❤️🔥ከፍቅር በላይ💔
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።🤷♂
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም😕
እኔስ አልወድሽም።
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው😊
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደውስጥ ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።🥰
እርግጥ ነው አልክድም
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።❤️🔥
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ #አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።😡
እርግጥ ነው አልክድም
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።😢
እርግጥ ነው አልክድም
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው💗
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው🙄
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
ይህንም አልክድም
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን #አልወድም😒
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን #ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
ይህ ፍቅር አይደለም❤️🔥
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ #ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው #ያፈቀረኝ በዪ🥺
ከመውደድ በላይ ነው የወደድከኝ በዩ።
ሼር🙏
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።🤷♂
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም😕
እኔስ አልወድሽም።
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው😊
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደውስጥ ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።🥰
እርግጥ ነው አልክድም
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።❤️🔥
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ #አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።😡
እርግጥ ነው አልክድም
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።😢
እርግጥ ነው አልክድም
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው💗
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው🙄
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
ይህንም አልክድም
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን #አልወድም😒
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን #ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
ይህ ፍቅር አይደለም❤️🔥
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ #ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው #ያፈቀረኝ በዪ🥺
ከመውደድ በላይ ነው የወደድከኝ በዩ።
ሼር🙏