እኔኮ ከግሩፕ ውስጥ ነው አውጥቼ ያወራሁሽ ቴሌግራም ላይ ደሞ ቁጥርሽ አይወጣም ላኪልኝና እደውልልሻለሁ አለኝ።
እሺ ብዬ ላኩለት ።
በቃ እደውላለሁ ብሎ ከonline ወጣ እኔም እንቅልፌን ተኛሁ።
አምስት ሰአት አካባቢ ላይ ስልኬ ጠራ በእንቅልፍ ልቤ አነሳሁት ሄሎ ኤልዱ ሲለኝ እንዴት ብድግ እንዳልኩ ሁላ አላቅም ባንዴ ነበር እሱ መሆኑን ያወኩት ምነው በዚህ በሌሊት በሰላም ነው አልኩት።
አዎ በአምስት ብር የአንድ ሰአት ፍሪ ፓኬጅ ገዝቼ ነው እስከ ስድስት ሰአት ይቆያል ፈታ ብለሽ አውሪ አለኝ።
ድምፁን ስሰማ የማወራው ሁላ ጠፋብኝ እየደገምኩ ተመሳሳይ ነገር ማውራት መጠየቅ ጀመርኩ ።
እሱ ምንም አልመሰለውም ፈታ ብሎ ጥያቄዎችን ይጠይቀኛል ።
እህት አለሽ ወንድምስ??
ቤት ውስጥ ስንት ናችሁ ምን ያናድድሻል ምን ያስደስትሻል ,ክላስ ውስጥ ለምንድነው በዛ ልክ ኮስታራ የሆንሽው ?? ብቻ ስለራሴ ማወቅ ያለበትን ያህል ጠየቀኝ ።
እያሱ በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው ጥሎብኝ ሰዎችን አይቼ ከሚገዛኝ ነገር አንዱ ሲያወሩ እርጋታቸው ነው።
እያሱ እንደዛ ነው አንዱን ወሬ ጀምሮ ወደሌላኛው አይዘልም ሲያወራ አይቸኩልም ካፉ ሚወጡት ቃላት ተዘጋጅቶበት የሚያወራ ነው ሚመስሉት ብቻ ፈጣሪ በሚያቀው ምን ምን እያወራን 6 ሰአት እንደሞላ ማስታወስ አልችልም ግን እስከዛ እያወራን ነበር መጨረሻ ላይ ስልኩን ከመዝጋቱ በፊት ሳረሳው በጣም ቆንጆና ደስ የምትይ ልጅ እንደሆንሽ ሳልነግርሽ ማለፍ አልፈልግም ሀብታም ብሆን ኖሮ ሳድግ አንቺን ነበር ማገባው አለኝ።
ከት ብዬ ሳኩኝ ይሄ ከልብ የመነጨ ደስታ ሚባለው አለ አደል በቃ ከልቤ ደስ አለኝና ለትዳር ሀብት መስፈርት ይሆናል እንዴ አልኩት??
ግጥም አድርጎ ነዋ ለነገሩ ልጅ ነሽ አሁን ብዙም አይገባሽም ወደፊት ታቂዋለሽ በቃ ደና ደሪ አለኝና ስልኩ ተዘጋ ።
ደሞ ሚገርመው እሱም ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ልጅ ነው።
ስልኬን እያየሁ ፈገግ አልኩና መልሼ ኩስትር አልኩ። ምን እየሆነኩ ነው ሆ የምን መጃጃል ነው አልኩኝ ለራሴ መልሼ ደሞ ወይኔ ግን ታድሎ እንዴት እንደዚህ ፈጣሪ ሁሉን አሟልቶ ይሰጠዋል እልና መልሼ ፈገግ እላለሁ ብቻዬን ድራማ ስሰራ እንቅልፌን ተኛሁ።
ጠዋት ተነስቼ ክላስ ስገባ እያሱን እንደማየው እያሰብኩ ግቢው ውስጥ እስክደርስ ጓጉቼ ነበር።
ዴቭ ጠዋት ሲመጣ በቃ በጣም በሚባል ደረጃ አምሮበት ነበር
እንዴየሁት ፈገግ አልኩና ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ሙሽራ መስለሀል አልኩት ሰላምታ እየተቀያየርን።
ያው አንዳንዴ ያስፈልጋል እስኪ እናንተን እንምሰል ብዬ ነው አንቺ ምን እያገኘሽ ነው ሁሌ ሙሽራ መስለሽ ምትወጭው አለኝ።
ኦኦ ዛሬ አለባበስህ ብቻ አደለም ምላስህም ተቀይሯል በል በል እንሂድ ብዬው ጉዟችንን ጀመርን።
ወደ መኪናው ሲገባ የሸተተኝ ሽቶ ይለይ ነበር እንዴ ዛሬ ምትሄድበት አለህ እንዴ ከወትሮው ለየት ብለኽብኛል አልኩት።
አዎ አንድ ፕሮግራም አለኝ አንቺን ሳላደርስ እንዳልሄድ ብዬ ነው አለኝ።
አረ ችግር የለውም ነበር ነግረኸኝ ብትቀር ኖርማል ነው
ለማንኛውም ግን ዛሬ መጠለፍህ ነው ዘጠኝ ሰአት መጥቶ ሚወስደኝ ሰው ማጣቴ ነው ጠረንህ ሁላ ከሩቅ ይጠራቸዋል አልኩት።
አረ የምርሽን ነው አንቺን ከሩቅ ጠርቶሻል እንዴ አለኝ።
አረ እኔ ባይጠራኝምኮ ወዳንተ መምጣቴ አይቀርም ነበር አልኩት እየሳኩ።
እሱም እኔም በጣም እያወራን ትምህርት ቤቴ በር ላይ ደረስን ልወርድ ስል በል በቃ መመለስህንም እንጃ ልሰናበትህ እንጂ ብዬ ቀልጄበት ቻው ብዬው ከመኪናው ወረድኩ ተከትሎኝ ወረደና መመለሴን ከተጠራጠርሽማ በቃ ልሰናበትሽ ብሎ አቅፎ አንጠለጠለኝ ስስቅ ተማሪ እንዳያየኝ ሳቄን ዋጥ አድርጌ አንተ አውርደኝ ጉዴ ፈላ በቃ አስተማሪ አየኝ አልኩት እንዲደነገጥ ብዬ
🔻ክፍል ስድስት ነገ ማታ3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtu@Kezerareaction33' rel='nofollow'>be.com/@Kezerareaction333
@Kezerareaction33' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@Kezerareaction33