶሎ ትዝ የሚላት ቀይስ ቢሆነሰም ትዳር ድረስ እንደማትደርስ ታስባለች። አባቷ ለአባቱ ያለውን ጥላቻ ማወቋና ቀይስ በከተማ ሴት ሊጠለፍ መቻሉን አብዝታ ማሰቧ ያመጣባት ፍርሃት ቀመስ እምነት ነበር።
ቁመቷ አጠር ቢልም ሁለመናዋ ጎምርቷል። ፊቷ ድምቀትን ከጨረቃ የምትዋስ እንቡጥ ፅጌሬዳ መሰሏል፡፡እጅጉን አምሮባት፣ የልጅነት ወዟ ሳይጠፋ ወጣትነት እየተዋሃዳት ነው፡፡ ትንሿን ለይላም አላጣባትም፡፡ ግን አዲስና ሌላ የቁንጅና ሰገነት ላይ የምትንጎራደድ ለይላም ጨምሮ አጊንቶባታል። ልዩ መስህብ የማይጠገብ እይታ፡፡
የትዝታ ሞገድ ቀድሞ የነበረውን የተቀበረ ፍቅር ወጀቡን አክሎ መላ ሰውነቱን ለይላ ባህር ውስጥ ሲዘፍቀው ታወቀው᎓᎓ ከልጅነት እስከ እውቀት ያለውን የሷና የሱ የወዳጅነትና የአብሮ አደግነት ትውስታ ከምናቡ ቋት ጨልፎ አዲስ ፍቅር ከሚሉት ጦስ ጋር ኣዋህዶ ልቡ ውሰጥ ሲሸቀሸቅ ተሰማው፡፡ ለይላ አላት፡፡ ቀይስ አለችው:: ተቀራረቡ ዝም ብለው ተያዩ። መተቃቀፍሞ መነካካትም አይታሰብም የሁለቱም ጓደኞች ታዛቢ ሆነው ተሰይመዋል። በጣም አድገሻል ውብ ሆነሻል አላት፡፡ አንገቷን ደፍታ እና ብቻህን እንዲያምርብህ ነበር ፍላጎትህ ብላ ተሸኮረመመች፡፡ በጥቂቱም ቢሆን አፍ የፈቱ ያህል ተሰምቷቸው እፎይ አሉ፡፡ ያን ቀን ጥቂትም ቢሆን አውርተው
ተለያዩ።
ቀይስና ለይላ ከቀናት በኋላ ወደ ድሮው ቀረቤታቸው ተመለሱ፡፡ ሁለቱም አድገዋል። ነገራቶችም ጠጠር እያሉ ነው፡፡ የልጅነት የነበረው ፍቅር አዳዲስ ስሜቶችን እያስተናገደ ከበፊቱ እየባሰ ነው። በራሳቸው ላይ አዳዲስ ነገሮችን ያስተውሉ ይዘዋል። መለያየት እየከበዳቸው ናፍቆትም እየታወቃቸው ሄዷል። ሁለቱም በየፊናቸው የሚሰማቸውን ስሜት አዳፍነው እንደ ልጅነታቸው ይጨዋወታሉ፡፡ ባይሆን አሁን ነፍስ አውቀዋልና መገናኘታቸው የቤተሰብ ፀብ እደሚያጋግም ተገንዝበዋል። እናም የሚገናኙት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው ::
የቀይስ አባት ቀይስን ለመዳርና ትመጥነዋለች የሚላትንም ሴት ለመምረጥ እየተንጎዳጎደ ነው። ምንም የንግድ ጉዞው ቢራዘም ሳያገባ ላይልከው ለራሱ ቃል ገብቷል። ቢሆንም ለቀይስ አልነገረውም። ቀይስ እየወጣ ውሎ ይገባል፡፡ ለይላም ተደብቃ እየወጣች ከቀይስ ጋር ትንሽ ቆይታ ትመለሳለች። የቀረውን ቀን ቀይስ ከጓደኞቹ ጋር ይውላል፡፡ ሰለ ለይላ ይጠይቃቸዋል፡፡ ያወራቸዋል። በጀርባው ተንጋሎ ስለሷ ያስባል፡፡ ያሁኑ ውዴታ ከልጅነታቸው ልቋል። ሁለቱንም ብቻቸውን ያስቃቸዋል። በህልማቸው ያቀራርባቸዋል። ስንኝ ያስቋጥራቸዋል ወደፊትን ያሳስባቸዋል። ሁሉንም እያስረሳቸው መጥቷል። በተለይ ቀይስ ነጋዴ መሆኑን እንኳ ማስታወስ አይፈልግም፡፡ አሁን ላይ እንደ ቀደሙ ለይላ እያለች የበኑ ዓሚርን ጎሳ ጥሎ መውጣት አይታሰብም ። የእስከዛሬው ያለሷ ያሳለፈው ያ ሁሉ ጊዜ ከንቱ መሰለው። አሁን ላይ እሷን በማየት ጥሙን ይቆርጣል፡፡ ይጠግባል። ይደሰታል፡፡ አዲሱ የገነፈለ ፍቅር ድንቅ ገጣሚነቱን ሊያፈነዳው ቀጠሮ ይዟል፡፡
🔥Is Continued… … … …
❤️ℓιкє..ιѕ ιмρσятαит......