╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... #መጅኑኑ_ለይላ❤️🔥🧕
......
✎ ፀሐፊ፦ ሷሊህ አስታጥቄ
✎አዘጋጅ፦Mukerem
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
በ @Hafu_islamic_posts የተዘጋጀ
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
የተዳፈነው ፍቅር
╚════•| ✿ |•════╝ቀናት በተቆጠሩ ለይላ እና ቀይስ ይበልጥ በተቀራረቡ ቁጥር በልባቸው ውሰጥ ተዳፍኖ የነበረው ፍቅር አመዱን ገልጬ ካልወጣሁ እያለ ነው፡፡ በዚያ ፍጥነት ይሆናል ብለው ባልገመቱት መንገድ ተጋጋመ። መተያየታቸው ለኳሽ ሆኖ በሁለቱም ልብ ውስጥ ፍቅር ተያያዘ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ይፋቀሩ እንጂ ፍቅራቸውን አልተነጋገሩም። ሁለቱም ፍቅርን ያህል ነበልባል አዘል ፍም ታቅፈው እየተለበለቡ ነው:: ችላ አይሉት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ከቃጠሎው ጋር የተጣመረው የመሃባ ስቃይ ደሰታንም አምቋል፡፡ ይዘውት አይቆዩ ደግሞ ፍጅቱ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚጠዘጥዝ ነው፡፡ ግራ የገባ ነገር፡፡
ሁለቱም ተመሳሳይ ስቃይ እየተጋሩ ነው፡፡ ቢሆንም እንዳይታወቅባቸው ይጥራሉ። በተለይ ከጓደኞቻቸው ጋር ሰብሰብ ብለው ሲጨዋወቱ በከፍተኛ ሁኔታ ስሜቶቻቸውን ለመደበቅ ይሞክራሉ፡፡ ሁለቱም ያፈኑት የሚንተከተክ ፍቅር ይፋ ባይታይም እንፋሎቱ ግን በአቅራቢያቸው ላሉት ምልክት እየሰጠ ነው።
በእርግጥ ቀይስ ለአንዳንድ የቅርብ ጓደኞቹ ስለ ስሜቱ አጫውቷቸው ነበር፡፡ ፍቅሩን ለሷ ለማካፈል ያለውን ፍላጎትም አዋይቷቸዋል፡፡ ግን አንዱ ይቅርብህ እጁን ለትዳር መጠየቅ እንጂ ፍቅር ይፋ ማውጣት ትርፉ ውርደት ነው፡፡ ሌላኛው አትሆንህም አባትህና አባቷ ፀበኛ ስለሆኑ ላይድሩህ ነገር አትልፋ፡፡ ይባሱን ስቃይ አትግዛ ደግሞ እሷ ባትወድህና ምላሿ ሚያደማህ ቢሆንስ ምን ሊውጥህ ነው? ደግሞ ቆፍጠን ማለትና ወንድ ወንድ መሽተት፤ ከቻሉ አንዷን አግብቶ መኖር እንጂ ለአንዲት ኮረዳ የምን መብረክረክ ነው? እያሉ ኩም አድርገውታል፡፡ እሱ ግን እሷን እንጂ ሌላማ አይደረግም እያለ የመፍትሄ ሃሳብ ነው ያለውን እየዘረዘረ ይከራከራቸዋል፡፡ እነሱም ይመልሱለታል፡፡ የምታስበው ሁሉ ግራ ነው ይሉታል፡፡ ሲታክታቸው ጥለውት ይሄዳሉ።
ቀይስ አይገባችሁም እያለ ይጮሀል።እነሱንም ፍቅር እንዲደቁሳቸውና እንዲያዩት ይመኛል።
አባት ሙለወሕ በዚያ በኩል ሚስት መፈለጉን አጧጡፎታል፡፡ አንድ ቀን ምሽት ላይ ቀይስ ጠጋ ብሎ ልጄ በል እንግዲህ ወደ ንግዱ ከመሄድህ በፊት ልድርህ ነው አለው።ቀይስ በደሰታ ፊቱ ፈካ፡፡ አባትም በልቡ ለካ ልጄ ባይናገርም ይፈልግ ኖሯል ብሎ ደስ አለው። አስከትሎም ውብና ወላድ የሆነች ቆንጆ ኮረዳ ነው የምድረህ! አንተ ያየሃት ካለች ወዲህ በል! ካልሆነ ግን እኔ ካየኋቸው ላስመርጥህና ቶሎ ሽማግሌ እንላክ አለ። ቀይስ ያኔ አፉ ተሳሰረ፡፡ እንዴት ሽሸጉን ያውጣው? የሱ አባትም ቢሆን የለይላን አባት ይሄ ስም አጥፊ እያለ ሲወቅሰው ደጋግሞ ሰምቷል፡፡ ለይላን ዳርልኝ ሊለው አሰበና፤ አንተ ቅዠታም ብለህ ብለህ ከጠላቴ ጋር ልታዛምደኝ ያምርሃል ብሎ የሚያንባርቅበት መሰለው። አባቱን ደግሞ ይወዳልም ይፈራልም፡፡እናም አንገቱን ደፋ።
አባትሞ ያየው የለም ማለት ነው ብሎ የእገሌን ልጅ አይተሃታል ቁመቷ ብትል ውበቷ በዛ ላይ የነ እገሌ ዝርያ ናት፡፡ እህቶቿም ሆኑ እናቷም ወላዶች ናቸው፡፡ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ የሚባለውኮ እውነት ነው። እናቷ ወላድ ከሆነች ልጅቷም እንደዛው ነው የምትሆነው ይለዋል። ቀይስ ግን ለይላ ካላለው በስተቀር የመቀበል ፍላጎቱ የለውም፡፡ አይ አትሆንም ደስ አትለኝም አለ ቀይስ ፊቱን ጭፍግግ አድርጎ።ከአባቱ ምርጫ ውስጥ ለይላ ልትኖር ትችላለች የሚል የተስፋ ጭላንጭል ነበረው። ግን አልሆነም፡፡
ምሽቱን አባት የመንደሯን የደረሱ ሴቶች ስምና መረጃ እየዘረዘረ አንዷን እንዲመርጥ ቢለፋም ቀይስ አንዷንም እሷ ትሁን በቃ ብሎ ሊሰማማ አልቻለም፡፡ አባት ጨንቆት የምትወዳት ካለች ንገረኝ አለ። ቀይስ አሁንም ዝም አለ፡፡ ሶሪያ ወይም ዒራቅ ሳለን አንዷ ልብህን ወስዳዋለች መሰል። ከዚያ ነው እንዴ የምትፈልገው? እኔኮ የመንደራችን ሴቶች ይሁኑ ብዬ የማስመርጥህ አኗኗራቸው ከአኗኗርህ ጋር ስለሚጣጣም አትቸገርም ብዬ ነው እያለ ይለፈልፋል።ቀይስ ግን ልቡ አልተገኘም::ይሄኔ አባትየው ታክቶት ጥሎት ሄደ።ሙለወሕ የቀይስን እናት እስኪ አንቺን ከሰማ የሚፈልገውን ጠይቂው ብሎ ላካት። እናትም ወደ ቀይስ ሄዳ ፀጉሩን እየዳበሰች በፍቅር ወግ የማረከችው ሴት እንዳለች ጠየቀችው። ቀይስ ግን አሁንም ሊናገር አልፈለገም፡፡ መጨረሻ ላይ በቃ እራስህ ፈልግና እገሊትን ዳሩኝ በለን፡፡ በመንደሩ ወጣ ወጣ እያልክ ሴቶቹን እያቸው አለችው። ይሄን ጊዜ ቀይስ ተስማማ። ወትሮም ጊዜ መግዣ ምክንያት ነበር የሚፈልገው:: ጉዞህ መራዘም የለበትም ቶሎ አሳውቀን እያለችው እናቱም ሄደች፡፡
ቀይስ አሁንም ከለይላ ጋር ይገናኛል፡፡ በማህበር ከጓደኞቻቸው ጋር ተሰብሰበው በጋራ የሚጨዋውቁበት ጊዜም ይበረክታል። በተለይ ፍቅራቸውን አምቀውታል። ቢሆንም ግን ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ነገራቶችን በማስተዋል ለመረዳዳት ይሞክራሉ፡፡ በተለይ ለይላ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመቀራረብና እሱን ጣል ጣል በማድረግ በቅናት የሚሆነውን የቆሪጥ እያየች ለሷ ያለውን ፍቅር ለመለካትና ድምዳሜ ላይ ለመድረሰ ትሞክራለች፡፡ ምልክቶችሞ ታያለች፡፡ ሆኖም የልቧ አይደርስላትም።በዚህ አድራጎታቸውና በየልባቸው ያለውን ፍቅር ለመለካት በሚያደርጉት ጥረት በጓደኞቻቸው ይፋቀራሉ በሚል ቢጠረጠሩም ያፈጠጠ ነገር ስለሌለ አፍ አውጥቶ መናገር ከባድ ሆኗል።
🔥Is Continued… … … …
❤️ℓιкє..ιѕ ιмρσятαит......