ፅጌሬዳ
ክፍል 10
ከዛን ቀን ቡሀላ ከማሂጋ ሳንገናኝ ቀረን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ያህል አልመጣችም ነበር።
ጎዳና ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ተኝቼ ሰማይ ሰማይ እያየሁ እንባዬ እየወረደ ነበር ማሂ ካባቷጋ በመኪና ወደኛ የመጣችው።
ለምን እንደሆነ አላቅም ሳያት ደስ አለኝ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ እሷን ላለማየት ወደ ሌላ ቦታ ፊቴን አዞሩክኝ አባቷ በቅርቡ ቤታቸው ውስጥ ትልቅ ደስታ እንዳለና ሁላችንም ፏ ብለን የክብር እንግዳ እንድንሆን እንደሚፈልጉ ወጫችን እሳቸው እንደሚችሉን ነገሩንና እኔን ግን ለብቻዬ ማናገር እንደሚፈልጉ ወደ መኪናው እንድገባ በእጃቸው ምልክት ሰጡኝ እሳቸውን እንቢ ማለት ስለደበረኝ ከኋላ ገባሁ ማሂም ከኔ አጠገብ ከኋላ ገባችና ቁጭ አለች አባቷ ቀጥታ ወደፊት ነዱት ።
ሁላችንም ዝም አልን እኔም ዝም ማሂም ዝም አባቷም ዝም የሆነ የተጣለለ ግቢ በር ላይ ሲደርሱ ክላክስ አደረጉና በሩ ተከፈተላቸው ከመኪናው ወረድንና ገባን ግቢው ውስጥ ግር ግር በዝቷል ሁሉም እኔን የተለየ ፍጡር አድርገው በተለየ መልኩ አዩኝ ከሰራተኛ እስከጥበቃ ድረስ ገላመጡኝ።
ሁሉም በአግራሞት እኔን እኔን ነው ሚያዩት የዛኔ ማናቸውንም ላለማየት አንገቴን ደፋሁኝ።
አባቷ እየመሩን ወደ አንድ ክፍል ገባን የቤቱ ስፋት ፅዳት ለጉድ ነው።
ማሂን አንቺ ወደራስሽ ጉዳይ ሂጂ እኔና እሱ እናወራለን አሏት እሺ ብላ ወጣች።
እንዴት ነህ የኔ ልጅ አቶ ሳሙኤል እባላለሁ ብለው እጃቸውን ዘረጉልኝ ድምፃቸው በራሱ ግርማ ሞገሱ ያስደነግጣል ።
ዝም ብዬ እጃቸውን ጨበጥኳቸውና መሬት መሬት እያየሁ ዝም አልኳቸው።
ጥሩ ስላንተ ማሂ ሁሉንም ነግራኛለች በጣም አዝኛለሁ ግን በጣም ስተት ነው የሰራኸው ከመጀመሪያው ፊደልን መርጠህ ቤተሰቦችህን ስትተው አንዱን ስተት ሰራኽ ከዛም ደሞ ፊደል ስትሞት ነገሮችን በመጋፈጥ ፈንታ ጎዳና ላይ እራስህን በሱስ መሸሸግህ ደሞ ሁለተኛውና ትልቁ ስተት ነው ።
እኔ ከማሂ እናትጋ ስተዋወቅ ምንም አልነበረኝም እሷም ምንም አልነበራትም ነበር።
ሁለታችንም አብረን ሰርተን እንቀየራለን ብለን አምነን ወደ ትዳር ገባን።
ለድፍን ሰባት አመት ሁለታችንም ያለማቋረጥ ቀንና ሌት ሰርተን እራሳችንን በኢኮኖሚ ከገነባን ቡሀላ አሁን ደሞ ልጆች ነው ሚያስፈልጉን ብዙ ልጆችን እንውለድ ብለን እቅድ አወጣን ።
ማሂ ተረገዘች ተወለደች አባት ሆንኩኝ እሷም እናት ሆነች ቤታችን በደስታ ተሞላ ማሂ በተወለደች በ35 ቀኗ እናቷ አረፈች ምክንያቱም ስትወልድ ስቲሽ ሲያደርጓትና ሲሰፏት ደም ስሯን አግኝተውት ነበር ።
የሷ እናት ከሞተች ቡሀላ መኖር አስጠላኝ ባገኘሁት አጋጣሚ በሙሉ ለመሞት አስብ ነበር ግን አላደረኩትም።
ፍቅሬን ናፍቆቴን ጉዳቴን በውስጤ ዋጥጥ አደረኩኝና ከበፊቱ የበለጠ ጠነከርኩኝ ይኸው እዚህ እድሜ ላይ እስክደርስ ድረስ ሴት ሚባል አጠገብ ደርሼ አላቅም ልቤን አብሬ ከማሂ እናትጋ ቀብሬዋለሁ ።
ግን አየህ ለማሂ የሚያስፈልጋትን ህይወት ሰጥቻታለሁ እናቷ አንዴ ሞታለች በህይወት የቀረችኝን ማሂን ግን መንከባከብ አለብኝ ።
አንተ ፊደልን ከምትወዳት አስርሺ እጥፍ እኔ የማሂን እናት እወዳት ነበር በማጣቴም በማግኘቴም አልተለየችኝም ነበር አብረን ለማርጀት ቃል ተገባብተን ነበር ሲከፋኝ ደስ ሲለኝ ምደገፍባት እሷ ነበረች ግን በቃ ሞተች ።
አንተም ከሞተችው ይልቅ በህይወት ያሉትን መንከባከብ እንጂ ከሞተችውጋ አብረኽ መሞት የለብህም ነገ ሌላ ቀን ነው እኔ ያንን ጊዜ ጥንክር ብዬ ህመሜን ዋጥጥ አድርጌ የሚመጣብኝን ሁሉ ስለተጋፈጥኩ ይኸው ማሂን ለመዳር እየተዘጋጀሁ ነው ልጄ ለወግ ማእረግ ልትበቃልኝ ነው የዛሬ ሳምንት ሰርጓ ነው አሉኝ። ምን እንዳስደነገጠኝ አላቅም ቀና ብዬ አየኋቸው ....
ፍዝዝዝ ድንዝዝ በራሴ አፈርኩኝ ተናደድኩኝ ምን እየሆንኩ ነው ከራሴጋ ሙግት ጀመርኩ።
የማሂ አባት ቀጠሉ እኔ በህይወት ዘመኔ ሁለት ነገር በጣም ይምታታብኛል።
አንደኛው ምናለ ሌላ ሴት ባገባሁና ለማሂ እህትና ወንድም በሰጠኋት እላለሁ ሌሎች ሰዎች እህቴ ወንድሜ እያሉ ሲያወሩ እሷ ልክ እንደብርቅ ሲሆንባት ሳይ እናደዳለሁ አሁን ካለፈ ቡሀላ ይከነክነኝ ጀምሯል።
ባንድ በኩል ደሞ በህይወቴ ያፈቀርኩት አንድ ሰው ነው ለሷ ታማኝ ሆኜ እድሜ ዘላለሜን ከልቤ ሳትወጣ ልጃችን ፍሬያችንን ለክብር በማብቃቴ እኮራለሁ።
አንተም ከህመምህ አገግም አሁን አንተ እያደረክ ያለኸው ልክ አደለም ።
ለፊደል የሰጠኻትን ቦታ ግማሹን እንኳን ለቤተሰብህ ስጥ አቃለሁ ሴት ተከትለህ ከቤት ወጥተህ በባዶ እጅህ ጎዳና ተዳዳሪ ሆነህ መመለስ ያሳፍራል ግን አታስብ እኔ ሙሉ የቤተሰቦችህን ሀላፊነት እወስዳለሁ ቤተሰቦችህ ትደርሳለህ ብለው ሚጠብቁት ቦታ ላይ ባትደርስ እንኳን ቢያንስ ግማሹን ሆነህ ታሳያቸዋለህ በኔና በልጄ ላይ እምነት ይኑርህ አሉኝ።
እንባዬ መጣ ተነስቼ አቀፍኳቸው ሲበዛ ደስ ሚሉ ሰው ናቸው ደግነታቸው ፊታቸው ላይ ይታያል።
ስለሚስታቸው ሲያወሩ ልክ እንደዛሬ ነው ፍቅራቸው ደስ ይላል።
ታሪካቸውን ስሰማ ትንሽ ተፅናናሁ ለካ ፈጣሪ እኔን ጠልቶኝ አደለም ሁሉምጋ ያጋጥማል ለካ ብዬ ተፅናናሁ።
እና ቆይ እኔን እንዴት ነው ምታግዙኝ አልኳቸው??
✎ክፍል 11 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333