.እስቲ ላፍቅር ደግሞ
ለብቻ መጓዙ ካልተመቸው ጎኔን
የነጠላ ኑሮ ካበዛው ህመሜን
ታግዬው ካልቀናኝ የህይወት ጎዳና
እስቲ ልሞክረው ደግሞ ላፍቅርና
ትዕቢቴን ቀንሼ፤
ከሰው ተናንሼ፤
ልኑር እንደሌላው፤
ልቤን እንዲደላው፤
ይፈወስ እንደሆን የያዘኝ አባዜ
ያወጣኝ እንደሆን ነቅሎኝ ከትካዜ
እንዳዲስ ካበበ የመኖር ጉጉቴ
ይሻል እንደሆነ ነገ ከትላንቴ
ጎደሎው ከሞላ ጠማማው ከቀና
እስቲ ልሞክረው ደግሞ ላፍቅርና
👉@fiyam_etaya
ለብቻ መጓዙ ካልተመቸው ጎኔን
የነጠላ ኑሮ ካበዛው ህመሜን
ታግዬው ካልቀናኝ የህይወት ጎዳና
እስቲ ልሞክረው ደግሞ ላፍቅርና
ትዕቢቴን ቀንሼ፤
ከሰው ተናንሼ፤
ልኑር እንደሌላው፤
ልቤን እንዲደላው፤
ይፈወስ እንደሆን የያዘኝ አባዜ
ያወጣኝ እንደሆን ነቅሎኝ ከትካዜ
እንዳዲስ ካበበ የመኖር ጉጉቴ
ይሻል እንደሆነ ነገ ከትላንቴ
ጎደሎው ከሞላ ጠማማው ከቀና
እስቲ ልሞክረው ደግሞ ላፍቅርና
👉@fiyam_etaya