🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰3️⃣0️⃣
የመጨረሻ ክፍል
በዚህ አመታት ውስጥ አንድም ቀን ምን ጎደላችሁ ምን ላሟላላችሁ ብያቸው አላውቅም እንደውም በተቃራኒው በሄድኩ ቁጥር ሽሮ በርበሬ ተቀብዬ እመለሳለሁ ይሄን ያህል አመት እናቴ አንድም ቀን አናግራኝ አታቅም እንደጠላት ነው ምታየኝ ይባስ ብላ ሊገለኝ ነው ድረሱልኝ ብላ ጮሀ አሳስራኝ ባለቤቴ ናት ያስፈታችኝ እኔ ይሄን ያህል አመት ስቆይ ቋሚ ስራ እንኳን የለኝም አንዱጋ ስገባ በሆነ ምክንያት ያባሩርኛል ሌላውምጋ እንደዛው እኔ ከማንም በላይ ነው ምሰራው ለጉልበቴ አልሳሳም ስራ አልመርጥም እንደዛም ሆኖ ግን ሊሳካልኝ አልቻለም ይሄን አመት ስኖር ቋሚ ጓደኛ እንኳን የለኝም ማንም ከኔጋ ጓደኛ ለመሆን አይፈልግም እናቴ ቀድማ በየሰፈሩ ምታወራው ምን እንደሆነ አላቅም ባለቤቴጋ ስመጣ ሁሉም ፊት ይነሱኛል እናቴጋ ስሄድ ጭራሽ ስታየኝ ደሟ ነው ሚፈላው ልጆቼ እናታቸው ቤት ኪራይ ሲደርስባት ስትጨናነቅ ሲያዩ ሁሉም የነሱ ጓደኞች የራሳቸው ቤት እየኖሩ የራሳቸው ክፍል እያላቸው እነሱ ግን አንድ ክፍል ቤት ውስጥ ታፍነው መኖራቸውን ሲያዩ በኔ ይናደዷል።
እንደ አባት መከበር ምን እንደሆነ አላቀውም እንደውም በተቃራኒው ነው ድንገት ስልክ አንስተውልኝ ልመጣ ነው ካልኳቸው ቤት ውስጥ የታጠበም ያልታጠበም ልብስ ተከምሮ ይጠብቀኛል ለሁለት ለሶስት ቀን ያንን ልብስ አጥቤ ስጨርስ ወደደቅረ ዘይት እመለሳለሁ።
እንዴት ናችሁ ለማለት ስልክ ስደውል በልመና ነው ሚያነሱልኝ እኔ እነሱጋ ስሄድ ሁሉም ቁጭ ብለው እንደህፃን ይሄን አምጣ ይሄን ስጠኝ የምባለው እኔ ነኝ እረፍት አጣሁ መሸሸጊያ ቸገረኝ አርፌ ደብረ ዘይት ቁጭ ስል በጣም ይርበኛል ዱቤ መጠየቅ ያሳፍረኛል እነሱጋ ቢያንስ ጠግቤ እንኳን እበላለሁ እዛ ልቀመጥ ብዬ ስሄድ ደሞ ባለቤቴም ልጆቼም ለምን አትሰራም እማዬ እንደዚህ እየለፋች ውላ ስትመጣ አንተ ቁጭ ብለህ ስትጠብቃትኮ ሞራሏ ይነካል ይሉኛል።
ከሱ በላይ በጣም ውስጤን ሚነካው ምን መሰለሽ የባለቤቴ ጓደኞች ሁሉም ባሏን ፈትታ ብቻዋን እንደምትኖር ነው ሚያቁት ባለቤቴ ደሞ በጣም የሰው መውደድ ስላላት ብዙ ሰው ቤት ይመጣል ልክ ጓደኞቿ ከመጡ እነሱ ተጫውተው ጭስኪሄዱ ድረስ አንተ ወደ ውጭ ውጣ እባላለሁ ጓደኞቿ ወንዶችም ሴቶቹም ናቸው በተለይ ወንዶቹ ስራ ቦታ በደንብ ስለሚያግዟት ስለሚሸከሙላት ልጆቼም ይወዷቸዋል እሷም ለነሱ ትልቅ ክብር አላት ታዲያ እሁድና ቅዳሜን ብዙ ጊዜ ይመጣሉ አጋጣሚ ሆኖ ምግብ ቀርቦልኝ እየበላሁ ጓደኞቿ መጣን ካሉ ቶሎ ውጣ እነሱ ሲሄዱ ትበላዋለህ እባላለሁ ግን ስመለስ አስታውሰው ካላቀረቡልኝ ፆሜን ነው ማድረው።
ሶስት አራት አይነት ምግብ ተሰርቶ
ስመለስ ግን እቃው እንኳን ሳይነሳሳ ለኔ ምንም ነገር ሳያስቀሩልኝ ነው ሚጠብቁኝ።
አሁን አሁን እዚህ ምድር ላይ ለምን እንደምኖር አላውቅም ወንዱ ልጄ ቀጣይ አመት ከunversty ይመረቃል ሴቷም ከኮሌጅ ቀጣይ አመት ትመራቃለች ወንዱ ልጄ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው ልክ እያደገ የእናቱን እንግልት እያየ ሲመጣ ድንገት የትምህርት ቤቱ ሰቃይ ተማሪ ሆነ ማትሪክንም ሚኒስትሪንም ሰቅሎ ነው ያለፈው በልጆቼ ስኬት ላይ የሆነ አሻራዬን ባሳርፍ ብዬ እመኛለሁ ግን ቅንጣት ታክል እነሱን መርዳት አልችልም በተቃራኒው እንደውም እነሱ ናቸው እኔን የሚረዱኝ።
አሁን እዚህ ላይ መናገር ማልችላቸው ብዙ ስቃዮች አሉ በህይወቴ ውስጥ አድርጌው የተደሰትኩበት አንድ ነገር የለም እኔን ላለማጣት መስዋትነት የሚከፍል ወዳጅ የለኝም ከልጆቼጋ አብሬ ስለማልኖር አባት የላችሁም እንዴ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም አዎ ነው ሚሉት የልጆቼ ጓደኞች ምን አይነት እንደሆኑ አላቃቸውም እነሱም አያቁኝም።
ልጆቼጋ ድግስ ወይ የሆነ ፕሮግራም ካለ እኔ እዛ ፕሮግራም ላይ መገኘት አልችልም ምናልባት ካለፈ ቡሀላ ሰው ሲበተን ነው መሄድ ምችለው ።
ቢያንስ ወደ አምስት ጊዜ እራሴን ለማጥፋት ሞክሪያለሁ ግን ይመስለኛል ፈጣሪም የኔን ነፍስ ተፀይፏት መሰለኝ ሊሳካልኝ አልቻለም ደብረ ዘይት ሄጄ ማታ ቤቴ ገብቼ tv የለ ሬድዮ የለ እንዲሁ መብራትም ምንም ሳላበራ ጉልበቴን አቅፌ ቁጭ ስል ጭንቅላቴ ውስጥ እራስን ማጥፋት ሚለው ነገር ይመላለስብኛል።
ነገ የልጆቼ ምርቃት ላይ እንኳን መገኘት እንደማልችል ሳስበው ያመኛል ኑሮ ሚባለው ነገር ግሽግሽ ያደርገኛል።
ወንድሞቼ ልሙት ልኑር አያውቁም በእርግጠኝነት እነሱ ዛሬ ምን የመሰለን ኑሮ እየኖሩ ነው።
እኔ ግን...
ብቻ በቃ አንዳንዴ የተሰጠን እድል አንዴ ብቻ ሊሆን ይችላል
ደሞም አንዴ መንገዳችንን እድላችንን ለሰበሩብን ሰዎች መቼም ቢሆን እድል መስጠት አያስፈልግም እኔ እናቴ ገና በልጅነቴ ካባቴ ነጥላ ገጠር ወስዳ ስጥለኝ የመጀመሪያውን እድሌን ቀበረቸው እንደምንም አድጌ ህይወት ስጀምር ደሞ ና እኔ ነፃ መሬት ልስጥህ ቤት ስራ ብላ ሁለተኛውን እድሌን ቀበረችው ።
በመጀመሪያው ካባቴና ከወንድሞቼጋ እንዳላድግ ማድረጓ ሳይበቃ ደገመችና ከልጆቼጋ አንድ ቤት ውስጥ ያገኘነውን እየበላን ትኩሳችንን እየጠጣን እንዳልኖር አደረገችን።
መቼ እራሴን ሞቼ እንደማገኘው አላቅም ደም ማስተፋቱ ተባብሶ ቀጥሎብኛል በተለይ እናቴን አይቻት ስገባ ባፌም ባፍንጫዬም ደም ነው ምተፋው
እንዲሁ ስላልሞተ ብቻ ሚኖር ሰው ህይወቱ በስቃይ ተጀምሮ በስቃይ የተቋጨ በምድሩም በሰማዩም የተጠላ ሰው ታውቂያለሽ ተብለሽ ከተጠየቅሽ ስለኔ ማውራት ትችያለሽ እኔ አለሁ።
ለሁሉም ሰው ማለት ምፈልገው ህይወታችን ውስጥ ተላላ መሆን አያስፈልግም ቸልተኝነትና ሞኝነት ሲበዛ ዋጋ ያስከፍላል ቆራጥ መሆንን መለማመድ አለብን ከህይወታችን መውጣት ያለባቸውን ሰዎች ዛሬውኑ ማስወጣት እንጂ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም ይሄንን ሁላ እንዲፃፍ ያደረኩት የሆነ ቀን ላይ ቤቴ ውስጥ ብሞት እንኳን እሬሳዬ በስብሶ ሲሸታቸው ካልሆነ ማንም እንደሞትኩ አያቅም ማንም የት ጠፍተህ ነው ብሎ ሚጠይቀኝ የለም ።
ማን ያቃል ቢያንስ እንደዚህ አይነት ታሪክ ያሳለፈ ሰው ነው ተብሎ መወራቱ ለኔ ንልቅ ቁም ነገር ይሆናል........
ፅሁፉ ተፈፅሟል
የሰውየው ህይወት ደሞ ይቀጥላል.....
(በተቻለኝ መጠን ታሪኩን ዋና ዋናውን አጠር አጠር እያደረኩ ለመፃፍ ሞክሪያለሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን ከስር አስፍሩልኝ በእንደዚህ አይነት ህይወት ውስጥ ያላችሁት እናንተ ብትሆኑ እውነት መቋቋም ትችላላችሁ???!)
🔻.. አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtu@Kezerareaction33' rel='nofollow'>be.com/@Kezerareaction333
@Kezerareaction33' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@Kezerareaction33
💗 ጥቁር ልብ 💗