╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......📓መጅኑኑ_ዲያሪ📓......
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 8⃣
╚════•| ✿ |•════╝
የልጁን እናት መድሃኒት ከውጪ ለማስመጣት የኔ እናት ትረዳናለች ብዬ አሰብኩኝ።እናቴ ከዚህ ከሄደች ብዙም ባትቆይም ግን ከማዳሟ ጋር የተለየ ቁርኝት እንዳላት በላከችው የደብዳቤ ፖስታ ነግራን ነበር።በዚያን ወቅት እንደአሁኑ ብዙም ስልክ አይታወቅም ነበር።ስለዚህም ከእናቴ ጋር የምንገናኘው በረዥም ጊዜ ልዩነት በምትልካቸው ደብዳቤዎች ነበር።የመድሃኒቱ ጉዳይ ደግሞ አፋጣኝ እንደሆነ ሲናገሩ ስለሰማሁ ለእናቴ በደብዳቤ ማሳወቁ ብዙም ጥቅም እንደሌለው ስረዳ ሀሳቤን እርግፍ አድርጌ ተውኩት።ዛሬ ከትምህርት የተባርኩበት ማግስት በመሆኑ ለአክስቴ እንዳመመኝ ነግሬ ዋሽቼ ቀረሁ።ምክንያቱም እንደተባረርኩ ካወቁ ለኔ ጥሩ አይደለም።በዚያ ላይ የባሏን ሽኩቻ ችላ፣ያለባት የኢኮኖሚ ቀውስ ሳያግዳትና ድህነቷን ሰበብ ሳታደርግ እኔን ከእህቷ(ከኔ እናት) ተቀብላ ከልጇ ሳታሳንስ በአንድ ጎጆ የምታኖረኝን አክስቴን ማስከፋት አላሻኝም።እለቱም ጁመዓ ስለነበር ገላዬን ተጣጥቤ ወደ መስጂድ ሄድኩ።አክስቴንና ባሏን ጨምሮ የሰፈሩ ሰው በኔ ሁኔታ ተገርመው አይናቸውን ጥለውብኛል።ወደ መስጂድ ስገባ ድባቡ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቴ በእጁ ይዞኝ የመጣንበትን ጊዜ በጨረፍታም ቢሆን አስታወሰኝ።አባቴን ሳስብ እንባዬ ቅርር ይላል።አንዳንዴ የሱ መሞት ለኛ መከራ መምጣት መነሻ መሆኑን ሳስብና ከሱ ሞት በኋላ ዝቅ ያልንባቸውን ገጠመኞች ሳስብ ይከፋኛል።ወደ መታጠቢያው ወይም ኡዱዕ ማድረጊያው ሄጄ ተቀመጥኩ።ከአጠገቤ የተቀመጡትን ባለ ነጭ ፂም አባት ኡዱዕ አደራረግ በቀስታ እየተመለከትኩ እንደርሳቸው ኡዱዕ አድርጌ ከመስጂዱ ገባሁ።በመስጂዱ የተገኙ ሰዎች ገሚሱ መቁጠሪያቸውን እያንቋጨሉ በተመስጦ ውስጥ አፋቸውን ያጉተመትማሉ።ከፊሎቹ ደግሞ ቁርዓን ይቀራሉ።መስጂዱ ደግሞ በመልካም የሽቶ ጠረን ተሞልቷል።እኔም ከአንዱ ጥግ ሄጄ ቁጭ ብዬ አይኔን መቀላወጥ ያዝኩኝ።ቀስ በቀስ መስጂዱ በሰዎች መሞላት ጀመረ።አንድ በእጃቸው ሽመል የያዙና ከአናታቸው ላይ ጥምጣም እና ኮፍያ የደፉ አባት ከወንበራቸው ላይ ቁጭ ብለው ንግግር (ኹጥባ) አደረጉ። የሳቸው ንግግር ከተጠናቀቀ በኋላ የስግደት ስነስርዓቱ ተፈፅሞ ሰዉ ከመስጂዱ ለመውጣት መጋፋት ሲጀምር እኔ ባለሁበት ደገፍ ብዬ ቁጭ አልኩኝ።ሰዉ ከተረጋጋ በኋላ ወደ ቤት ተመልሼ ልብስ ቀይሬ ወደትምህርት ቤት ሄድኩኝ።ወደትምህርት ቤት የሄድኩትም ለሁለት ነገሮች ነበር።ልጅቷን ለማየትና ርዕሰ መምህሩን እግሩ ስር ተደፍቼም ቢሆን ለመለመን ነበር።የትምህርት ቤቱ ጥበቃዎችም ስለሚያውቁኝና የመጣሁበትን ነገር በዝርዝር ነግሬያቸው ወደ ርዕሰ መምህሩ ቢሮ አንኳኩቼ ገባሁ።እንደገባሁም ከጠረጴዛውና ከመቀመጫቸው ተሽከርካሪ ወንበር መሀል ያሉ እግሮቹን ፈልጌ እግሩ ስር ድፍት ብዬ ስለእናቴና አሁን ስለምኖርበት ሁኔታ ጨምሬ ከተባረርኩ ስለሚገጥሙኝ ችግሮች እየተንሰቀሰቅኩኝ ነገርኩት።ምክንያቴ ደግሞ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ አሞኛል ብዬ በድጋሚ መወሽከት ስለማልችል ነበር።"አንተ ልጅ እግሬን ልቀቀኝና ተነስ"በለቅሶዬ ያዘነ በሚመስል ድምፁ ተቆጣኝ።እኔም ፊት ለፊቱ ካለው ወንበር ጋር ሄጄ እንባዬን በሹራቤ እጅጌ እየጠረግኩ አንገቴን ደፍቼ ቆምኩ።
ብሎ እንደ እንግዳ በእጆቹ ወደ ወንበሮቹ አመላከተ።
ለንቦጬን እንደ ህፃን ከአገጬ ላይ ዘረገፍኩት።
ብሎ ከመሳቢያው ውስጥ ወረቀት አውጥቶ ስሜን ፅፎ አስፈረመኝ።እኔም አመስግኜ በሩን ከፍቼ ልወጣ ስል "ኦማር" ብሎ ጠራኝ።
ደነገጥኩ።
አለኝ እንደ አባት በሚያሳሳ አስታየት እያየኝ።
ብዬ ወጣሁ።ንግግሩ ልቤ ድረስ ሰርጎ ተሰማኝ።በንግግሩ እየተብሰለሰልኩኝ ጊቢውን ለቅቄ ወጣሁኝ።ከጊቢው ውጪ ቆሜ ስለ ንግግሩ እያሰብኩኝ ተማሪዎች መውጣት ሲጀምሩ ከሃሳቤ ወጥቼ በአይኔ ልጅቷን መጠባበቅ ጀመርኩ።የአክስቴ ልጅ መርየምን ሳገኛት የደስ ደሱን ነግሬያት ቤት እመጣለሁ ብያት ወደ ቤት እንድትሄድ አደረግኩኝ።ተማሪዎች በጠቅላላ ወጡ።ነገር ግን ልጅቷን እስከ አሁን ድረስ አላየኋትም።በስተመጨረሻም የትምህርት ቤቱ በር ሊዘጋ ሲል ጀለብያውን የሰጠኝ ልጅ አቅፏት እየተሯሯጡ ወጡ።ባየሁት ነገር ደሜ ፈልቶ ተከተልኳቸው።በየመንገዱ ያዝላታል ይሳሳቃሉ።የተከዳሁኝ ያህል ተሰማኝ።ወደ አንድ ሰፈር ሲገቡ መከተሌን አቁሜ በንዴት እንደጦፍኩ ወደ ቤቴ ብቻዬን እያወራሁ ተመለስኩኝ።
ይቀጥላል .....❤️🔥
Like90+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫